ASTU Network ®️
4.2K subscribers
1.47K photos
33 videos
291 files
352 links
🛜 ASTU Network ®️

➲ Join us || @ASTU_Network ||
|| @ASTU_Network_Group ||

📚 Library: @ASTU_Network_Library

👁‍🗨 We are here to keep you updated!

➲ Admin 📩
👤 @NS_Nazu

Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷]

|➲| @ASTU_Network
Download Telegram
ፌስታል‼️

በኢትዮጵያ ከጥር 23 ቀን 2018 ጀምሮ፣ ስስ ፌስታል መጠቀም እንደማይቻልና ይዞ የተገኘም ከ5000-10,000 ብር እንደሚቀጣ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል። በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም፣ ማመረት እና ወደ አገር ውስጥ ማስገባት በገንዘብ እና በእስራት የሚያስቀጣ ድንጋጌ የተካተተበት ረቂቅ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ይታወሳል።

The takeaway thing... 🌚🫠😅
.
🤣40👀6🤬31🤷‍♀1🫡1💅1
ASTU Network ®️
ፌስታል‼️ በኢትዮጵያ ከጥር 23 ቀን 2018 ጀምሮ፣ ስስ ፌስታል መጠቀም እንደማይቻልና ይዞ የተገኘም ከ5000-10,000 ብር እንደሚቀጣ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል። በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም፣ ማመረት እና ወደ አገር ውስጥ ማስገባት በገንዘብ እና በእስራት የሚያስቀጣ ድንጋጌ የተካተተበት ረቂቅ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መፅደቁ ይታወሳል። The takeaway…
በዚህ ጉዳይ የግል አስተያየት...

በመጀመሪያ ይሄ ረቂቅ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከመቅረቡ እና ተወካዮቹም ዝምብለው አጨብጭበው ከማጽደቃቸው በፊት በትክክል አስበውበታል ወይ አላሰቡም! እነሱ አጨብጭበው ማጽደቅ አይሰለቻቸውም 😏... ምን ቸገራቸው ለራሳቸው ጥሩ ኑሮ እየኖሩ ነው። ደሃውን ግን ማን ያስባል😔

Almost ሁሉም ሰው እቃ ወይም የተለያየ ነገር ለመያዝ ቀለል ባለ መልኩ የሚጠቀመው ፌስታልን ነው። ታዲያ ፌስታል ሲከለከል ሌላ እሱን የሚተካ ነገር ተዘጋጅቷልወፍ! 🤷‍♂️
ይሄ ህግ ከጸደቀ በኋላ ፌስታል ከመጠቀም ወደ አለመጠቀም የመሸጋገሪያ በቂ ጊዜ ተሰጥቷል አልተሰጠም! 🤷‍♂️

እርምጃው ትክክል ሊሆን ይችላል እኮ ፣ ነገርግን በትክክለኛው ጊዜ አይደለም ሊተገበር ያለው። በቅድሚያ የዜጎች የኑሮ ሁኔታ መሻሻል ይኖርበታል። 😕

ቆይ የዚህች ሀገር ደሃው ማህበረሰብ ምን ይሁን የኑሮ ውድነቱ ሌላ ታሪክ! ይቀንሳል ይሻሻላል ሲባል ጭራሽ እየጨመረ ነው። ደሃው ሰው ቡሌ እንኳን ሰብስቦ እንዳይበላ ይኸው ፌስታል መጠቀም እየተከለከለ ነው... 😁

የቴካዌይዋን ነገር ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን! 😂

ኧረ እስኪ መጀመሪያ ሀገራችን 🇪🇹 ሰላም ትሁን ፤ ሌላው ቀስ ብሎ ይደርሳል! 🥱😒😑
.
👏1210👌2👍1😭1😨1
If anyone has a used scientific calculator for sale, pls DM us!

📥 Sc.Calculator

@Astu_marketplace
#ዜና_መዝናኛ 😸

ጊነስ የአለም ሪከርዶች የኬንያዊቷን ለ48 ሰዓታት ዛፍ አቅፎ የመቆየት ተግባር በሪከርድነት መዝግቧል።

ትሩፊና ሙቶኒ የተባለች ኬንያዊት ከፈረንጆቹ ጥር 31 እስከ የካቲት 2 ድረስ ለሁለት ቀናት ያህል ዛፍ አቅፋ መቆየት የቻለች ሲሆን ጊነስ ይህንን በሪከርድነት መዝግቧል።

ምንም እንኳን ጊነስ ለየካቲቱ ሪከርድ አሁን ገና እውቅና ቢሰጣትም ሙቶኒ ከቀናት በፊት ለሶስት ቀን ወይም 72 ሰዓታት ዛፍ በማቀፍ ይህንኑ ሪከርድ አሻሽላለች።

ሙቶኒ የ48 ሰዓቱን ዛፍ የማቀፍ ሪከርድ ለመያዝ 5 ወር ዝግጅት ነበራት ሲባል ሙቶኒ ዛፍ የማቀፉን ተግባር የፈፀመችው ዛፍ ማቀፍ የሚሰጠውን የአዕምሮ ሰላም ላይ ያለውን ንቃት ለመጨመር እንደሆነ ገልፃለች።

ጊነስ የአለም ሪከርድ ሙቶኒ 72 ሰዓት ማቀፏን በሪከርድነት ለመመዝገብ ያሏትን ማስረጃዎች እንድታቀርብ ጠይቋል።

ጊነስ የቀረበውን ሪከርድ ከተመለከተ በኋላ የሙቶኒን የ48 ሰዓታት ሪከርድ ከቀናት በፊት ወዳሻሻለችው የ72 ሰዓት ሪከርድ ከፍ ያደርገዋል።

ዘገባው የኬንያንስ ነው።

በቃ እኛም የሆነ ቦታ ቁጭ ብለን ሪከርድ ሰብረን ጊነስ የአለም ሪከርዶች ላይ እንመዝገባ... 😂
.
🤣102👍1💅1💊1
If anyone has a used scientific calculator for sale, pls DM us!

📥 Sc.Calculator

@Astu_marketplace
1
Good Morning, everyone! 👋🌅

Just a quick reminder for today... 😁

1. Today is Monday — the first day of the week... 🥲🥱
2. It's December 15, 2025. (ታህሳስ 6 ፣ 2018) 🙆🏻‍♂
   > Only two weeks left until 2026! 🤯
   > And exactly three weeks until our final exam... 🫠

Happy Monday! 🙌

Have a great day! 🤗
.
9😭7👍3🍾3
DATA_TEMPLATE_LATEST_2018_UPDATED_PRIVATE.xlsx
19.7 KB
በጥር 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ እጩ ምሩቃን ዝርዝርና ሙሉ መረጃ መሙያ ቅፅ

|| @ASTU_Network
4
#ሰበር 🔥

የሁሉም ፈቃድ ተሰረዘ‼️

የሁሉም የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች ፈቃድ ሙሉ በሙሉ ተሰረዘ‼️


የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰሩ የሁሉም የስፖርት ውድድር ውርርድ (Betting) ድርጅቶች የተሰጠውን የሥራ ፈቃድ ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መሰረዙን አስታውቋል።

የሥራ ፈቃዱ የተሰረዘው በውርርድ እና በፋይናንስ ዘርፎች ላይ በተካሄደ ጥልቅ አገር አቀፍ ግምገማ ውጤት ላይ ተመስርቶ ነው።

የሕዝብን ጥቅም ማስከበር እና የዘርፉን ስርአት ማስተካከል ነው።

በሂደት ላይ ያለው ምርመራ በዘርፉ ውስጥ ሰፊ የሆነ ሕገ-ወጥ አሰራር፣ የፈቃድ ውል ጥሰት፣ እና ለብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሚሆን ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር መኖሩን በግልጽ አሳይቷል።

የሎተሪ አገልግሎቱ ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ውሳኔው በሥራ ላይ ባሉትና ቀደም ሲል በይፋ በታገዱት በሁሉም የውርርድ ድርጅቶች በእኩልነት ተፈጻሚ እንደሚሆን ገልጿል።

የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እና ሲስተም ኦፕሬተሮች/አቅራቢዎች ወዲያውኑ እንዲያቆሙ የተሰጠው መመሪያ፡

* ከታህሳስ 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካልም ሆነ በዲጂታል መንገድ የሚካሄድ ማንኛውም የውርርድ ሥራ እንዲቋረጥ ተደርጓል።

* ሁሉም የገንዘብ ማስገቢያ መንገዶች አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ ታዝዘዋል።

* አዲስ ውርርድ መቀበል ፈጽሞ አይቻልም።

ይህ እርምጃ በሀገሪቱ የፋይናንስ እና የብሔራዊ ደህንነት ስጋት የሆኑ ህገ-ወጥ አሰራሮችን ለመከላከል የተወሰደ ወሳኝ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።

|| @ASTU_Network
👏157😭3👎1🔥1
Student name list.pdf
2.6 MB
Announcement:

Students listed above are informed that their certificates for participating in the ASTU Cleaning Campaign can be collected from Tuesday to Thursday (December 16–18) at Block 302, Room 9, between 12:00–3:00 (night) local time.

Please note that certificates will only be issued during the stated dates and time. Students who come before or after the arranged schedule will not be served.

|| @ASTU_Network
😁21
#Ad

Be their best!

Looking for a truly thoughtful gift 🎁?

Order your beloved ones custom realistic portrait that's

Unique.
Meaningful.
Unforgettable for your loved ones
.

Be their best, for a lifetime.

View prices and place your order through this bot
@jaredstudio_bot
6🔥2
‎" ከዛሬ ጀምሮ ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ይዘጋሉ፤ ትራንስፖርትን ጨምሮ ለበሽታዉ አስጊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ገደብ ጥለናል" - የዳሰነች ወረዳ አስተዳደር

‎በደቡብ ኦሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ በማርበርግ ቫይረስ ስጋት ምክንያት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ ሕዝብ የሚሰበሰብባቸዉ የትራንስፖርት እና የመዝናኛ ቦታዎች ላይ ዕገዳ መጣሉን የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ኡመር ኖኩዌ  ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

‎በአከባቢው አንድ ሰዉ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን ተከትሎ ዉሳኔው መተላለፉን የገለፁት ምክትል አስተዳዳሪዉ በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የሚመራ ግብረሃይል ተወያይቶ ዉሳኔ ማስተላለፉን ገልፀዋል።

‎በዚህም መሠረት በወረዳዉ የሚከተሉት ጉዳዮች ላይ ዕገዳና ክልከላ መጣሉን አቶ ኡመር ገልፀዋል።

‎በዚህም መሰረት ፦

➡️ ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ ሆነው ይቆያሉ፤

➡️ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት እንዳይሰጡና የሁለት እግር ሞተር ሳይክሎችም ከአሽከርካሪው ውጪ ሁለተኛ ሰው ላልተወሰነ ጊዜ መጫን አይችሉም፤

➡️ ሰርግ፣ ምረቃ፣ ድግስና በሀዘንም ህዝብ ሊያሰባስቡ የሚችሉ ሁኔታዎችም ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆሙና ቀብር በጤና ባለሙያዎች ስምሪት ብቻ እንዲከናወን፤

➡️ ዲ ኤስ ቲቭ (Dstv) ጨምሮ ፑል ቤቶች፤ ቤቲንግ ቤቶች እንዲሁም የምሽት ዳንስ ቤቶች፣ ጫት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግተው እንዲቆዩ፤

➡️ ሰዎች በቡድንና በብዛት የሚሳተፉባቸዉ ማንኛውም አይነት ስፖርታዊ ውድድሮች በወረዳዉ እንዳይካሄዱ ዉሳኔ መተላለፉን አብራርተዋል።

|| @ASTU_Network
7😭3😁1
If anyone has a used scientific calculator for sale, pls DM us!

📥 Sc.Calculator

@Astu_marketplace
#Ad

🌟 Stop Walking, Start Clicking! 🍔🍕

LIYU DELIVERY — Fast • Cheap • Reliable


🍕🍔 We deliver it ALL at ASTU:

- 🍲 FRESH FOODS from top restaurants
- 💧 WATER JARS right to your Dorm
- 🍔 PIZZA & BURGERS for your cravings


Hot and fresh — delivered to your dorm.


WHY LIYU?


Super fast delivery
🎯 Easy ordering – pick what you want in seconds
🛍️ Tons of choices
💸 Affordable for students


📣 ORDER NOW https://t.me/liyudelivery_bot

LIYU DELIVERY — Comfort delivered.
4
Lost 🆔

Name: Fahmi Abdi
ID.№: Ugr/34392/16

Contact: @Fahm798
4
#ከርዕስ_ውጪ

የህንድ 🇮🇳 ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ተቀብለዋቸዋል።

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ይፋዊ የስራ ጉብኝት የተለያዩ የሁለትዮሽ ውይይቶችን የሚያደርጉ ሲሆን ነገ ህዝብ ተወካዮችና ፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደርጋሉ።

Amazing! 🔥👌👏

🇪🇹 🤝 🇮🇳

||
@ASTU_Network
4👍2🔥1😱1