ASTU Network ®️
4.16K subscribers
1.44K photos
32 videos
288 files
346 links
🛜 ASTU Network ®️

➲ Join us || @ASTU_Network ||
|| @ASTU_Network_Group ||

📚 Library: @ASTU_Network_Library

👁‍🗨 We are here to keep you updated!

➲ Admin 📩
👤 @NS_Nazu

Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷]

|➲| @ASTU_Network
Download Telegram
#ዜና

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠበቅባቸውን መሥፈርቶች ካላሟሉ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ይደረጋሉ — ትምህርት ሚንስቴር

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚጠበቅባቸውን መሥፈርቶች ማሟላት ካልቻሉ ሰፋ ያለ ሁለተኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚደረጉበት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል የትምህርት ሚንስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ አስታወቁ፡፡

ሚንስትሩ ይህን የተናገሩት ነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በዳግም ምዝገባ አፈጻጸም ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና የትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን በጋራ ባዘጋጁት የውይይት መድረክ ላይ ነው።

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በወቅቱ ለትምህርት ጥራት ከፍተኛ ቦታ እየሰጡ መሄድ ያስፈልጋል በሚል ከግል ተቋማት ጋር ከአራት ዓመታት ጀምሮ እየተሠራ እንደሆነ፣ ዳግም ምዝገባን በተመለከተም ባለፉት ሦስት ዓመታት ስለመሥፈርቱ የማሳወቅ ሥራ ሲከናወንና የማያሟሉ በዘርፉ መቀጠል እንደማይችሉ ሲገለጽ መቆየቱን አንስተዋል።

አያይዘውም መሰል ግምገማ በመንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይም እንደሚደረግ ጠቅሰው በዚሁ አሠራር መሠረት ይዘጋሉ ብለው የሚታሰቡት የግሎቹ ብቻ ሳይሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች ጭምር መሆናቸውን ጠቁመዋል።

|| @ASTU_Network
🤣294😁1
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲሄዱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ይዘው እንዲሄዱ ገቢዎች ሚኒስቴር አሳሰበ።

የገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት ክፍያ ለመሰብሰብ እያንዳንዱ የወጪ መጋራት ተጠቃሚ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማውጣት እንዳለበት አስታውሷል።

ሚኒስቴሩ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ የፋይዳ ቁጥር በመያዝ በአካባቢያቸው በሚገኝ ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት (ገቢዎች) ወይም ቢሮ በመቅረብ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እንዲያወጡ ማሳሰቡን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሚኒስቴሩ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲ በሚገቡበት ወቅት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ይዘው እንዲቀርቡ አስገንዝቧል።

©️ tikvahethiopia

||
@ASTU_Network
🤣24🤷‍♀43🤨2🤔1😭1
ASTU Network ®️
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲሄዱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ይዘው እንዲሄዱ ገቢዎች ሚኒስቴር አሳሰበ። የገቢዎች ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ወጪ መጋራት ክፍያ ለመሰብሰብ እያንዳንዱ የወጪ መጋራት ተጠቃሚ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማውጣት እንዳለበት አስታውሷል። ሚኒስቴሩ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) አዲስ እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ የፋይዳ…
#TIN (Taxpayer Identification Number) — የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር

◽️ የዚህ ነገር አጠቃላይ ሀሳቡ ምንድነው

👉 የወደፊት የግብር ስርዓት:

▬ ተማሪዎች ይማራሉ ፣ ይመረቃሉ ፣ ስራ ይይዛሉ ከዚያም ገንዘብ ያገኛሉ። TIN ሲኖራቸው ወደፊት የሚያገኙትን ገቢ በቀላሉ በማግኘት ግብር የመሰብሰብ ስራን ቀላል ያደርጋል።

👉 የፋይናንስ መለያ(ID):
▬ TIN በሀገሪቱ የፋይናንስ ስርዓት ውስጥ ልክ እንደ መለያ ቁጥር ያገለግላል። ይህም የባንክ አካውንት ሲከፈት ፣ ነፃ የትምህርት እድል ሲገኝ እንዲሁም ከመንግሥት ጋር የተገናኙ ስራዎችን በሀገሪቱ የመረጃ ቋት ለማደራጀት ያግዛል።

👉 ምዝገባ እና ቁጥጥር:
▬ መንግስት የዜጎችን (ተማሪዎችን ጨምሮ) አጠቃላይ መረጃ መያዝ ይፈልጋል። ይሄም ምን ያክል ተመራቂዎች ፣ ሰራተኞች እና እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች እንዳሉት ለማወቅ ይረዳዋል።

#ማጠቃለያ
👉 ተማሪዎች አሁን TIN ያስፈልጋቸዋል ማለት አሁን ግብር ይከፍላሉ ማለት አይደለም። ይልቁንስ መንግስት የዜጎቹን (የተማሪዎችን ጨምሮ) መረጃ ለመሰብሰብ ፣ ለመመዝገብ ፣ ለመለየት እና ለወደፊቱ አጠናቅሮ ለማዘጋጀት የሚጠቀመው መንገድ ነው።
👉 ኢትዮጵያ የተማሪዎች የወጪ መጋራትን (Cost Sharing) መልሰው የሚከፍሉበትን "Student loan system" እየተገበረች መሆኑን ማሳያ ነው።
👉 TIN ማውጣት ያስፈለገው የዩኒቨርስቲ ቆይታን የወጪ መጋራት (Cost Sharing) ልክ ግብር በ TIN እንደሚከፈለው ስለሚከፈል ነው።
👉 ተማሪዎች ተምረው ፣ ተመርቀው ፣ ስራ ይዘው ገንዘብ ማግኘት ሲጀምሩ መንግስት የ TIN ቁጥርን በመጠቀም የወጪ መጋራት (Cost Sharing) ክፍያን እና ግብርን በቀላሉ እንዲሰበስብ ይረዳዋል።

|| @ASTU_Network
7👍5😭2🤷‍♀1
The letter ‛h’ in the word “University” stands for happiness... 😁

React only if you get it... 😂😭
.
🤣34😭4💔3
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔥2
#AASTU

አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአራት የአፕላይድ ሳይንስ የትምህርት ፕሮግራሞች ዓለም አቀፍ ዕውቅና አጊኝቷል።

ዩኒቨርሲቲው በባዮ-ቴክኖሎጂ፣ በምግብ ሳይንስና አመጋግብ ስርዓት፣ በኬሚካል ኢንዱስትሪ እንዲሁም በጅኦሎጂ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቱን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ደረጃ እንግዳ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ዕውቅናው (Accreditation) በትምህርት መስኮቹ የተመረቁ ተማሪዎች 'ያለምንም' መመዘኛ በውጭ ሀገራት ሥራ እንዲያገኙ የሚያስችል መሆኑን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ዕውቅና የተገኘባቸውን የትምህርት ፕሮግራሞች ለውጭ ሀገራት ተማሪዎች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፤ ዕውቅናው እ.አ.አ ከ2023 ዓ.ም ጀምሮ የተመረቁትን እንደሚያጠቃልል አስረድተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኘው Accreditation Board of Engineering and Technology (ABET) ተቋም ነው ዕውቅናውን ያገኘው፡፡

©️ tikvahuniversity

|| @ASTU_Network
9😱5👏4🔥2
Hmm... 🤔😕

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 የትምህርት ዘመንን አካዳሚክ ካላንደር ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። በዚህም መሰረት የሁሉም የቅድመ እና የድህረ ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡት ከመስከረም 05-10 ባለው ጊዜ ውስጥ ነው።

ዩኒቨርስቲያችን ASTU ባወጣው አካዳሚክ ካላንደር መሰረት ደግሞ ወደ ዩኒቨርስቲ የምንገባው መስከረም 21 ነው።

አሁን ላይ የተለያዩ የዩኒቨርስቲ ጥሪ ማስታወቂያዎችን ስንመለከት ዩኒቨርስቲዎች በብዛት በትምህርት ሚኒስቴር ካላንደር መሰረት እየጠሩ ይገኛሉ።

ከዚህ በፊት በዩኒቨርስቲያችን በተለመደው አሰራር አንዴ አካዳሚክ ካላንደር ከወጣ በኋላ revise ይደረጋል። ነገርግን ለ2018 ተብሎ የወጣው አካዳሚክ ካላንደር እስካሁን revise አልተደረገም።

ስለዚህ በቀጣይ ሶስት ነገር ሊሆን ይችላል:-
1. ምናልባት ዩኒቨርስቲያችን ካላንደሩን revise አድርጎ በትምህርት ሚኒስቴር ካላንደር መሰረት ሊያደርገው ይችላል።
2. ካላንደሩ revise ተደርጎ ወደ ዩኒቨርስቲ የምንገባበት ቀን ተለውጦ ነገርግን በትምህርት ሚኒሰቴር ካላንደር መሰረት ያልሆነ ሊሆን ይችላል።
3. ዩኒቨርስቲው ምንም ካላንደሩን revise ሳያደርግ አንዴ ባወጣው ካላንደር መሰረት ሊቀጥል ይችላል።

በዚህ ጉዳይ ከዩኒቨርስቲው የተባለ ነገር ወይም የወጣ መረጃ የሌለ ሲሆን ፣ አዲስ ነገር ካለ ለማሳወቅ እንሞክራለን። እናንተም አዲስ ነገር ከሰማችሁ በግሩፓችን ላይ አሳውቁን።

እናመሰግናለን! 🙏

||
@ASTU_Network
👍234🤷‍♀3👀2
#AASTU

የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያለምንም ሌላ መመዘኛ በያዙት ድግሪ ውጭ ሀገር ስራ ሊያገኙ ነው ተባለ


ተማሪዎች ያላቸውን ድግሪ ተጠቅመው ያለምንም ሌላ መመዘኛ የውጭ ሀገር ስራ እንዲያገኙ ለማድረግ ዕውቅና ማግኘቱን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ።

እውቀናውን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ደረጃ እንግዳ (ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው በአፕላይድ2 ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ ማለትም በባይዮ ቴክኖሎጂ፣ በምግብ ሳይንስና በአመጋግብ ስረዓት፤ በኬሚካል ኢንዱስትሪና በጅኦሎጂ ዓለም አቀፍ ዕውቅና አግኝቷል ብለዋል።

አክለውም ዩኒቨርሲቲው ያገኘው ዕውቅና በተለያዩ መርሃግብሮች የተመረቁ ተማሪዎች ያለምንምን መመዘኛ በውጭ ሀገራት ስራ እንዲያገኙ ያደርጋል ሲሉ ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም ተማሪዎች የተመረቁበትን ድግሪ ይዘው በውጭ ሀገር ስራ መቀጠር አይችሉም ነበር ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በሚቀጠሩበት ሀገር መመዘኛ መፈተን ግዴታ ነበር አሁን የተገኘው ዕውቅና ግን በድግሪያቸው ቀጥታ ስራ እንዲቀጠሩ የሚያደርግ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

አያይዘውም ዓለም አቀፍ ዕውቅና የተገኘባቸውን የትምህርት ፕሮግራሞች ለውጭ ተማሪዎች ለመስጠት እየተሰራ ነው ያሉ ሲሆን የውጭ ተማሪዎች መማራቸውም ለዩኒቨርሲቲው ተጨማሪ ገቢ ያስገኛል ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ዕውቅናው ከጎርጎሮሳውያኑ 2023 ጀምሮ የተመረቁትን እንዳሚያጠቃልል ገልጸው በኢንጀሪንግ ትምህርት ዘጠኝ የትምህርት ፕሮግራሞች ዓለም አቀፍ እውቅና በቀጣይ ህዳር ወር ያገኛሉ ማለታቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው።

|| @ASTU_Network
😁43😭2🤬1🙉1
From: ASTU Students

To: The Administrators and Leadership of Adama Science and Technology University

Subject: Request for Improved Transparency and Responsiveness


Dear Esteemed Administrators and Leaders,


First and foremost, we would like to extend our warm greetings and appreciation.

As you know, ASTU is one of the two science and technology universities in Ethiopia. Over the years, it has played a vital role in educating and graduating students in applied and engineering fields, thereby producing skilled science and technology professionals for our country. We are proud to be part of this remarkable institution and its forward-looking vision.

Among the 12 principles of ethical service that guide our university, “Transparency” and “Responsiveness” are particularly important. We strongly believe that upholding all these principles, especially in communication and information-sharing, is essential for ASTU to excel as a leading science and technology university.

Unfortunately, we students are facing challenges in accessing timely and reliable information. Despite the presence of the university’s official website and telegram channel, we often struggle to obtain accurate updates. Five specific issues illustrate this concern:

1. Academic Calendar
The academic calendar is not published on the official website, leaving students uncertain and dependent on unofficial sources such as random groups. This creates confusion and affects our ability to plan and manage our studies effectively. We respectfully request that the academic calendar for the upcoming year be made available through official channels as soon as possible.

2. Cutoff Points
For most schools and departments, cutoff points are not officially announced. As a result, students rely on speculation rather than accurate data. Publicly sharing cutoff points is essential not only for current students but also for incoming batches who need clarity when selecting their desired schools or departments. We have observed that other universities provide detailed information, allow re-checking, and enable students to make informed choices—practices that we believe would greatly benefit ASTU as well.

3. Class Schedules
Although class schedules are posted on notice boards, students often struggle to keep up with the latest updates. There are more efficient ways to share this information. If an official website or channel were dedicated to posting class schedules for all students, it would allow timely access, reduce confusion, and save unnecessary effort and time.

4. Updates and Clarifications
The Ministry of Education often announces changes such as entry dates or department restructuring. However, students at ASTU are frequently left uncertain about whether these changes will take effect at our university or how they will be applied. Clear and timely communication from the university would reduce confusion, build students’ confidence, and ensure smoother academic planning and decision-making.

5. Curriculum Updates
There are rumors that the university may revise its curriculum to align with international standards. Students are unsure if these changes will affect current or future courses. Providing official clarification would eliminate uncertainty, strengthen trust, and help students plan their studies more effectively.


Furthermore, when we seek clarification directly from offices, we often face unresponsiveness or, at times, are treated disrespectfully. This discourages us and leaves us without the answers we need. Such experiences undermine the principle of responsiveness and create unnecessary frustration.

We sincerely request that these issues be given due consideration. Ensuring transparency in information-sharing and responsiveness in student services will strengthen ASTU’s reputation, enhance student trust, and help the university achieve its vision.

Thank you for your attention to this matter. We remain proud of our university and hopeful that with your leadership, these concerns will be addressed promptly.

Respectfully,
ASTU Students

||
@ASTU_Network
37👍15👏8😁3👌3🙏2🔥1
ASTU Network ®️
From: ASTU Students To: The Administrators and Leadership of Adama Science and Technology University Subject: Request for Improved Transparency and Responsiveness Dear Esteemed Administrators and Leaders, First and foremost, we would like to extend our…
#MAGA 🥲

If all these problems are properly resolved and addressed, the old meaning of MAGA will no longer apply.

MAGA = Make America Great Again
🗽

Instead, it will stand for the new MAGA:

MAGA = Make ASTU Great Again
🎓☑️
... 😁
.
🤣25👌5🫡43😭1🆒1
አንድ ዜና ተሰማ 👇... 🌍🎓

የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ያለምንም ሌላ መመዘኛ በያዙት ድግሪ ውጭ ሀገር ስራ ሊያገኙ ነው ተባለ


የ ASTU ተማሪዎች ምን አሉ

👥: በሌላው ጊዜ "ASTU ይበልጣል... "ASTU ቀዳሚ ነው... ASTUን ሚደርስበት የለም" ሲሉ የነበሩ 👇
🗣 ምን አለበት ያኔ AASTU ብገባ ... ወይኔ እኔ!... ወይኔ በላቸው! 🫩😁

👥: ቀለሜያንሱ 🧠🥸... 👇
🗣 ASTU reform ያስፈልገዋል ከላይ እስከ ታች 😤

👥: ASTUም international degree በቅርቡ መስጠት ይጀምራል ያሉ ተስፈኞች 👇
🗣 ለእኛም ቀን አለ 🤧

👥: አንዳንዶች 👇
🗣 እንዲህ ስትናገሩ አሁን ድግሪውን በትክክል አውቃችሁ ተምራችሁ አሜሪካ ሀገር የምትቀጠሩበት አይመስልም? 😁

👥: ሌሎች 👇
🗣 በ International degree ስራ አጥ መሆንንስ ማን አየበት... 😂
.
🤣202
ASTU Network ®️
Hmm... 🤔😕 የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 የትምህርት ዘመንን አካዳሚክ ካላንደር ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው። በዚህም መሰረት የሁሉም የቅድመ እና የድህረ ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡት ከመስከረም 05-10 ባለው ጊዜ ውስጥ ነው። ዩኒቨርስቲያችን ASTU ባወጣው አካዳሚክ ካላንደር መሰረት ደግሞ ወደ ዩኒቨርስቲ የምንገባው መስከረም 21 ነው። አሁን ላይ የተለያዩ…
#Update

ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ማለት በሚቻል ደረጃ ከመስከረም 04-10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት ለተማሪዎቻቸው ጥሪ እያደረጉ ነው።

ይህን ለየት የሚያደርገው ደግሞ የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲም ጭምር የተማሪዎች መግቢያ ከመስከረም 08-09/2018 ዓ.ም እንደሆነ አስታውቋል።

ይህንን ሁሉ ስንመለከት ASTUም ቀድሞ ያወጣውን ካላንደር revise አድርጎ በተመሳሳይ ጊዜ (ከመስከረም 05-10/2018 ዓ.ም) ባለው ጊዜ ውስጥ ሊጠራ ይችላል የሚለው ጥርጣሬያችን ከፍ እንዲል አድርጓል።

ሆኖም ግን ከዩኒቨርስቲው የወጣ ይፋዊ ማስታወቂያም ሆነ መረጃ የለም። ለማንኛውም አሁን ላይ ዩኒቨርስቲዎች እየጠሩ ባሉበት ቀናት ልንጠራ የምንችልበት እድል ሰፊ ስለሆነ ቀድሞ መዘጋጀቱ አይከፋም።

አዲስ ነገር ካለ ለማሳወቅ እንሞክራለን። እናንተም አዲስ ነገር ከሰማችሁ በግሩፓችን ላይ አሳውቁን።

|| @ASTU_Network
😭4510👀4😁3🤷‍♀1🤔1🤬1💔1
የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ተጠናቀቀ!

🇪🇬 ግብፅ 2—0 ኢትዮጵያ 🇪🇹


የኢትዮዽያ ብሄራዊ ቡድን በግብፅ አቻው ተሸንፏል። በረኛችን ግን ክብር ይገባዋል! 👏👏

እኛስ ግድቡ አለን!

ሲጀመር ዝምብሎ መራገጥ ምን ያደርጋል ፣ ዋናው ውሃ መያዝ እና ሃይል ማመንጨት ነው! 😉😭

#IT_IS_MY_DAM! 🇪🇹😂
.
😁14😭94💔1🗿1
ASTU Network ®️
"ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዘው እንዳይሄዱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል" - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) || @ASTU_Network
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተማሪዎች ሞባይል ስልክ፣ ታብሌት እና መሰል ኤሌክትሮኒክስ ቁሶችን ይዘው ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሔዱ ከልክሏል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን አጀማመር ላይ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጋር የበይነ-መረብ ምክክር አድርጓል።

የ2018 ትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ሰኞ መስከረም 05/2018 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጿል።

ተማሪዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ታብሌት እና መሰል ኤሌክትሮኒክስ ቁሶችን ይዘው በትምህርት ቤት መገኘት ክልክል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

በሌላ በኩል፤ ባለፈው ዓመት ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎችን ጨምሮ ሁሉም ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት እና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ ወላጆች፣ መምህራን እና የዘርፉ ባለድርሻዎች የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ተጠይቋል።

|| @ASTU_Network
🙉6👌53
#GERD 🇪🇹

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ!

የሀገር ኩራት!

#GERD 🇪🇹
#Ethiopia 🇪🇹
.
🔥12🥰5❤‍🔥2🎉2