ASTU Network ®️
4.16K subscribers
1.44K photos
32 videos
288 files
346 links
🛜 ASTU Network ®️

➲ Join us || @ASTU_Network ||
|| @ASTU_Network_Group ||

📚 Library: @ASTU_Network_Library

👁‍🗨 We are here to keep you updated!

➲ Admin 📩
👤 @NS_Nazu

Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷]

|➲| @ASTU_Network
Download Telegram
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።

ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል። #Fortune

|| @ASTU_Network
👎52🤬8💔4😭32👍2😢1🏆1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Wishing you the best of luck on your midterm exams! Stay focused, believe in yourself, and remember to take breaks. 🤗

You've studied your best and now it's time to do your best! You've got this! 🫡 🙌

May God help us all achieve good results in our exams! 🙏

|| @ASTU_Network
🙏24🤗3🫡32👍1🕊1
Electronics Circuit I🤔🙄
.
😭45👌8🤣5👍4🍾3🤷‍♀2💔2
🔉 A2SV is accepting students for Generation 7!

The picture above shows the number of A2SVians who have been placed at top global tech companies such as Google, Bloomberg, Amazon, Goldman Sachs, and many more , and you could be next!

Check Placement -> here
What is A2SV training about?

A2SV (Africa to Silicon Valley) equips top university students with:

- Data Structures and Algorithms
- Problem Solving and Competitive Programming
- Project Development Experience
- Soft Skills and Interview Preparation

Students are mentored by Experienced Engineers , build real projects, and get fully prepared for international job and internship opportunities.

📍 On-site locations:

🇪🇹 Ethiopia — ASTU, AASTU, AAIT
🇷🇼 Rwanda (new!) — University of Rwanda, AUCA
🇬🇭 Ghana — University of Ghana

🌍 Not in these countries? You can still apply for remote education from anywhere in Africa.

-> it is FREE to Join

Who can apply?

Open to all university students with ambition, a growth mindset, and some problem-solving skill
Freshman upto GC
Any Departement



⚡️ Applications close soon act fast!

⏱️ It only takes 7 minutes to apply. Take your shot at joining A2SV G7 Education today!

👉 Apply now: https://form.typeform.com/to/wOWdCFrZ


DEADLINE: NOV 21
#A2SV #TechAfrica #SoftwareEngineering #CodingAfrica #A2SVGeneration7 #ASTU
32👍1
" የበሽታውን ምልክት አሳይተው የነበሩ 6 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ነገር ግን በላብራቶሪ ማረጋገጥ የተቻለው የሦስቱን ብቻ ነው " - ጤና ሚኒስቴር

የጤና ሚኒስቴር በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የተከሰተው የሄሞራጅከ ፊቨር (Viral Hemorragic Fever) በሽታ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መግለጹ ይታወቃል።

ይህን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።

በዚህ መግለጫ ላይ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እስካሁን በበሽታው 17 ሰዎች ተጠርጥረው ምርመራ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል።

በዚህም 3ቱ በላብራቶሪ ምርመራ በበሽታው መያዛቸው መረጋገጡን ገልጸዋል።

የበሽታውን ምልክት አሳይተው የነበሩ 6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የገለጹት ሚኒስትሯ፥ ነገር ግን በላብራቶሪ ማረጋገጥ የተቻለው የሦስቱን ብቻ መሆኑን ነው የገለጹት።

ምርመራ ከተደረገላቸው 17 ሳምፕሎች በሽታው በላብራቶሪ ማረጋገጥ የተቻለው በሦስቱ እንደሆነም ነው የጠቆሙት።

ምርመራውም በሀገር አቅም መደረጉን ነው የጠቆሙት።

|| @ASTU_Network
😭54
ASTU Network ®️
" በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል " ሲሉ ተናግረዋል።
አንዳንዶቻችሁ በምደባ ነው ወይስ በመጣንበት አከባቢ እያላችሁ እየጠየቃችሁ ነው። በእርግጥ ብዙም ግልጽ የሆነ ፣ ዝርዝር የተብራራ ነገር ባይኖርም የትምህርት ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ሲናገሩ እንደሰማነው “...ወደ አስተማረው ማህበረሰብ ተመልሶ...” ነበር ያሉት። ስለዚህ እንደዛ ነው ሊሆን የሚችለው እንጂ በምደባ ላይሆን ይችላል።

ገና ወደ ትግበራ ስላልተገባ ብዙ ግልጽ ያልሆኑ ነገሮች አሉ። ነገሮች በሂደት እየታወቁ እና ግልጽ እየሆኑ የሚመጡ ይሆናል።

|| @ASTU_Network
👎26🤬5💔5😭2
ASTU Network ®️
" የበሽታውን ምልክት አሳይተው የነበሩ 6 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ ነገር ግን በላብራቶሪ ማረጋገጥ የተቻለው የሦስቱን ብቻ ነው " - ጤና ሚኒስቴር የጤና ሚኒስቴር በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የተከሰተው የሄሞራጅከ ፊቨር (Viral Hemorragic Fever) በሽታ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መግለጹ ይታወቃል። ይህን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ሚኒስቴር መስሪያ…
🚨🚨 #ALERT 🚨🚨

በሽታው እየተስፋፋ ነው‼️😥

በቅርቡ የተከሰተው የማርበርግ ቫይረስ በሽታ እስከአሁን ድረስ በተከሰተበት ጂንካ አከባቢ ብቻ እንደሚገኝ ፣ ወደ ሌሎች አከባቢዎች እንዳልተስፋፋ እና ስርጭቱን ባለበት ሙሉበሙሉ ለመግታት እየተሰራ እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር መግለጹ ይታወቃል።

ነገርግን ይሄ ሳይሆን ቀርቶ በአርሲ ዞን አሰኮ ወረዳ ሁሉቆ ቀበሌ ላይ በማርበርግ ቫይረስ በሽታ እንደተጠቁ የተጠረጠሩ 13 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን መሰረት ሚዲያ ማረጋገጡን ዘግቧል።

"የአካባቢው አመራሮች መረጃውን ካወጣችሁ ተጠያዊ ትሆናላችሁ ብለው ፀጥ አስብለውናል። አሁን ላይ በአካባቢው የመንግስት ወታደሮች ተሰማርተው ማንም እንዳይወጣ ተከልክሏል" ሲሉ የአካባቢው የጤና ባለሙያች ተናግረዋል።

ነገሩ በጣም አሳሳቢ ነው... እንጸልይ! 🤲🙏

||
@ASTU_Network
😭37🙏6👀43😨1🙉1
#ለጥንቃቄ

📌 የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው
🦠

👉 ከአፍ፣ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ሥር ደም መፍሰስ፤

👉 ከፍተኛ ትኩሳት፣ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት፤

👉 የጡንቻ እና ጀርባ ህመም፤

👉 ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ፤

👉 ደረት፣ ጀርባ እና ሆድ ላይ በጣም ጎልቶ የሚታይ ሽፍታ...

|| @ASTU_Network
🙏122💊1
Hmmm... 🤔

ኧረ ወዴት እየሄድን ነው ወገን🤔


1. Entrance ከ 9-12 ያለውን መጽሐፍ አንብበው ይፈተኑ 🤯

2. University ገብተው ይፈተኑ 😑

3. ትንሽ ውጤት የሚያንሳቸው ተማሪዎች remedial course ይማሩ (ተጨማሪ አንድ ዓመት) ☹️

4. አንድ ዓመት የተማሩት የ remedial ዉጤት አይያዝ እንደገና ሬሜዲያል ከተማሩ በኋላ ይፈተኑ 🤨

5. የ Freshman የትምህርት አመት (ተጨማሪ አንድ ዓመት) 😫

6. ዩኒቨርስቲ ውስጥ ያለው ህይወት በአጠቃላይ... ትምህርቱ ፣ ፈተናው ፣ የሚፈልጉትን ዲፓርትመንት ማግኘት ምናምን... 😩😰

7. ከፍተኛ መጠን ያለው የ cost sharing ጭማሪ .... 💰🫥🤷‍♂️

8. ትምህርት ሲጨርሱ Exit exam ይፈተኑ ፤ የወደቁት እንዳይመረቁ 🎓💔

9. Exit exam የወደቁ ተማሪዎች በራሳቸው ወጪ ይማሩ 😳🙄

10. 3ኛ ዓመት ሲሆኑ (ለኢንጂነሪንግ አራት) /ለመመረቅ አንድ አመት ሲቀራቸው ማህበረሰብ ያገልግሉ (ለአንድ አመት ያስተምሩ) 🫠

ሌላም ካለ ጨምሩበት! 😸🤧

ቀጣይስ ምን ይመጣ ይሆን
እግዚኦ... 👐

||
@ASTU_Network
😭694💔3💯1
#የወንዶች_ቀን 🧔🏻‍♂🗿👨🏻

ዛሬ ሁላችንም መኖሩን የማናወቀው ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበራል 😁 lol 😸

እውነት ለመናገር ወንድ ልጅ ለዚህች ዓለም ያልሆነላት ነገር የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ወታደር 🧑‍🚀 ፣ የሀገር መሪ 👨🏻‍💼 ፣ ተመራማሪ 👨‍🔬 ፣ መካኒክ 👨‍🔧፣ የማዕድን አውጪ 👨‍🚒 ፣ በተለይም ደግሞ በጣም ጉልበት የሚጠይቁ ሥራዎችን ለቤተሰባቸው እና ለሀገራቸው ብለው ራሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው የሚሰሩ እልፍ የሆኑ ጀግኖች ወንዶችን መሬታችን አፍርታለች ሸኝታለችም።

ወንድ ልጅ ችግሩን ዋጥ አድርጎ ህመሙን ሸፍኖ እያንዳንዷን የሌላውን ችግር እየፈታ የሚኖር ነው። እንደ ሴት ልጅ ግልጽ ሆኖ ባያወራም ይሄ ተፈጥሮው ነውና የሚያበስለውም ነገር ስለሆነ እንዳለ መቀበል ያስፈልጋል።

ለአፍታ ችግሩን ለማውራት ቢሞክር... “አንተ ወንድ አይደለህ እንዴ?” ይባላል! 😑 አሁን እዛ ውስጥ አንገባም! 👐

በተለይ ደግሞ ማህበረሰባችን ሁልጊዜ ትልቁን ኃላፊነት (burden) የሚሰጠው ለወንዶች ነው። ሁሌ እንደምንሰማው ገንዘብ ያለው 💰 ፣ ቤት ያለው 🏠 ፣ መኪና ያለው 🚘 ይባላል 😂... ግን እውነት ለመናገር ❝ያላት❞ ብዙ ጊዜ አይባልም 💔... ወይኔ በላቸው!!! 🤧😁

ሁላችሁም ወንዶች ላመናችሁበት ነገር ሚዛናዊ ሆናችሁ በአቋማችሁ እንድትጸኑ ዓለማቀፋዊው የወንዶች ምክር ቤት ጥሪ ያቀርባል! 💪🏽🌎😁

አዎ አንተ ወንድ ነህ‼️🫵
አለማችን አንተን በጣም ትፈልጋለች! 🌍
ለህልምህ ፣ ለራዕይህ እና ለአላማህ ጸንተህ ቁም!

እውነትም ሰዎቹ እንደሚሉት “አንተ ወንድ አይደለህ እንዴ የምን መልፈስፈስ ነው😁 ጠንከር በል እንጂ MAN! 🙂

ቀና ቀና በል BRO! 🫶🏽🫂
በመከራህ ታገስ! ፈጣሪህን አስብ!
ተስፋ አትቁረጥ! በርታ! ጽና!
ይሳካልሃል! 🗿🔥🤗

መልካም የወንዶች ቀን

||
@ASTU_Network
42🤣6🔥5👍4🥱3❤‍🔥2🤬1🫡1
#Non_Cafe

ወርሃዊው የነን-ካፌ ተጠቃሚ ተማሪዎች ገንዘብ ወደ ተማሪዎቹ አካውንት መግባት ጀምሯል። የገንዘቡ መጠን እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ እንደ ባለፈው 3.8K አይደለም ፤ 3K ብቻ ነው...🤦🏻‍♂💔! አሁን እንደው ምን አለበት ለደንቡ ትንሽ ቢጨምሩ... 🫴🥲😁

|| @ASTU_Network
😁331
Why do men just go about their normal lives and work, not really caring or paying attention, even when it’s their international day🤔

*Me: Because they know every day and every single moment is theirs—not just November 19. 🚬😎🗿
And honestly, even March 8! 🙈🙄
... (just kidding) 😁
.
🤣102🤪2🗿2
አዲስ የትምህርት ደንብ‼️ እስከ 150,000 ብር የሚደርስ ቅጣት እና የባህል ጥበቃ‼️

የትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማትና አካባቢያቸው የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አዲስ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ማውጣቱን አስታወቀ።

ይህ ደንብ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ብቁ ዜጎችን ለመፍጠር ያለመ ነው።

ዋና ዋና ነጥቦች እና ዓላማዎች:
* የትምህርት አዋኪ ድርጊቶችን የሚፈጽሙ ግለሰቦች እና ተቋማት እስከ 150,000 ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተመላክቷል።

ደንቡ እየጨመሩ የመጡትን አዋኪ ጉዳዮች ከመግታት ባሻገር፣ ከኢትዮጵያውያን ወግና ልማድ ጋር ይቃረናሉ ተብለው የተለዩ የውጭ ባህላዊ ልማዶችን በትምህርት ተቋማት አካባቢ መፈጸም ሙሉ በሙሉ ይከለክላል።

ዋንኛው ዓላማ በትምህርት ቤቶችና አካባቢ የሚስተዋሉ አዋኪ ጉዳዮችን በመከላከል፣ ሁለንተናዊ ስብዕናው የተሟላ፣ በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀና ግብረ-ገብነትን የተላበሰ ብቁ ትውልድ እንዲፈጠር ማስቻል ነው።

የተከለከሉ የውጭ ባህላዊ ድርጊቶች ምሳሌዎች:
አዲሱ ደንብ የሀገሪቷን ባህልና ወግ ይቃረናሉ ተብለው በግልጽ የዘረዘራቸውን አሉታዊ መጤ ድርጊቶችንና ክብረ በዓላትን ይከለክላል።

ከእነዚህም መካከል:
* Crazy Day
* Gentle Day
* Olds Day
* Valentine Day
* Color Day
* Pyjama Day የሚሉት ይገኙበታል።

|| @ASTU_Network
🤣35👌9👏5🫡42😢2