ASTU Network ®️
4.18K subscribers
1.45K photos
33 videos
289 files
348 links
🛜 ASTU Network ®️

➲ Join us || @ASTU_Network ||
|| @ASTU_Network_Group ||

📚 Library: @ASTU_Network_Library

👁‍🗨 We are here to keep you updated!

➲ Admin 📩
👤 @NS_Nazu

Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷]

|➲| @ASTU_Network
Download Telegram
ASTU Network ®️
#Academic_Calendar #2018 👉 የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ቢሮ የ2018 የትምህርት ዘመን አካዳሚ ካላንደርን ይፋ ባደረገው መሰረት በአመቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት እንደሚከተለው ቀርበዋል 👇 1. 1st Semester Registration/Readmission [የመጀመሪያ ሴሚስቴር ምዝገባ] ➠ Oct.1 - 2/2025 G.C. (Wednesday - Thursday) ➥…
🔔 Calendar Reminder!

1. First Semester Mid-Exam
[የመጀመሪያ ሴሚስቴር ሚድ ፈተና]


➠ Nov.17-21/2025 G.C.
(Monday - Friday)
➥ ህዳር 8-12/2018 ዓ.ም
(ሰኞ - አርብ)

_  _  _  _  _  _  _  _  _  _  _  _  _  _  _

2. First Semester Class End
[የመጀመሪያ ሴሚስቴር ትምህርት ማብቂያ]


➠ Jan.2/2026 G.C.
(Friday)
➥ ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም
(አርብ)


_  _  _  _  _  _  _  _  _  _  _  _  _  _  _

3. First Semester Final Exam
[የመጀመሪያ ሴሚስቴር ማጠቃለያ ፈተና]


➠ Jan.5-16/2026 G.C.
(Monday - Next Friday)
➥ ታህሳስ 27 - ጥር 8/2018 ዓ.ም
(ሰኞ - ቀጣይ አርብ)


|| @ASTU_Network
5😭5
CoCEA_First_Semester_UG_&_PG_Mid_Exam_schedule_of_2025_26.xlsx
97.2 KB
#SoCEA

Mid-exam schedule for all School of Civil Engineering and Architecture


|| @ASTU_Network
💔4🗿1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#AI 🤖

Coca-Cola 2025 official AI generated holiday ad...

Coca-cola በAI generate ያደረገውን የገና official ማስታዎቂያ ለቀቀ።

ኮካ-ኮላ ከ2024 ጀምሮ official የበአል ሰሞን ማስታወቂያዎችን በvideo generating AI መስራት ጀምሯል።

አምና ተሰርቶ የነበረው ቪድዮ ብዙ አነጋጋሪ ችግሮች የነበሩበት ቢሆንም በዚህ አመት ግን በአንፃራዊነት የተሻለና እውነተኝነትን የተላበሰ እንደሚመስል ብዙዎች መስክረዋል።

ኮካ-ኮላ ይህን ማስታወቂያ Silversideና Secret Level  ከተባሉ ሁለት የAI studios ጋር ጥምረት ፈጥሮ መስራቱን ተዘግቧል።

ከፍተኛ በጀት ተመድቦለት በብዙ ተዋናዮች ፣ ዳይሬክተሮችና ኤዲተሮች በብዙ ልፋት ይሰራ የነበረው ማስታወቂያ አሁን በተወሰኑ ቀናትና በ1 ኮምፒውተር ብቻ መሰራት መቻሉ ወደፊት Artificial intelligence የሰው ልጆችን ስራ የመቀማቱ ነገር የማይቀር መሆኑ ዋና ማሳያ ሆኗል።

ሀሳብ ስጡበት...

©️ bighabesha

||
@ASTU_Network
5👎5😱5😐1
#ጥቆማ

Lab ገብታችሁ ስለሰራችሁት ስራ lab report ለመፃፍ ከተቸገራችሁ ምናልባት ይሄ ዌብሳይት ሊረዳችሁ ይችላል። በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በሚገኙ እና የተለያየ ፊልድ በሚማሩ የኮሌጅ እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተሰሩ የ lap report'ኦች እና ሌሎች ዶክመንቶች የሚገኙበት ዌብሳይት ነው።

የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የ lab report'ኦችም ተካተውበታል።

በተለይ SoEEC ላይ Circuit & Fundamental ላይ የ Lab report ስለሚበዛ የአፃፃፉን sample እና መንገዱን እንድታገኙ ይረዳችኋል።

የምትፈልጉትን የ lab report ርዕስ እዛው ዌብሳይት ላይ search በማድረግ የ lab report'አችሁን እንድትጽፉ የሚረዷችሁን ዶክመንቶች ማግኘት ትችላላችሁ።

🔗 Link:
www.studocu.com


||
@ASTU_Network
👍96🔥1🥰1
One of the biggest myths people have ever said in history is, "If you get into SE or CSE, the courses are easy, you'll have a lot of free time, there are hardly any classes, and you can just chill and learn at your own pace." 😁

Nah, that's completely false. It’s just a myth someone started and it keeps going around. The reality is totally different. Don't be fooled... 😅

✍️ Writing this after ending two classes at 6:00 that started at 2:00.... 👨‍🦯‍➡️💔
.
😭32🤣11👍1😈1
#Notice to all ECE students!

||
@ASTU_Network
1
#ኢትዮጵያ 😰🇪🇹💔

ሁላችንም እንደምናውቀው ሀገራችን ኢትዮጵያ በግጭት እና በጦርነት ውስጥ ያለች ሀገር ናት። ከዚህ በፊት እጅግ ደም አፋሳሽ የሆኑ ውጊያዎችን ከሌላ የውጪ ወገን ጋር ሳይሆን እርስበርስ ተዋግተን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አልቀዋል። በድምሩ በሚሊዮኖች 💔። ሁሌም ትርጉም የሌለው እና ከአለማስተዋል የሚመጣ ውጊያ እየተዋጋን እንገኛለን።

ከዛሬ 5 አመት በፊት የተቀሰቀሰው የሰሜኑ ጦርነት ወንድም በወንድሙ ላይ የከፈተው እና በወንድማማቾች መካከል የተደረገ ውጊያ ሲሆን ለማመን በሚከብድ ሁኔታ እጅግ ደም አፋሳሽ እንደነበር ታሪክ መዝግቦታል። የተጎዱ እና ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን መቁጠር እስከማይቻል ድረስ ከባድ ጊዜ ነበር ያሳለፍነው። ይሄ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው።

ይሄ ሁሉ አልፎ አሁን ትንሽ ለመረጋጋት ሲሞከር ደግሞ አሁንም ባለፈው ጦርነቱን የቀሰቀሰው ሀይል ዳግም ጦርነት ለመጀመር ብዙ ትንኮሳዎችን እየፈጸመ እንደሆነ እየተዘገበ ነው። በዚህ እንደአዲስ እየተፈጸመ ባለው ትንኮሳ ምንም የማያውቁ ፣ አርፈው እርሻቸው ላይ ስራቸውን ሲሰሩ የነበሩ ንጹሃን አርሶአደሮች ተገድለዋል።

ቀጣይ ምን እንደሚፈጠር እና ነገሩ ወዴት እንደሚሄድ አናውቅም። ባለፈው በዚያ ልክ ተሰቃይተን አሁንም ያንን ስህተት መድገም በጣም የሚያሳፍር እና አንገት የሚያስደፋ ነገር ነው።

እናም የዩኒቨርስቲያችን ተማሪዎች ፣ ይህ ችግር የእናት ሀገራችሁ ፣ ስቃዩም የእርሷ ነውና በየሃይማኖታችሁ ወደ ፈጣሪያችሁ ጸልዩ። ጦርነቱ እኔ ያለሁበት ቦታ አይደርስም እኔ መሀል ነኝ አትበሉ። ነገሩ ሲከርር መሃሉም ዳር መሆኑ አይቀርምና።

መቼ ነው ግን ከጦርነት የምንወጣው?😭... ኧረ መረረን እኮ ወገን! 😭... መቼ ነው ሀሳባችንን ወደ እድገት እና ልማት ብቻ የምናዞረው?😭... እስከመቼ ነው እርስበርስ የምንዋጋው የምንጨራረሰው?😭... ለምንድነው መሰልጠን ያቃተን?😭... ምንድነው የሚሻለን?😭... ጭንቅላት የለንም እንዴ?😭... እኛ ቆይ ምንድነን?😭... ምናችንን ነው የሚያመን?😭

ኧረ ፈጣሪ ሆይ አስበን... 🙏😭🇪🇹💔

||
@ASTU_Network
😭386👍5🤪3🤣2😴1👀1💊1
#Department: #MSE #3rdYear

Third year first semester mid-exam schedule


#Tentative

||
@ASTU_Network
2
#Department: #MSE     #4thYear

Fourth year first semester mid-exam schedule


#Tentative

||
@ASTU_Network
#Department: #MSE     #5thYear

Fifth year first semester mid-exam schedule


#Tentative

||
@ASTU_Network
1
#FYI

If you’re a SE or CSE student and want to discuss anything related to your academics or other concerns, you can visit the SE & CSE department head office during the days and hours mentioned above to talk to the dean.

📍 B510, 1st Floor, R7


|| @ASTU_Network
2👎1🙏1
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስርዓተ ትምህርት ክለሳ እየተደረገበት ነው። - ትምህርት ሚኒስቴር


‌‎የሚከለሰው ስርዓተ ትምህርት በ2018 ዓ.ም ዩኒቨርስቲ የገቡ ተማሪዎች የአንደኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።

ስርዓተ ትምህርቱን የመከለስ ሥራ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ተልዕኮ መሰረት ባደረገ መልኩ እየተሠራ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ገልፀዋል።

የቀድሞዎቹ ስርዓተ ትምህርቶች ዘመኑን ያልዋጁና ከዘመኑ ጋር በአግባቡ ያልተቃኙ በመሆናቸው ክለሳው ማስፈለጉን መሪ ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

የሚከለሰው ስርዓተ ትምህርት ምሩቃን ሥራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ትምህርት ፕሮግራሞች ዴስክ ኃላፊ ተስፋዬ ነገዎ ገልፀዋል።‎

እስካሁን በሁለት ዙሮች 55 የትምህርት ፕሮግራሞች ተከልሰዋል የተባለ ሲሆን፤ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ከ80 የሚበልጡ ፕሮግራሞች እንደሚከለሱ ተገልጿል፡፡

©️ tikvahuniversity

|| @ASTU_Network
3
Forwarded from Gibi Vent
Hi everyone 👋

🔖 We are excited to launch our platform 🎭 Gibi Vent, a new and safe space made by students for Ethiopian college/university students!

💡 At Gibi Vent, you can:
✔️ Share your thoughts, feelings or confessions with anonymity
✔️Relate to what other students are going through
✔️ Heal and laugh and connect.

🌐 So whether you had a bad day, a funny thing happened, or something is bothering you, this is your space to free vent and speak your mind.

💫 Let’s build a supportive student community together

⚡️ Start venting, reacting and connecting now!

🤖 Use our bot: @GibiVentBot

💬 Team Gibi Vent
2👎2
Screen Magnifier for your phone! 📱🤗

To enjoy watching football 🏟
For reading 📖
Works without power need
☑️ Magnifies your screen

👉 Condition: New packed! 🤗

DM:
ScreenMag

@Astu_marketplace
4👍2
ተማሪን ነፃነት የምታሳጡ እና የምታስጨንቁ ብሎም ጥቃት ለማድረስ እና ለመዝረፍ የምትሞክሩ ሰዎች ግን ጤነኛ ናችሁ ምናችሁን ነው የሚያማችሁ በቃ ሰብአዊነት የሚባል ነገር የለም ማለት ነው🤔

በዚህ ጉዳይ እንመለስበታለን!
.
😭32👍81🤔1
#ATTENTION‼️

ሰሞኑን አንዳንድ ያልተለመዱ ነገሮች እየተሰሙ ነው። በተለይ ወደ ሴቶች ዶርም አከባቢ። ተማሪዎች ላይ አደጋ ለማድረስ ወይም ጥቃት ለመፈጸም የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ሰዎች እንዳሉ እየሰማን ነው።

እኛ ተማሪዎች ነን። ግቢም ያለነውም በመጀመሪያ ደረጃ ለመማር እና እራሳችንን ለማሳደግ ነው እንጂ ለሌላ ነገር አይደለም።

በእርግጥ ሁለቱም ፆታዎች ጥበቃ እና ደህንነት ያስፈልጋቸዋል። ነገር ግን ሴቶች ደግሞ ከወንዶች የበለጠ ጥበቃ እና ደህንነት ያስፈልጋቸዋል። ቢያንስ ወንዶች በተወሰነ ደረጃ እራሳቸውን መከላከል ይችላሉ። ሴቶች ግን ለጾታዊ ጥቃት ጭምር ሊጋለጡ ይችላሉ። ከቤተሰብ እርቀው ግቢ ሲመጡ በእንደዚህ አይነት ጭካኔ በተሞላበት መንገድ እነሱን ለማጥቃት የሚነሳ ሰው መኖሩ በራሱ በጣም አሳፋሪ ነገር ነው።

በግቢያችን ከሌሎች ግቢዎች የተሻለ ጥበቃ እና ደህንነት ቢኖርም ፣ ነገርግን አንዳንዴ ትንሽ የሚመስሉ ችግሮች ሲፈጠሩ “ያጋጥማል” በሚል ንቆ ማለፍ አደገኛ ነገር ነው። ትንሹ ችግር ነው ነገ አድጎ ትልቅ ነገር የሚያበላሸው የሚያጠፋው።

እዚህ ጋር ሁሉቱም ጾታዎች አደጋ ውስጥ እንደሆኑ መታወቅ አለበት። አሁን እስከ ሴቶች ዶርም ድረስ ሲገባ ነገሩ ትንሽ አነጋጋሪ ሆነ እንጂ ብዙ ጊዜ የወንዶች ዶርም ድረስ እየተገባ እቃ እንደሚዘረፍ ባንዘነጋ ጥሩ ነው።

ግቢያችን ውስጥ ተማሪዎች በፈለጉት ሰዓት እና በየትኛውም ቦታ በነፃነት ቢንቀሳቀሱ መልካም ነው። ያው ብዙ ኃላፊነቶች ስላሉብን ፣ ያሉብን ኃላፊነቶች ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ ነው እንጂ ሌላ ከኢሰብአዊነት በሚመጣ ነገር ምክንያት ተጨማሪ ሸክም በላያችን ላይ ባንጨምር ጥሩ ነው።

ይህንን ጉዳይ ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ አስፈላጊ ቢሆንም ያን ያክል አጥጋቢ መልስ ይገኛል ተብሎ አይታሰብም።

👉 ስለዚህ ምን እናድርግ🤔
በቻላችሁት መጠን እራሳችሁን ጠብቁ። እኛው ነን ለእኛው ያለነው እና እርስበርስ እንጠባበቅ። በተለይ ሴቶች ደግሞ ለሊት ላይ ብቻችሁን ብዙ ባትንቀሳቀሱ ጥሩ ነው። ከተቻለ በጊዜ ዶርም ብትገቡ ይመከራል። ዶርም እንደገባችሁ በር መዝጋታችሁን አረጋግጡ። ያሏችሁን ነገሮች (ስልክ፣ላፕቶፕ፣...) በደንብ ያዙ። ወንዶችም እንዲሁ!

🗣 የመጨረሻ መልዕክት...
እንደዚህ የምታደርጉ ተስፋ የቆረጣችሁ እና እዚህም እዚያም ያላችሁ ሰው አላየኝም ብላችሁ እንደዚህ አይነት ዘግናኝ እና አስጸያፊ ነገር የምታደርጉ ተራ እና ከንቱ ሰዎች ፣ መንግስትን ባትፈሩ ፣ ጥበቃዎችን ባትፈሩ ፣ ማንንም ባትፈሩ ፣ ፈጣሪን ፍሩ ፣ ሰብአዊነትን አስቡ እና ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ። ሀይማኖት አለኝ የሚሉ ሰዎች ናቸው እንዲህ አይነት አሳፋሪ ተግባር የሚፈጽሙት። እንደዚህ አይነት ከንቱ ተግባር በየትኛው እምነት ወይም ሀይማኖት ተቀባይነት የሌለው እርካሽ ተግባር ነው። የዘራችሁትን ዘር ማጨዳችሁ አይቀርምና በዚህ የወጣትነት ዘመን በቻላችሁት መጠን መልካም ዘር ብቻ ዝሩ!

እረፉ! 🤨 አድቡ! በስነስርዓት ኑሩ‼️

||
@ASTU_Network
62👍21❤‍🔥4💯4😭4🤔2🤬1👀1
#TechNews #AI 🤖

Google ጠፈር ላይ AI data center ሊገነባ ነው።

የአሜሪካው ኩባንያ google የArtificial intelegence datacenters በspace /ጠፈር/ ላይ የመገንባት እቅድ እንዳለው ገልጿል።

በ2027 ይሞከራል የተባለውም ይህ ፕሮጀክት power ከሶላር የሚያገኝ ሲሆን ይህም መሬት ላይ ካለው ከቦታ እና የማቀዝቀጫ ውሀ ወጪ ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ነው።

በዚህም google TPU (tensor processing unit) የተሰኙ chips የያዙ 2 ሳተላይቶችን ሊለቅ እንደሆነ ገልጿል።

በተጨማሪ spaxe Xም ዳታ ሴንተሮችን space ላይ የመገንባት ዕቅድ አለው።

||
@ASTU_Network
7🤯4😁1