ATLAS COLLEGE_official
694 subscribers
1.62K photos
26 videos
23 files
216 links
❤️ Welcome to the Official Telegram channel of ATLAS BUSINESS AND TECHNOLOGY COLLEGE. Join us and get exciting updates.
Download Telegram
#እንድታውቁት

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን በድጋሚ የሚፈተኑ ተፈታኞች በበየነ መረብ (ኦንላይን) መመዝገብ እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተፈታኞች በራሳቸው የሚመዘገቡበት አድራሻ https://register.eaes.et/Online እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ የበይነ መረብ (አንላይን) ምዝገባ መተግበሪያ ራስ አገዝ (self services ) ሲሆን ተመዝጋቢዎች የሚፈልጉትን ድጋፍ በመጠየቅ ከማዕከል ማግኘት ይችላሉ ተብሏል።

(እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል ከላይ ይመልከቱ)

(የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)
Forwarded from ETA Re-Registration
#ማስታወቂያ
ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምርት ተቋማት
ባሉበት

ጉዳዩ፦ በጥር ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የመዉጫ ፈተና ውይይት ስለሚኖር እንድትሳተፉ ስለማሳወቅ፤

በ2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞችን ምዝገባ ለማካየድ ይረዳን ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የሶፍት ዌር ቴምፕሌት በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ታህሳስ 28/2017ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ላይ የሚጀምር ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሶፍት ዌር ቴምፕሌት አጠቃቀም ዙርያ ላይ በzoom meeting ማብራርያና ገለፃ ስለሚደረግ እንድትሳተፉ እያሳሰብን የzoom meeting link ቀደም ብሎ የሚለቀቅ ይሆናል፡፡

#መረጃ_44
Forwarded from ETA Re-Registration
#ማስታወቂያ
   ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምርት ተቋማት
   ባሉበት

                    ጉዳዩ፦ በጥር  ወር 2017 ዓ.ም ለሚሰጠው  የመዉጫ ፈተና  ውይይት ስለሚኖር እንድትሳተፉ ስለማሳወቅ፤

በ2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞችን ምዝገባ ለማካየድ ይረዳን ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የሶፍት ዌር ቴምፕሌት በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ታህሳስ 28/2017ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የሶፍት ዌር ቴምፕሌት አጠቃቀም ዙርያ ላይ በzoom meeting  ማብራርያና ገለፃ እነደሚደረግ መግለጻችን ይታወቃል ስለሆነም ከዚህ በታች በተቀመጠዉ የzoom meeting  link እንድትሳተፉ እናሳስባለን፡፡

👇👇👇👇

Join Zoom Meeting
https://zoom.us/j/96289753941?pwd=Rw83jFlfOKd9vJyzLctbnYVXKfzedW.1
Meeting ID: 962 8975 3941
Passcode: 013658

#መረጃ_45
Noted
#MoE

የመውጫ ምዘና ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 12
/2017 ዓ/ም ድረስ እንደሚሰጥ ተገለጸ።

በክረምት በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ድግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ሲከታተሉ ቆይ የመውጫ ምዘና ለሚጠባበቁ መምህራን የመውጫ ምዘና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደርጓል።

በዚህም የመውጫ ምዘናው ከየካቲት 10 እስከ የካቲት 12/2017 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን መምህራኑ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዳያድረጉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ ምዘናው በየአቅራቢያ ባሉ ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጥ መሆኑን ገልጾ " በቀጣይ ክልል / ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮዎች በኩል የምናሳውቃችሁ ይሆናል " ብሏል።

#MinistryofEducation
Enjoy these #Newgreetings in some of the world’s most beautiful languages, reflecting ABTC’s incredible #UnityInDiversity!

As we step into 2025, we wish that our #ABTCFamily weaves stronger bonds and achieves greater milestones.

Leave your comments!

#ABTCstaff#Welcome2025 #ABTCForYou #LPUDiaries #ABTCReview #LifeAtABTC #GlobalFamily #BestCollege #TopCollege #ABTCstaffAchievements #DreamBIG #AchieveBIG
ዝርዝር መረጃውን https://ngat.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን
የመውጫ ፈተና ከጥር 26 እስከ  ጥር 30 ይሰጣል።

የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ለአዲስ እና በድጋሜ ለመፈተን ላመለከቱ በሙሉ እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲዎች የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡

ሚኒስቴሩ ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ፥ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ አሳስቧል፡፡

በሚኒስቴሩ የመምህራን ትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ከሳምንት በፊት የተጻፈው ደብዳቤ፥ "በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ ለመሸጋገር የትምህርት ማሻሻያ ስልጠና የሚከታተሉ መምህራን፣ ስልጠና ሳያጠናቅቁ መረጃ እየተሰጠ እንደሆነ" ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡

በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ለማሻሻል ስልጠና እየወሰዱ ያሉ መምህራን፣ የማስተማር ሙያ (PGDT) መውሰድና የመውጫ ምዘና ማጠናቀቅ እንዳለባቸው በመስከረም 2017 ዓ.ም የትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁን በደብዳቤው ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ ክልሎች ከዚህ በተለየ የማስተማር ሙያ ስልጠናም ሆነ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን፣ የደረጃ ዕድገት እየሰጡ መሆኑናቸውን መረዳቱን አሳውቋል፡፡

ማንኛውም ሠልጣኝ የትምህርት ማስረጃ ማግኘት የሚችለው የትምህርት ምዘና ወስዶ ማለፍ ሲችል መሆኑ እየታወቀ፣ የዲግሪ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ በማድረግ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያና የደረጃ ዕድገት የሚሰጡ አንዳንድ ተቋማት መኖራቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው መሪ ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ወጪያቸውን በመሸፈን የሚያስተምረው የበቁ መምህራንን ለማፍራት ነው ያሉት ኃላፊው፤ ማንኛውም ተቋም የመውጫ ምዘና ወስደው ላላለፉ ዕጩ መምህራን ምንም ዓይነት ማስረጃ እንዳይሰጥ በደብዳቤ ማሳወቁን አስረድተዋል፡፡
ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በምዝገባ ላይ ነን!
**
የTVET ሙሉ መረጃ ከዚህ በታች ይገኛል።
👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾

*TVET full information*
1. Pharmacy
2. Clinical Nursing
3.Midwifery
4.Information Technology
5. HRM
6. Accounting
7. Secretarial Science
8. Marketing
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ነገሮች
  👉🏽  የትምህርት ማስረጃ ማለትም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ማስረጃ
  👉🏽 የመመዝገቢያ እና የትምህርት - ክፍያ
  👉🏽 2 ጉርድ ፎቶ

አትላስ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
       ጋምቤላ ካምፓስ
176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ

👉ፈተናው ከጥር 26 እስከ 30 ድረስ ይሰጣል

ጥር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ 176 ሺሕ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው 176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና ለአሐዱ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የሚገኙ በሁሉም የኒቨርሲቲዎች ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን፤ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ያልሆነው የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ጭምር በዚህ ፕሮግራም ተካታች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የግል ኮሌጆችን በሚመለከት አሐዱ ላቀረበላቸው ጥያቄ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ኮሌጆች ላይ ገብቶ ለመፈተን የሚያስችል መዋቅር እንደሌለው በማንሳት፤ ነገር ግን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የመንግስት ተቋም በኩል መፈተን እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የፈተና ቀኑ በተለያዩ ምክንያቶች ዘግይተው ትምህርት የጀመሩትን ዩኒቨርሲቲዎች ታሳቢ ያደረገና በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ከተረጋገጠ በኋላ መወሰኑን ተናግረዋል።

ፈተናውን ለመስጠት ታቅዶ የነበረው ጥር 14 እና 15 የነበረ ቢሆንም፤ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እኩል ትምህርት ባለመጀመራቸው ወደ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም. እንዲሸጋገር መደረጉን ገልጸዋል፡፡
በዚህ የፈተና ፕሮግራም ተንቀሻቃሽ ስልክና የወረቀት ፅሁፍ ይዞ መገኘት ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን የገለጹት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ "ተፈታኞች መታወቂያ መያዝና ከፈተና ፕሮግራሙ 30 ደቂቃ ቀድሞ ቦታው ላይ መድረስ ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል፡፡ የወጣው ፈተናም ከተማሩት በመሆኑ ሳይጨነቁ በተረጋጋ መንፈስ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የዘንድሮው የዩኒቨርስቲዎች የመውጫ ፈተና ከዚህ በፊት ይሰጥ እንደነበረው ሙሉ ለሙሉ በኦንላይን የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጥር 26 እስከ 30 ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

የተማሪዎች ፈተና እንደተጠናቀቀ ቅዳሜ ማለትም የካቲት 1 ቀን የመምህራንን ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ መምህራን ፈተና ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ለአሐዱ በሰጡት ቃል ገልጸዋል።
#Update

ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ያደረግነው ውይይት።

ለ2017 ዓ.ም አጋማሽ መውጫ ፈተና ዝግጅት

ጥር 25/2017 ዓ.ም

የአትላስ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የ2017ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው መውጫ ፈተና ተፈታኞች በብቃት እንዲያልፉ በእውቀት በቴክኖሎጂ እና በስነ-ለቦና ብቁ ሆነው እንዲገኙ እና ያለ ምንም ስጋት እና ጭንቀት ፈተናቸውን እንዲያልፍ : ተጨማሪ ሰዓቶችን በመጠቀም በተጋባዥ መምህራን እና የተለያዩ platform በመጠቀም ስናሰለጥን መቆየታችን ይታወሳል።

በዛሬው እለት ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጋር በነበረን የምከከር መድረክ: የኮሌጃችን የexit exam ተፈታኞች  ጥር 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ከኮሌጃችን የተመደቡ ተማሪዎችን የሚፈተኑበትን አዳራሽ እና ዝግጅት ጎብኝተናል።
በዩኒቨርሲቲው በኩል ለተደረገልን አክብሮት አጅግ እናመሰግናለን።

በዚህ መሰረት ተፈታኞች በአትላስ ቢዝነስና ቴክኖሎጂ ኮሌጁ ሆሳዕና ካምፓስ በመሔድ ተገቢውን መመሪያ በመውሰድ ለፈተናው  በዩኒቨርሲቲው በተያዘለት ፕሮግራም መሠረት የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያዎችን በመከተል ዝግጁ እንድትሆኑ አሳስባለሁ።

#አትላስ ቢዝነስና ቴክንሎጂ ኮሌጅ