ASTU Network ®️
4.16K subscribers
1.43K photos
32 videos
287 files
346 links
🛜 ASTU Network ®️

➲ Join us || @ASTU_Network ||
|| @ASTU_Network_Group ||

📚 Library: @ASTU_Network_Library

👁‍🗨 We are here to keep you updated!

➲ Admin 📩
👤 @NS_Nazu

Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷]

|➲| @ASTU_Network
Download Telegram
" ዩኒቨርሲቲዎች ስለተማሪዎቻቸውና ስለሚሠሩት ሥራ ትክክለኛ መረጃ ስጡን ብለን ከጠየቅን ሦስት ዓመት አልፎናል፡፡ ሆኖም እስካሁን የተሟላ መረጃ ለማግኘት ችግር ሆኖብናል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ዘንድ እውነተኛ መረጃ መስጠት አልተለመደም፡፡

ባለፈው ዓመት ከተማሪዎች ምገባ ጋር ተያይዞ የውሸት ሪፖርት ሲቀርብ ነበር፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪ ቁጥር በውሸት በመጨመር በጀት እንዲጨመርላቸው ያደርጉ ነበር።

ዩኒቨርሲቲዎች አሉን የሚሏቸውን የተማሪዎች መረጃ ከእነፎቷቸው አምጡ ስንል ግን፣ አሉን ብለው ካስመዘገቧቸው ተማሪዎች 251 ሺህ ያህሉ የት እንደገቡ አያውቁም፥ ለማምጣትም አልቻሉም፡፡

አንድ ዕውቀት ላይ እሠራለሁ የሚል ተቋም በዚህ ደረጃ ላይ የሚገኝ ከሆነና እውነተኛ መረጃ መስጠት የማይፈልግ ከሆነ፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንዲመጣ የምንፈልገውን ለውጥ አዝጋሚ ያደርገዋል። "
- የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የዩኒቨርሲቲዎች መረጃ አሰጣጥን በተመለከተ የተናገሩት፦

©️ @tikvahuniversity

|| @ASTU_Network
👏6🤷‍♀3👍32
#MoE

በኃላፊነት ላይ ያለ የመንግስት ሹመኛ ወይም ተመራጭ ለ #ክብር_ዶክትሬት እንዳይታጭ የሚከለክል መመሪያ የትምህርት ሚኒስቴር አወጣ፡፡

መመሪያው 8 ዙር ተማሪዎችን ያላስመረቁ እና ሶስተኛ ዲግሪ ወይም (PhD) የማያስተምሩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጡ ይከለክላል፡፡

በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ሃምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈርሞ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የተመራው ይህ መመሪያ በቅርብ ጊዜ የተመሰረቱ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት እንዳይሰጡ ይከለክላል፡፡

በመመሪያው ክፍል ሁለት ላይ የክብር ዶክትሬት የሚሰጡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መስፈርትን በተመለከተ የተቀመጠው ድንጋጌ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ለመስጠት ቢያንስ ከ8 ጊዜ በላይ ተማሪዎችን ያስመረቁ እና የሶስተኛ ዲግሪ የሚሰጡ መሆን እንዳለባቸው ያስገድዳል፡፡

በዚህም መሰረት ሰላሌ፣ ደምቢ ዶሎ፣ መቅደላ አምባ፣ ራያ፣ ደባርቅ እና መሰል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስምንት ዙር ተማሪዎችን ስላላስመረቁ በመመሪያው መሰረት የክብር ዶክትሬት መሰጠት አይችሉም፡፡

በዚሁ ክፍል ስር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የክብር ዶክትሬት ማዕረግ ለመስጠት አገር እና አለም አቀፍ መስፈርቶችን ማሟላት እንዳለባቸው ሰፍሯል፡፡

በሞያ መስኩ የተለየ ስራ ያበረከተ ከሆነ ኢትዮጵያዊም ሆነ ሌላ ዜጋ የክብር ዶክትሬት ማዓረግ ማግኘት እንደሚችል የዘረዘረው መመሪያው መስፍርቱን ካሟሉ ለግለሰብም ይሁን ለቡድን መስጠት እንደሚቻል አመላክቷል፡፡

በሕይወት ላለም ይሁን ለሌለ ሰው ማዕረጉን መስጠት እንደሚቻል የሚፈቅደው ይህ መመሪያው የክብር ዶክትሬት ለማግኘት የማይቻልባቸውን ገደቦችም በክፍል ሁለት አንቀጽ 10 ስር ዘርዝሯል፡፡

በዚህም መሰረት የከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ የሙሉ ሰዓት ተቀጣሪ ሰራተኛ፣ የሴኔት አባላት ወይም የአስተዳደር አካላት ከተቋሙ ጋር ያላቸው ቀጥተኛ ግንኙነት እስካላበቃ ድረስ ለክብር ዶክትሬት መታጨት እንደማይችሉ ደንግጓል፡፡

መመሪያው በስራ ላይ ያሉ የመንግስት ሹሞች ወይም ባለስልጣናት ለክብር ዶክትሬት እንዳይታጩም የሚከለክል ነው፡፡

የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ግለሰብ ዶክተር፣ የክብር ዶክተር እና መሰል መጠሪያዎችን ከሰጪው ተቋም ውጪ በየትኛውም ድርጅት ውስጥ መጠቀም እንደማይችሉም ደንግጓል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በለፈው ዓመት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሽምያ የሚሰጡ የክብር ዶክትሬት ማዕረጎች መመሪያ እስኪወጣ ድረስ እንዲያቆሙ ማዘዙ ይታወሳል፡፡

መረጃው የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
3🤷‍♀1
#MoE

የመውጫ ፈተና መሰጠት ከተጀመረ ወዲህ ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ፥ የዲግሪ ህትመት የሚዘጋጀው የመውጫ ፈተናውን ላለፉ ተማሪዎች ብቻ እንደሆነ ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ የዲግሪ ህትመትን የተመለከተና በሚኒስትር ዲኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ነሐሴ 06/2017 ዓ.ም የተፈረመ ደብዳቤ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልኳል፡፡ 

በዚህም የዲግሪ ማስረጃ ወይም ሰርተፊኬት ህትመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በማዕከል የሚታተም መሆኑን መጋቢት 02/2017 ዓ.ም ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ደብዳቤ ማሳወቁን አስታውሷል፡፡  ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተመረቁ እና ከዚህ በፊት ተመርቀው መረጃውን ያልወሰዱ ከተመረቁ ጊዜ ጀምሮ ህትመቱ በማዕከል ተከናውኖ በዩኒቨርሲቲው ወይም በተቋሙ በኩል የሚሠራ ወይም የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል፡፡

በመሆኑም ከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ ሊሠራለት የሚገባውን የሰርተፍኬት ይዘት (በውስጡ የሚገለፁ ይዘቶችን፣ ሎጎዎች እና ተጨማሪ መብት ያላቸው ጉዳዮች) በማካተት እጅግ ቢዘገይ እስከ ሐሙስ ነሐሴ 08/2017 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ እንዲያሳውቁ አሳስቧል፡፡

የመውጫ ፈተና መሰጠት ከተጀመረ ወዲህ ያለው ህትመት የሚዘጋጀው፣ የመውጫ ፈተናውን ላለፉ ተማሪዎች ብቻ መሆኑን ጠቁሟል፡፡

(ከትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ያገኘነው ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል፡፡)

©️ tikvahuniversity

|| @ASTU_Network
2🗿2
ASTU Network ®️
#AI 🤖 📌 Complete List of AI Tools for Every Task (2025 Edition) 💡 Stay ahead with these powerful tools for content creation, productivity, and more: ✍️ Write Texts – ChatGPT 🤖 🎬 Make Videos – Veo 3 🖼️ Create Images – Freepik 🖌️ 📽️ Create Slides – Gamma…
#AI 🤖

Best AI Tools You Have to Know


1. ChatGPT.com → Solve anything
2. LightPDF.com → Chat with files
3. Tome.app → Build presentations
4. Pika.art → Create videos
5. Gamma.app → Design docs
6. Suno.ai → Make music
7. PicWish.com → Image editing
8. Perplexity.ai → Research assistant
9. Krea.ai → Logo design
10. Fliki.ai → Voiceovers
11. Runway.ml → Film editing
12. Relume.io → Web design
13. Descript.com → Edit audio
14. ElevenLabs.io → Clone voices

Join us 👇

|| @ASTU_Network
🙏21🤔1
#Telegram12thAnniversary

❝Telegram turns 12 today!❞
Pavel Durov, Founder and CEO of Telegram
.
4👎4🏆2😱1
#ለመረጃ_ያክል... #AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጡትን የቅድመ-ምረቃ እና የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች በግላቸው ከፍለው የሚማሩ ተማሪዎች የሚከፍሉት ክፍያ በECTS ይህንን ይመስላል!

|| @ASTU_Network
3🤷‍♀1😨1
DO NOT MISS THIS CHANCE!     የLinkedIn አካውንቶ ገንዘብ መስራት እንደሚችልያውቃሉ።

ክፍያዎትን ባንክ ሆነ በባይናንስ መቀበል ይችላሉ።

እኛ ጋር ሲመጡ

  •100-299 connections: $7 በየሳምንቱ
  • 300-499 connections: $12 በየሳምንቱ
  • 500-999 connections: $14 በየሳምንቱ
  • 1000-1999 connections: $19 በየሳምንቱ
  • 2000+ connections: $24 በየሳምንቱ

super deal for only 3 first comers 💯💯💯.

50+ $7
100+ $8
300+ $15
500+ $20
1000+ $25
2000+ $30

🚨 አካውንቱ ከአንድ አመት በላይ ያገለገለ መሆን አለበት።
🚨Password በጭራሽ አይቀየርም።
🚨 በፈለጉበት ሰዓት አካውንቶን መልሰው መውሰድ ይችላሉ።
📌 Your Account is Used Only for Business Networking
ለተጨማሪ መረጃ 👉 @Lali88
https://t.me/linkedinrentalservice0 join fast
🤣52👍1
ASTU Network ®️
#AI 🤖 Best AI Tools You Have to Know 1. ChatGPT.com → Solve anything 2. LightPDF.com → Chat with files 3. Tome.app → Build presentations 4. Pika.art → Create videos 5. Gamma.app → Design docs 6. Suno.ai → Make music 7. PicWish.com → Image editing 8. Perplexity.ai…
#AI 🤖

25 AI Tools You Can’t Ignore in 2025


1. ChatGPT.com – solves anything
2. Syllaby.io – create and publish videos
3. MidJourney.com – generates art
4. Replit.com – writes and runs code
5. Heygen.com – creates AI avatars
6. Soundraw.io – produces music in seconds
7. Ranked.ai – rank higher on Google
8. Submagic.co – turn long videos into shorts
9. SlidesAI.io – makes presentations for you
10. PicWish.com – edits photos fast
11. Fastread.io - create ebooks
12. Bibley.io - ai for Bible study
13. Manus.im - code any app
14. Capsho.com - podcast into content
15. Webinarkit.com - ai for webinars
16. Creatorunlock.com - ai for YouTube
17. sociable.how - write viral comments
18. Adcreative.ai - ai tool for advertising
19. Canva.com - design anything
20. Fastphoto.io - create ai headshots
21. askcoachken.com - ai relationship coach
22. threadmaster.ai - create viral Facebook thread
23. V0.dev - create frontend mockups
24. suno.com - create ai music
25. keywordsearch.com - boost ad conversions

|| @ASTU_Network
3👍1💔1
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ተቀራራቢ ይዘት ባላቸው የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራሞች ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ክለሳ በማድረግ ወደ ትግበራ ገብቷል።

ሚኒስቴሩ ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ተቀራራቢ ይዘት እና ስያሜ የነበራቸው ፕሮግራሞችን በመለየት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኢንዱስትሪዎች ከተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በፕሮግራሞቹ ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ማስተካከያ አድርጓል፡፡

ተቀራራብ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞችን በማጠፍ/በማዋሃድ አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜዎች መሰጠቱን በአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ደብዳቤ ያሳያል።

በዚህም 147 ፕሮግራሞችን ወደ 54 በመጠቅለል አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜ መሠጠቱ ተገልጿል። በተወሰኑ ፕሮግራሞች ላይ ማስተካከያ የተደረጉ ሲሆን የታጠፉ ፕሮግራሞች እንዳሉም ለማወቅ ተችሏል።

ይህም በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። (የፕሮግራሞቹ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)

©️ tikvahuniversity

|| @ASTU_Network
👀5👎2👏2😁2😨21😢1
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካላንደርን ይፋ አድርጓል፡፡


በትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን ነሐሴ 12/2017 ዓ.ም የተፈረመ የ2018 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካላንደር ዝርዝር ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተልኳል፡፡

መስከረም 05-06/2018 ዓ.ም
የመጀመሪያ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች (ሪሚዲያል ተማሪዎችን ጨምሮ) በየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ያደርጋሉ፡፡

መስከረም 08-09/2018 ዓ.ም
የሁሉም የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች (ሪሚዲያል ተማሪዎችን ጨምሮ) ምዝገባ ያደርጋሉ፡፡

መስከረም 12/2018 ዓ.ም
የሁሉም የቅድመ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች በቅጣት ምዝገባ፣
የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ትምህርት ይጀመራል፡፡

(ሙሉ የ2018 ትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካላንደር ከላይ ተያይዟል፡፡)

©️ tikvahuniversity

|| @ASTU_Network
🤷‍♀3🤣32🥰1