ASTU Network ®️
4.13K subscribers
1.42K photos
32 videos
285 files
340 links
🛜 ASTU Network ®️

➲ Join us || @ASTU_Network ||
|| @ASTU_Network_Group ||

📚 Library: @ASTU_Network_Library

👁‍🗨 We are here to keep you updated!

➲ Admin 📩
👤 @NS_Nazu

Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷]

|➲| @ASTU_Network
Download Telegram
ሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ተጀመረ።

የ2017 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

የመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች መሰጠት ተጀምሯል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የሚኒስቴሩ አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢ/ር ነጋሽ ዋጌሾ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ፈተናውን አስጀምረዋል።

ዘንድሮ በወረቀትና በበየነ መረብ ከ608 ሺ በላይ ተማሪዎች ፈተናቸውን ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው።

©️ tikvahethiopia

|| @ASTU_Network
5🕊5
#NationalExam🇪🇹

ፆታዊ ትንኮሳ የፈፀሙ ሦስት ተማሪዎች ከሀገር አቀፍ ፈተና ታገዱ።

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ባለው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ወደ መቱ ዩንቨርስቲ ከገቡት ተማሪዎች ውስጥ ሦስት ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ዕፆታዊ ትንኮሳ በመፈፀማቸው ከፈተናው መታገዳቸውን የመቱ ዩንቨርስቲ አስታወቀ።

ዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት አለሙ ድሳሳ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " በርካታ ተማሪዎች ወደ ግቢ ከገቡ በኃላ ወጣ ያለ ፀባይ እያሳዩ ነበር " ብለዋል።

ዩኒቨርስቲውም ለፈተናው ከተቋቋመ ኮማንድፖስት ጋር በመሆን የመቆጣጠር ሥራ ሲሰራ እንደነበር በማንሳት፤ ሦስቱ ተማሪዎች በሴት ተማሪዎች ላይ ሰኔ 22 ቀን 2017 ዓ.ም አደባባይ ላይ ትንኮሳ መፈፀማቸውን ተበድለናል ብለው በመጡ ሴቶች ቅሬታ እና ዩንቨርስቲውም ባደረገው ማጣራትብ ድርጊቱን መፈፀማቸውን አረጋግጧል።

" ትንኮሳ አድራጊዎቹ በአደባባይ ሴቶችን በግድ መሳም፤ ልብሳቸውን መገለብ እና መንካት የማይፈቀድ የአካላቸውን ክፍል በመንካታቸው ሴቶቹ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል " ብለዋል።

በዚህ የተነሳ የትንኮሳ ወንጀል በፈፀሙ ወንዶች ላይ ከዘንድሮው አመት ፈተና እንዲታገዱ መደረጉን ገልጸዋል።

ተማሪዎቹ አንዱ ከኢሉ አባቦር ዞን በቾ ወረዳ ሁለቱ ደግሞ ከምስራቅ ወለጋ የመጡ መሆናቸውን ፕረዝዳንቱ አክለዋል።

እርምጃ ከተወሰደ በኃላ በግቢው ሲስተዋል የነበረው የተማሪዎች ሥነ ምግባር መሻሻሉንም ተናግረዋል።

ወደፊትን ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠር ትምህርት ቤቶች የፈተና ሥነ ምግባር ላይ ለተማሪዎች ግንዛቤ መስጠት እንዳለባቸው የገለፁት  አለሙ ድሳሳ (ዶ/ር) ሴት ተማሪዎችም ራሳቸውን እንዲጠብቁና ለትንኮሳ ራሳቸውን እንዳይጋብዙም ጠይቀዋል።

©️ tikvahethiopia

|| @ASTU_Network
8😁4
#AAU

EXIT EXAM ከዚህ በኋላ በቁጥር አይገለጽም Just Pass or Fail... 😁
.
👍13😁135
የ85 ዓመቱ አባት የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲን መንገድ ያዙ!

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለመውሰድ ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጉዞ የጀመሩት አቶ ማኖ ማገሶ የዘንድሮውን ፈተና ከምን ጊዜውም በተለየ መልኩ ታሪካዊ አድርገውታል።

የ85 ዓመቱ አባት የካቻ ካሻሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ሲሆኑ፣ በዚህ ዕድሜያቸው ፈተና መፈተናቸው በእርግጥም ትልቅ አርአያነት ነው።

አቶ ማኖ ማገሶ

* የአምስት ወንዶችና
* የስድስት ሴቶች፣ በድምሩ የአስራ አንድ ልጆች አባት ናቸው።

ቀደም ሲል በጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር ጋርዱላ አውራጃ የገበሬ ማኅበር ጽ/ቤት ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል።

ከዚህም በላይ በገረሴ ወረዳ ጌዣ ደንን በማስተካከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርን ከጀመሩት መካከል አንዱ ናቸው።

የካሻሶ ትምህርት ቤትን በማቋቋም እና ለመምህራንና ለአካባቢው ህብረተሰብ ምቹ እንዲሆን ማኖ ገበያን (ወይም ካሻሶ ገበያን) በመክፈት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ልጆቻቸውን በማስተማርም አርባ ምንጭ፣ አዲስ አበባ አልፎ ተርፎም ቻይና ድረስ በትምህርት እንዲደርሱ የረዱ ታላቅ አባት ናቸው።

የቦንኬ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት እንዳስታወቀው፣ የአቶ ማኖ ማገሶ ለ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ዙር ማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መፈተን እጅግ ልዩና ታሪካዊ ክስተት ነው።

መልካም ዕድል ለአቶ ማኖ
እና ለሁሉም ተፈታኞች! 🙏

Via የቦንኬ ወረዳ መንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

|| @ASTU_Network
👏8🤣43
ASTU Network ®️
Photo
የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ተፈታኝ ተማሪዎችን እየተቀበለ ይገኛል
==========================


የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ  የ2017 ዓ/ም የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ተፈታኝ ተማሪዎችን  እየተቀበለ ነዉ::

ከሰኔ 23- ሀምሌ 8 /2017 ዓ/ም በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠዉን የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች  በዩኒቨርሲቲዉ የበላይ አመራሮችና የጸጥታ አካላት አቀባበል እየተደረገላቸዉ ነው::  በዚህ በሁለተኛዉ ዙር  የማህበራዊ ሳይንስ 5140 ተማሪዎች በወረቀት እንዲሁም 897 ተማሪዎች ደግሞ በበየነ-መረብ ለፈተናዉ እንደሚቀመጡ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ፕሮግራም  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ተገኔ ደሳለኝ ገልፀዋል ።

|| @ASTU_Network
😢41
የመንግሥት ሠራተኞች "የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ነጻ ስልጠና" የግድ ሊወስዱ እንደሆነ ተሰማ።

የበይነ መረብ ስልጠናውን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ ሠራተኞች የሥራ እና የደምወዝ እድገት እንዲሁም የዝውውር ዕድል እንደማያገኙ ተሰምቷል።

ስልጠናውን ያጠናቀቀ የመንግሥት ሠራተኛ የምስክር ወረቀቱ ከግል ማህደሩ ጋር እንደሚያያዝ ዋዜማ ምንጮቿን ጠቅሳ ዘግባለች።

የምስክር ወረቀቱን መያዝ እንደ አንድ መስፈት መቀመጡን የጠቀሰው ዘገባው፤ ሁሉም የመንግሥት መዋቅሮች ማሠልጠን ያለባቸውን የሠራተኛ ኮታ እንደተቀመጠላቸው ታውቋል።

አንድ ሠራተኛ ፈተናውን ወስዶ የሚያልፈው ከ20 ከሚያዘው ነጥብ 12 እና ከዚያ በላይ ካመጣ እንደሆነ ተገልጿል።

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርትፍኬት ማግኘት የሚያስችለውን ስልጠና ባለበት ሆኖ መውሰድ ይችላሉ።

ለመመዝገብ 👇
https://www.ethiocoders.et/

የስልጠና ዘርፎች፦

► ዌብ ፕሮግራሚንግ
► አንድሮይድ ማበልፀግ
► ዳታ ሳይንስ
► አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ፋንዳሜንታልስ

©️ tikvahuniversity

|| @ASTU_Network
🤣242
#ዜና

ኢትዮጵያ የራሷን የዋትስአፕ፣ ጂሜይል እና ዙም ስሪቶች እያበለፀገች እንደሆነ መገለጹን፣ ስፑትኒክ ዘገበ።

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) አማካኝነት የተገነቡት የዲጂታል ቴክኖሎጂ መድረኮች የሳይበር ደህንነትን ለማሻሻል እና ከኢትዮጵያ የቁጥጥር ማዕቀፍ ውጪ በሆኑ የውጭ ኩባንያዎች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ የታለሙ መሆናቸውን የሃገር ውስጥ ሚዲያዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።

ለጂሜል አማራጭ ሆኖ የቀረበው “እርጋሜል” ከወዲሁ በመንግሥት ተቋማት ሥራ ላይ መዋል እንደጀመረ ተነግሯል፡፡ "ሰርኩትኒ" የዋትስአፕ እና ቴሌግራም ምትክ እንዲሆን የሚጠበቅ ሲሆን ገና በትግብራ ላይ ነው የሚገኘው፡፡

ለቨርቹዋል ግኑኝነቶች እንዲሆን በኢንሳ የበለጸገ የተባለው የዙም ምትክ “ደቦ” ደግሞ የሙከራ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ዘግቧል።

ምንጭ:- Zehabesha

|| @ASTU_Network
🤣388🗿2👍1😱1
#Update

The student portal is now reopened. If you have anything to check or edit, please do so before it closes.

🔗 Link 🔗
https://estudent.astu.edu.et


||
@ASTU_Network
😁11🙏3
#Ad

> LinkedIn rental በመከራየት በየሳምንቱ 20$ (3000ብር) ተከፋይ ይሁኑ! 💰

> ከተከፈተ አንድ አመት የሆነውና ከ 100 በለይ connection ያለው Linkedin

> አካውንት ያላቹ ማከራየት ትችላላችሁ።
ማወቅ ያለባችሁ የናንተን LinkedIn  አካውንት email እና password  መስጠት አለባችሁ ለማከራየት ፣ ነገርግን ያለ እናንተ ፈቃድ email ወይም password  መቀየር ስለማንችል አካውንታችሁ አደጋ ላይ አይወድቅም።

>በአሁኑ ጊዜ፣ ለማስታወቂያ ብዙ ተከታዮች
ያሏቸው በርካታ የLinkedIn አካውንት እንፈልጋለን።

● *ዓላማ:* > የማስተዋወቂያ እና ህጋዊ የንግድ አላማዎችን ብቻ ማገልገል
> የመለያውን ደህንነት ያረጋግጡ
> እናንተ አካውንት ውስጥ ላሉ friendoch/ ጓደኞች መልእክት አይላክም
● *መስፈርቶች:* > ከ 100 በላይ ግንኙነቶች (connection )  እና ከተኸፈተ ቢያንስ 1 አመት የሆነው አካውንት

> የLinkedIn መለያዎን ለመከራየት ፍላጎት ካሎት እባክዎን በቴሌግራም
@linkedin_rentalll ያውሩን
🤔4😡42
#EthiopianDefenceUniversity

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በቢሾፍቱ እያስመረቀ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በምህንድስና፣ በጤና ሳይንስ እና በማኅበረሰብ ሳይንስ የትምህርት መስኮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ተማሪዎችን በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚገባ በትምህርት ሚኒስቴር መገለፁ ይታወቃል፡፡

©️ tikvahuniversity

|| @ASTU_Network
😁7🔥5🗿1
በአዲስ አበባ በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በዲኤስቲቪ ሲመለከቱ የነበሩ ደጋፊዎች በነበሩበት ሆቴል በተፈጠረ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ።

ትላንት ምሽት በአሜርካ ኒው ጀርሲ በሚገኘው ሜትላይፍ ስታዲየም በፒኤስጂ እና ቼልሲ መካከል የተደረገውን የዓለም የክለቦች ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ "ለቡ" አካባቢ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ በዲኤስቲቪ እየተመለከቱ በነበሩ ተመልካቾች መካከል በተፈጠረ ግጭት የአንድ ለጋ ወጣት ህይወት አልፏል።

በቀብር ስነስርዓቱ ላይ የተገኙ የሟቹ ወዳጆች ፣ ጓደኞች "አሟሟቱ እጅግ የሚያሳዝን ነው" ያሉ ሲሆን "ግለሰቡም ተይዟል" ብለዋል።

"እስከ ምሽት 3:00 ሰአት ድረስ ከቤተሰቦቹ ጋር ካመሸ በኋላ ከጓደኞቼ ጋር ትንሽ ልዝናና ብሎ ሆቴሉ እንደገባ ነው ክስተቱ የተፈጠረው" ሲሉ ተናግረዋል።

በአሟሟቱ ቤተሰቦቹ እጅግ ከፍተኛ ሀዘን ውስጥ እንደሚገኙ ለመመልከት ችለናል።

"ወጣቱ ከኳስ ስሜታዊነት መቆጠብ ወይም የእግር ኳስ ጨዎታዎችን ተሰባስቦ ከማየት መቆጠብ አለበት ካልሆነ ግን የቤተሰብን ሀዘን ማብዛት ነው" ሲሉ ለቀስተኞች ተናግረዋል።

"ወጣቶች እባካችሁ ለቤተሰቦቻችሁ ሀዘን አታብዙ፣ ሁሉን በማስተዋል አድርጉ፣ ማታ ማታ አታምሹ፣ በአጭሩ እየተቀጫችሁ ሃዘናችንን አታብዙት" የሚሉ እና ሌሎች ልብ የሚነኩ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል።

በስልክ ቃላቸውን የሰጡ አንድ እናት ሟቹን ወጣት እንደሚያውቁት ገና በ22 ዓመቱ በተፈጠረው ፀብ እንደተቀጠፈ ገልጸዋል። 

"በውጭ ኳስ ምክንያት የለጋ ወጣት ህይወት መጥፋቱ እጅግ ያሳዝናል። ሁሉም ወጣቱ ከስሜታዊነት መራቅ አለበት፣ የሚመለከታቸው አካላትም እንዲህ ያለው ነገር እንዳይፈጠር የራሳቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው" ሲሉ እናታዊ መልዕክታቸውን በሀዘን ስሜት አስተላልፈዋል።

|| @ASTU_Network
😭83💔1