ASTU Network ®️
4.16K subscribers
1.44K photos
32 videos
288 files
346 links
🛜 ASTU Network ®️

➲ Join us || @ASTU_Network ||
|| @ASTU_Network_Group ||

📚 Library: @ASTU_Network_Library

👁‍🗨 We are here to keep you updated!

➲ Admin 📩
👤 @NS_Nazu

Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷]

|➲| @ASTU_Network
Download Telegram
ከፍተኛ ውጤት የት ተመዘገበ ?

በተፈጥሮ ሳይንስ ከ600 ፦

➡️ 591 ወንድ ተማሪ ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት

➡️ 579 ሴት ተማሪ ከብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት

በማህበራዊ ሳይንስ ፦

➡️ 562 ወንድ ከአምቦ ቦርዲግ ትምህርት ቤት

➡️ 548 ከሴት ከሴንት ጆሴፍ ትምህርት ቤት

|| @ASTU_Network
6👏4🏆1
1 ሺህ 249 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም

በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 1 ሺህ 249 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማጠናቀቂያን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት 50 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል።

|| @ASTU_Network
🙊62🤣1
ASTU Network ®️
Photo
#MoE : 1,249 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ሳያሳልፉ ቀርተዋል።  ከአምናው ጋር ሲነጻጸር 114 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በማሳለፍ መሻሻል ታይቷል።

መቶ በመቶ ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉት 50 ትምህርት ቤቶች ናቸው።

|| @ASTU_Network
1💔1🙉1
ከፍተኛ የተማሪ ቁጥር የት አለፈ ?

" ዘንድሮ 8.4 በመቶ ተማሪ ከ 50 በመቶ በላይ በማስመዝገብ ፈተናውን አልፏል " - ትምህርት ሚኒስቴር

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት እየተገለጸ ይገኛል።

በዘንድሮ አመት ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች ውስጥ 8.4 በመቶ ተማሪ ከ 50 በመቶ በላይ በማስመዝገብ ፈተናውን አልፏል ተብሏል።

ከፍተኛ ተማሪዎችን ያሳለፉ ክልሎች ፦
- አዲስ አበባ፣
- ሐረሪ
- አማራ ክልል ናቸው።

ዘንድሮ " የተፈታኙ ቁጥር ቀንሷል ያለፈው ተማሪ ቁጥር ግን ጨምሯል " ያሉት ትምህርት ሚኒስትሩ ዘንድሮ በአጠቃላይ 48,929 ተማሪዎች ማለፋቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው አመት ያለፈው ተማሪ ቁጥር 36,409 ነበር።

በጾታ ስብጥር
30,451 ወንድ ተማሪዎች አልፈዋል።
18,478 ሴት ተማሪ አልፏል።

በተፈጥሮ ሳይንስ ከፍተኛ ውጤት

ወንድ 591/600 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
ሴት 579/600 ብስራተ ገብርኤል ትምህርት ቤት

በማህበራዊ ሳይንስ
ወንድ 562/600 አምቦ አምቦ ቦርዲንግ ስኩል።
548 /600 ሴንት ጆሴፍ ትምህርት ቤት።

አማካይ ውጤት
87 በመቶ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች
86 በመቶ ዓለማቀፍ ትምህርት ቤቶች
5.4 በመቶ የመንግስት ትምህርት ቤቶች
51 በመቶ የግል ትምህርት ቤት ውጤት

|| @ASTU_Network
2🫡1
በኦንላይን የተፈተኑ ተማሪዎች የተሻለ የማለፍ ምጣኔ አስመዝግበዋል

በኦንላይን ከተፈተኑት 134 ሺህ 609 ተማሪዎች መካከል 29 ሺህ 239 ተማሪዎች አልፈዋል።

ይህም በወረቀት ከተፈተኑት ጋር ሲነጻጸር በጣም የተሻለ ነው።

|| @ASTU_Network
😁9👀21
ከ500 በላይ ያገኙ ተማሪዎች

👉 ከአዲስ አበባ: 888
👉 ከኦሮሚያ: 794
👉 ከአማራ: 385

|| @ASTU_Network
🔥3
በዘንድሮ ዓመት ሬሜዲያል /የአቅም ማሻሻያ/ ፕሮግራም እንደሚኖር የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።

ካለፈው አመት ግን መግቢያው ከፍ እንደሚደረግ እና የሚገባው ተማሪ ቁጥርም ቅናሽ እንደሚኖረው ተገልጿል።

|| @ASTU_Network
🤗1
ዘንድሮ የሬሜዲያል /አቅም ማሻሻያ/ ፕሮግራም ይኖራል ?

በዘንድሮ ዓመት ሬሜዲያል /የአቅም ማሻሻያ/ ፕሮግራም እንደሚኖር የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል።

" ከባለፈው ዓመት መግቢያውን ከፍ በማድረግ ሬሚዳል ይሰጣል " ነው ያሉት።

ምን ያህል ተማሪዎች ሬሜዲያል ይገባሉ ? ለሚለው ጥያቄ ሚኒስትሩ " አልወሰንም " ሲሉ መልሰዋል።

" ዘንድሮ ሪሚዲያል እድል የሚሰጣቸውን ተማሪዎች ቁጥር አልተወሰነም። 40-50 በመቶ መካከል ይሁን የሚለው ላይ በውይይት ላይ ነው " ብለዋል።

ካለፈው አመት ግን መግቢያው ከፍ እንደሚደረግ እና የሚገባው ተማሪ ቁጥርም ቅናሽ እንደሚኖረው ተገልጿል።

|| @ASTU_Network
1
ከ500 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፦

አጠቃላይ- 2384
በተፈጥሮ ሳይንስ፦ 2215
በማኅበራዊ ሳይንስ፦ 169

በክልል ደረጃ ከ500 በላይ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች፦
አዲስ አበባ- 888
ኦሮሚያ- 794
አማራ- 385

|| @ASTU_Network
👌3
ከ50 በመቶ በላይ ውጤት አምጥተው ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች በደረጃ፦

- አዳሪ ትምህርት ቤቶች 87.1%
- ዓለም አቀፍ ኮሚዩኒቲ ት/ቤቶች 86.6%
- የግል ትምህርት ቤቶች 51.6%
- የመንግሥት መደበኛ ትምህርት ቤቶች 5.6%

በሌላ በኩል 1,249 ትምህርት ቤቶች ዘንድሮ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ገልፀዋል።

ይህም ከአምናው ጋር ሲነጻጸር 114 ተጨማሪ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በማሳለፍ መሻሻል ታይቷል።

መቶ በመቶ ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉ 50 ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸው።

|| @ASTU_Network
🕊2
ውጤት መቼ ይለቀቃል ?

" ውጤት እስከ ነገ 6:00 ሰዓት ይለቀቃል " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

|| @ASTU_Network
🤬1
እስከ ነገ ቀን 6:00 ሰዓት ውጤት ይለቀቃል።

" ምንም የተሳሳተ ነገር እንዳይኖርና እርግጠኛ ለመሆን ስለፈለግን የተወሰኑ ልጆች አሉ የተዛባ እሱን አስተካክለን እስከ ነገ ቀን 6:00 ሰዓት የፈተናው ውጤት ይለቀቃል። " - የትምህርት ሚኒስትር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

|| @ASTU_Network
🕊2
በ12ኛ ክፍል ፈተና 50 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን አሳልፈዋል

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ውጤትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ 50 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳለፍ እንደቻሉ አመልክተዋል።

ፈተናውን 134 ሺህ 609 ተማሪዎች በኦንላይን መውሰዳቸውን አስታውሰው÷ ከእነዚህ መካከል 29 ሺህ 233 ተማሪዎች ማለፍ እንደቻሉ ጠቁመዋል።

|| @ASTU_Network
1😢1
" ስንጠብቅ ያነበረው ይህንን ውጤት ነው " - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ2017 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑት 585,879 ተማሪዎች መካከል 48,929 ተማሪዎች 50 በመቶ አምጥተው አልፈዋል። ይህም 8.4 በመቶ ነው።

በ2016 ዓ/ም ከ674,823 ተማሪዎች ያለፉት 36,409 ወይም 5.4 በመቶ ነበሩ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በ2017 ዓ/ም ተማሪዎች ስላስመዘገቡት ውጤት ምን አሉ?

" ስንጠብቅ ያነበረው ይህንን ውጤት ነው።

የመጀመሪያ ሾክ ነበር ከዛ ግን በራሱ ውጤት የሚያልፍ ተማሪ እየመጣ ነው።

የፈተና ስርአታችን ሊያመጣው የሚፈልገው ውጤት እየመጣ ነው ትክክለኛው መስመር መሆኑን የተረዳንበት ነው።

ይህንን ሃገር የሚጠበቅበት ቦታ ለማድረስ ለእዛ የሚበቃ ትውልድ እያፈራን ነው።

በእዚሁ እንዲቀጥል ነው የምንሰራው።

15-20 በመቶ የሚሆን ማክሲመም ተማሪ እንዲያልፍ ነው የምንሰራው ሁለት እና ሦስት አመት ይፈጅብናል ነገር ግን እንደርስበታለን።

ዘንድሮም ጥሩ ውጤት ነው የመጣው ነው ነገር ግን የሚያኩራራ አይደለም በሚቀጥሉት ሦስት አመታት የተሻለ ውጤት ይመጣል " ብለዋል።

|| @ASTU_Network
🤷‍♀21