ASTU Network ®️
4.13K subscribers
1.42K photos
32 videos
285 files
340 links
🛜 ASTU Network ®️

➲ Join us || @ASTU_Network ||
|| @ASTU_Network_Group ||

📚 Library: @ASTU_Network_Library

👁‍🗨 We are here to keep you updated!

➲ Admin 📩
👤 @NS_Nazu

Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷]

|➲| @ASTU_Network
Download Telegram
በአዲስ አበባ በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በዲኤስቲቪ ሲመለከቱ የነበሩ ደጋፊዎች በነበሩበት ሆቴል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ።

ትላንት ምሽት በአሜርካ ኒው ጀርሲ በሚገኘው ሜትላይፍ ስታዲየም በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ "ለቡ" አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ በዲኤስቲቪ እየተመለከቱ በነበሩ ተመልካቾች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ለጋ ወጣት ህይወት አልፏል።

በቀብር ስነስርዓቱ ላይ የተገኙ የሟቹ ወዳጆች ፣ ጓደኞች "አሟሟቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው" ያሉ ሲሆን "ግለሰቡም ተይዟል" ብለዋል።

"እስከ ምሽት 3:00 ሰአት ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር ካመሸ በኋላ ከጓደኞቼ ጋር ትንሽ ልዝናና ብሎ ሆቴሉ እንደገባ ነው ክስተቱ የተፈጠረው" ሲሉ ተናግረዋል።

በአሟሟቱ ቤተሰቦቹ እጅግ ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኙ ለመመልከት ችለናል።

"ወጣቱ ከኳስ ስሜታዊነት መቆጠብ ወይም የእግር ኳስ ጨዎታዎችን ተሰባስቦ ከማየት መቆጠብ አለበት ካልሆነ ግን የቤተሰብን ሀዘን ማብዛት ነው" ሲሉ ለቀስተኞች ተናግረዋል።

"ወጣቶች እባካችሁ ለቤተሰቦቻችሁ ሀዘን አታብዙ፣ ሁሉን በማስተዋል አድርጉ፣ ማታ ማታ አታምሹ፣ በአጭሩ እየተቀጫችሁ ሃዘናችንን አታብዙት" የሚሉ እና ሌሎች ልብ የሚነኩ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል።

በስልክ ቃላቸውን የሰጡ አንድ እናት ሟቹን ወጣት እንደሚያውቁት ገና በ22 ዓመቱ በተፈጠረው ፀብ እንደተቀጠፈ ገልጸዋል። 

"በውጭ ኳስ ምክንያት የለጋ ወጣት ህይወት መጥፋቱ እጅግ ያሳዝናል። ሁሉም ወጣቱ ከስሜታዊነት መራቅ አለበት፣ የሚመለከታቸው አካላትም እንዲህ ያለው ነገር እንዳይፈጠር የራሳቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው" ሲሉ እናታዊ መልዕክታቸውን በሀዘን ስሜት አስተላልፈዋል።

|| @ASTU_Network
😭83💔1
ASTU Network ®️
በአዲስ አበባ በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በዲኤስቲቪ ሲመለከቱ የነበሩ ደጋፊዎች በነበሩበት ሆቴል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ። ትላንት ምሽት በአሜርካ ኒው ጀርሲ በሚገኘው ሜትላይፍ ስታዲየም በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ "ለቡ" አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ በዲኤስቲቪ እየተመለከቱ በነበሩ ተመልካቾች…
ለዚህ እኮ ነው ይሄ ነገር ልክ ይኑረው የሚባለው 😣... ወይ የሀገራችን ኳስ አይደለ 🤷‍♂️😕 ... የራሳችን ቢሆን እንኳ አንድ ነገር ይባላል 😐 ... ኧረ እንደውም እሱም አያስፈልግም! 🙅‍♂️

ጭራሽ ከእኛ ጋር በምንም በማይገናኝ በውጪ ኳስ ይሄን ያክል ነፍስ እስከሚጠፋ ድረስ በዚህ ልክ ያለ ስሜታዊነት ምን ማለት ነው? ጥቅሙስ ምንድንነው??🤔

ልጁ ቀኑን ሙሉ ከቤተሰቡ ጋር ውሎ ኳስ ለማየት ሄዶ አስከሬኑ ከኳስ ቦታ ሲመለስ ቤተሰቡ (በተለይ እናቱ) የሚሰማቸውን ስሜት አስቡት... 😭💔

ኧረ ጎበዝ ወዴት እየሄድን ነው? ኧረ ነገ ኮ ብዙ ነገር ነው የሚጠብቀን ... ኧረ ይሄ ነገርኮ የራሳችንን ኑሮ አስጥሎን ሁሉ ነገራችንን ቁማር (bet) እና ጊዜ ማባከን ላይ አስደረገን ... ኧረ ለራሳችን ማሰብ ቢያቅተን እና እንደው ህልም ምናምን የምንለው ፣ የምንኖርለት እና የምንጠነቀቅለት ነገር ባይኖረን እንኳን ቢያንስ ዋጋ ለከፈሉልን ቤተሰቦቻችን እናስብ ... ኧረ እንሰብሰብ ... ቅዱስ መጽሐፉም እኮ "ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ" ይላል... 😭🤲

በእውነት እጅግ በጣም ያሳዝናል! 😭💔
Bro ነፍስህ በሰላም ትረፍ! 🕊

.
😭7🤷‍♂31🤷‍♀1👍1
Many students have been asking this... 👇

Which school is better according to the education provided at ASTU? Choose one and share your reasoning in the comments section:
Anonymous Poll
29%
#SoMCME [School of Mechanical, Chemical and Material Engineering] 
20%
#SoCEA [School of Civil Engineering and Architecture] 
10%
I am not sure [IDK] 
40%
Just to see the vote!
🤔53😁1
በ2018 ዓ.ም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የጥራት ቁጥጥር እንደሚጀመር ታውቋል።

የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ በመጪው አመት 2018 ዓ.ም በመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ላይ የጥራት ቁጥጥር እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ውብሸት ታደለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃለመጠይቅ፣ በአሁን ወቅት በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እየተካወነ ያለው ዳግም ምዝገባና ምዘና ስራ ሲጠናቀቅ ይኸው እንቅስቃሴ በመንግስት ኮሌጆች፣ የማሰልጠኛ ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ላይም በቀጣዩ አመት እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

አቶ ውብሸት ታደለ በዝርዝር ምን አሉ ?

" አሁን እየተከናወነ ያለውን የመጀመሪያው ዙር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ምዝገባና ግምገማ እንደጨረስን፣ በሁለተኛውና በሶስተኛው ዙር የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን እንመዘግባለን፣ እንገመግማለን፡፡ በፌደራልና በክልሎች የተከፈቱ ኮሌጆችና የማሰልጠኛ ተቋማት አሉ፡፡ መጀመሪያ የምናየው እነሱን ነው፡፡ ቀጥለን ደግሞ ሁሉንም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን እናያለን፡፡

እስካሁን የግል ተቋማት ላይ ያተኮርነው፣ እዚህ ዘርፍ ላይ የነበረው ችግር ሰፊ ስለሆነ ነው፡፡ ያለንን የሰው ሀይልና ሀብት ወደዚህ ዘርፍ በማዞር ቅድሚያ ሰጥተናል፡፡ ሁሉንም አንድ ላይ ማየት አንችልም፡፡ አሁን የግሎቹን ተቋማት ካጠናቀቅን በኋላ፣ ወደ መንግስት ትምህርት ተቋማት ግምገማ እንገባለን፡፡

የመንግስት የትምህርት ተቋማት በመሰረተልማት በኩል ችግር የለባቸውም፡፡ የራሳቸው ህንፃና ግቢ አላቸው፡፡ ስለዚህ እነሱ ጋ ትኩረት የምናደርገው ጥራት ላይ ነው፡፡ ለምሳሌ ፕሮግራሞቹ/ትምህርቱ በበቂ መምህራንና አኳሀን መሰጠቱን እናያለን፡፡ አካዳሚያዊ የድርጊት መርሀግብራቸው ትክክል መሆኑን እንፈትሻለን፡፡

የተገቢነትና አስፈላጊነት ጥያቄ የሚነሳባቸው፣ ዝም ብለው ያለ በቂ ጥናት የሚከፈቱ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ የትምህርት ግብአት እና የላቦራቶሪ ቁሳቁሶች፣ እንዲሁም የዳታ ማዕከላቸው ይታያል፡፡ ለተማሪዎችና ለአስተማሪዎች የሚቀርቡት አገልግሎቶች ደረጃቸውን የጠበቁ ናቸው ወይ የሚለውን እናያለን፡፡

ቀደም ብለው የተቋቋሙት ነባሮቹ ዩኒቨርሲቲዎች የዚህ አይነት ችግር ላይኖርባቸው ይችላል፡፡ አዳዲሶቹ ዩኒቨርሲቲዎች ግን በነዚህ መስፈርቶች በኩል ክፍተት ይኖሩባቸዋል፡፡

በአጠቃላይ ግን ጥራትን እናምጣ ካልን፣ ሁሉንም የመንግስት ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎችን መፈተሽ አለብን፡፡ በዳግመ ምዝገባችን፣ በተቋማቱ የሚሰጡትን ሁሉንም ፕሮግራሞቻቸውን እናያለን፡፡ ፋይሎቻቸውን እንዲያስገቡ አድርገን እያንዳንዱን ፕሮግራም እንመዝናለን፡፡ አያስፈልጉም የምንላቸውን ፕሮግራሞች እንዲዘጉ፣ ያስኬዳሉ የምንላቸውን ደግሞ እንዲያስቀጥሉ እናደርጋለን፡፡

የመንግስት ተቋማትን ከግሎቹ በበለጠ ጠንከር ያለ ምዘና እናደርጋለን፡፡ ጠበቅ አድርገን ለማየት እንሞክራለን፡፡ የግሎቹን እንደጨረስን፣ በየክልሉ ያሉትንና በፌደራል ደረጃም ያሉትን ኮሌጆችና የማሰልጠኛ ተቋማትን እናያለን፡፡ ከዛም ወደ ዩኒቨርሲቲዎች እንሔዳለን፡፡ ይህ ስራ በ 2018 ዓ.ም የሚጀመር ይመስለኛል " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
6👏3
#ዜና

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ሁሉም ተማሪ ዩኒቨርስቲ የሚገባበት እለት መሆኑ ተነገረ

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የቀጣዩ አመት የዩኒቨርስቲ ት/ት ይጀመራል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የፈተና ውጤት ጳጉሜ ላይ ይፋ ይሆናል በማለት እስከዚያም ድረስ የሚቆየው ፈተና ያልወሰዱና በመጪው ነሐሴ ወር ለፈተና የሚቀመጡ ቀሪ ተፈታኝ ተማሪዎች በመኖራቸው መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

በተለያየ ምክንያት ዘግይተው ትምህርት የጀመሩ በመኖራቸው ነው ፈተና እኩል ያልወሰዱ ተፈታኞች ያሉት በማለትም በመሆኑም ጳጉሜ ወር ላይ የ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት ከታወቀ በኋላ መስከረም 8 ቀን ሁሉም ተማሪ ዩኒቨርስቲ የሚጀምርበት እለት እንደሚሆን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

የትምህርት ካላንደርን በአግባቡ አክብሮ በመስራት የፈተና ጊዜያትንም ላለመሻማት ይሰራል ሲሉ ያከሉት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ከመስከረም ጀምሮ ጥብቅ አሰራር እንደሚኖር ገልጸዋል።

እንደ ሀገር እኩል ውጤት ተናግሮ በእኩል ትምህርት ለማስጀመር ሲባል ቀሪ ያልተፈተኑ ተፈታኝ ተማሪዎችን ጠብቆ ማስጨረስ እንደሚገባ የተናገሩት የትምህርት ሚኒስትሩ በራሳቸው ፈቃድና ምክንያት አስቀድመው ፈተና ላይ ካልተቀመጡት በቀር ሌሎቹ የመመዘኛ መስፈርቱ አካል መሆናቸውን ገልጸዋል።

|| @ASTU_Network
😢279👎4💔2🤷‍♀1
#Ethiopia 🇪🇹 — the land of diverse societies and cultures! 🤗😁
.
🤣122👎1💔1😭1
#Tech_News

የቻይና ሳይንቲስቶች የንቦችን እንቅስቃሴ መቆጣጠር የሚያስችል ቴክኖሎጂን ተግባራዊ አደረጉ
****

የቤጂንግ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲስቶች 74 ሚሊግራም የሚመዝን የነፍሳት እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂን ንብ ላይ በመጠቀም በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነውን ፈጠራቸውን አስተዋውቀዋል።

|| @ASTU_Network
3😱2
#ዜና

በየአመቱ የዩኒቨርሲቲዎችን ደረጃ በማውጣት የሚታወቀው ፣ ፈር-ቀዳጅ እና አንጋፋ የሆነው ‛UNIRANK’ የ 2025 አመት የዩኒቨርስቲዎችን ደረጃ ይፋ አድርጓል።

አሁን ያለውን ሁኔታ መሰረት በማድረግም የኢትዮጵያን ዩኒቨርስቲዎች ደረጃ አውጥቷል። በዚህም መሰረት ከኢትዮጵያ ከ50 በላይ ዩኒቨርስቲዎችን ያወዳደረ ሲሆን ፣ በውድድሩ የመደበኛ ፣ የመንግስት ሰራተኞች እና የፖሊስ ዩኒቨርስቲዎችንም አሳትፏል።

በ 2025 ከኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች አንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲሆን ጅማ ዩኒቨርስቲ እና ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ሁለተኛ እና ሶስተኛ በመሆን ሲከተሉት ፣ ዩኒቨርስቲያችን አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ደግሞ በስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ከአንደኛ እስከ ሃምሳኛ ደረጃ የተቀመጡትን ዩኒቨርስቲዎች ከላይ ከተያያዙት ፎቶዎች ላይ ይመልከቱ!

📰 ዘገባው የASTU Network ነው!

|| @ASTU_Network
😭146💔2🙊1
ASTU Network ®️
Photo
#UNIRANK የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲን በተመለከተ ምን አለ

በ 2025 ያለውን የኢትዮጵያ የዩኒቨርስቲዎች ደረጃ ይፋ ያደረገው ‛UNIRANK’ ስለ ዩኒቨርስቲያችን አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የተወሰኑ መረጃዎችን አውጥቷል።

ዩኒቨርስቲው በ1993 እንደተመሰረተ እና በተለያዩ መስኮች በዲግሪ ፣ በማስተርስ እና በዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎቹን እያበቃ ያለ ተቋም እንደሆነ ገልጿል። በተጨማሪም ትምህርታዊ እና ትምህርታዊ-ያልሆኑ አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑንም አክሏል።

ደረጃውን በተመለከተ ባወጣው መረጃም ዩኒቨርስቲው በ 2025 በኢትዮጵያ 8ኛ ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ 7689ኛ ደረጃ መያዙን አስታውቋል።

ድህረገጹ ስለ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ያወጣቸውን መረጃዎች ከላይ ከተያያዙት ፎቶዎች ላይ ይመልከቱ!

📰 ዘገባው የASTU Network ነው!

|| @ASTU_Network
🙉13🙊4😭31👍1💔1
A Statement from Admin!

Hey second-year students! 
How have you been? 🙂


Summer is making me 🥶... I don't know about you, but I hope it feels the same! 😁 

Today, I want to ask you one thing... 🙂 

The ASTU Student Union is preparing an award for the "Best Telegram Channel of the Year"! You will vote for a channel that has provided you with accurate information and useful resources. 

Here’s a brief story: 

I created this channel on March 17, 2024, and have been serving my batches by providing accurate and timely information, reading materials, and much more! 

First, we started together on the «ASTU Freshman Channel. When the new freshman students came, we transitioned to this channel to tailor it to our needs. 

Since then, we have moved forward together with updates and resources on our channel! 

Now, it's clear that the best channel of the year for you is the «ASTU Network»! ❗️ 

It's time to win together! 🏆 

Follow the vote @astu_hl and make sure to vote for our fantastic channel when the poll is posted! 

Thank you! Love you all! 🫶🏽❤️‍🔥 

✍️👤: Admin 

|| @ASTU_Network
🏆84👎1👌1
Forwarded from ASTU -HL
✍️Final list channel!

Voting starts tonight at 1;00 LT (today) and will last for 2 consecutive days.
The voting will be held only on this Telegram channel.👉@ASTU_HL

®student Union

👉Please share and forward ⏭️

#@ASTU_HL
#@student_Union1
#join_now #competition #best #telegram #channel #in#2025
6👌2👎1🔥1