ASTU Network ®️
4.16K subscribers
1.44K photos
32 videos
288 files
346 links
🛜 ASTU Network ®️

➲ Join us || @ASTU_Network ||
|| @ASTU_Network_Group ||

📚 Library: @ASTU_Network_Library

👁‍🗨 We are here to keep you updated!

➲ Admin 📩
👤 @NS_Nazu

Ⓝ Ŋazarene Ŝon [🥷]

|➲| @ASTU_Network
Download Telegram
Wireless gaming mouse! 🖱️

DM:
Wireless 🖱

@Astu_marketplace
Scientific Calculator for sale!

It's new!

DM:
Sc.Calculator

@Astu_marketplace
👍1
🤣9🤯1
ASTU Network ®️
|| @ASTU_Network
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተቀጥረው የሚሰሩ የአንዳንድ የህንድ ዜጎች ፎርጅድ ዶክመንት ሲዳሰስ

- "ቅጥር ለማግኘት ለዩኒቨርስቲው ሰራተኞች የሁለት ወር ደሞዝ የሚሰጡ አሉ"

(መሠረት ሚድያ)- በኦሮሚያ ክልል በሚገኘው የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተቀጥረው የሚሰሩ አንዳንድ የህንድ ዜግነት ያላቸው አስተማሪዎች ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እንዳላቸው እና ይህ እንዳይታወቅ ከአንዳንድ የዩኒቨርስቲው አመራሮች ጋር እንደሚሰሩ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።

መሠረት ሚድያ የተመለከታቸው እና በአንዳንድ የህንድ አስተማሪዎች ጭምር እውነትነታቸው የተረጋገጠ እነዚህ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በወር በሺዎች የሚቆጠር ዶላር የሚከፈላቸው አንዳንድ ህንዳውያን የትምህርት ማስረጃቸው ወይ ሀሰተኛ ነው ወይም ያልተማሩትን የዶክትሬት ዲግሪ እንደተማሩ ሀሰተኛ ማስረጃ አቅርበው ተቀጥረዋል።

"አንዳንዶቹ የክህሎት እና የትምህርት ማረጋገጫ ሂደትን ግልፅ ባልሆነ መልኩ አልፈው ተቀጥረው ይገኛሉ፣ ይህ ደግሞ እየተደረገው በዩኒቨርስቲው ጥቂት አመራሮች ተሳትፎ ጭምር ነው" የሚሉት የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ መምህር የነበሩት ዶ/ር ሱረሽ ኩማር ናቸው።

አንዳንድ ህንዳውያን ግዜያቸውን እና ሙያቸውን በመጠቀም ለውጥ ለማምጣት ጥረት እያረጉ ቢሆንም እነዚህ ሀሰተኛ ዶክመንቶችን ይዘው እየመጡ የሚቀጠሩ ህንዳውያን ችግር እየሆኑ እንደመጡ ዶ/ር ሱረሽ ያስረዳሉ።

"ሀሰተኛ ዶክመንት ይዘው የሚመጡ እነዚህ ግለሰቦች የኢትዮጵያን የትምህርት ስርዐት እየገደሉት ነው" የሚሉት ዶ/ር ሱረሽ የእነዚህን ህንዳውያን ስም በዝርዝር ያቀረቡበትን ዶክመንት መሠረት ሚድያ ተመልክቷል።

አንዳንዶቹ ህንዳውያን ህገወጥ ዶክመንታቸውን ይዘው መጥተው ቅጥር ለማግኘት ለዩኒቨርስቲው ሰራተኞች የሁለት ወር ደሞዝ እንደሚሰጡ ታውቋል።

ከእነዚህ ህንዳውያን መሀል እስከ 14 አመት በኢትዮጵያ ያስተማሩ እንደሚገኙ የተጠቀሰ ሲሆን በዚህ ዙርያ የተሰጠ ማብራርያ የለም።

"አንዳንዶቹ ይባስ ብሎ ከሁለት ዩኒቨርስቲ ደሞዝ ይቀበላሉ፣ አንዳንዶቹ የስራ ፈቃድ የላቸውም ወይም ፈቃዳቸው ተቃጥሏል፣ ይህ ጉዳይ በአስቸኳይ ተጣርቶ እርምት ካልተደረገበት በሀገር ሀብት እና በተማሪዎች ትምህርት መቀለድ ነው" ያሉት ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የዩኒቨርስቲው ኢትዮጵያዊ መምህር ናቸው።

ከዩኒቨርስቲው ምላሽ ካገኘን ይዘን እንመለሳለን።

መረጃን ከመሠረት!

Meseret Media

||
@ASTU_Network
😁8👍7🤯3😢1
ASTU Network ®️
|| @ASTU_Network
ይህ መረጃ የተገኘው ከመሠረት ሚዲያ (Meseret Media) የቴሌግራም ቻናል እንደሆነ እና እኛን የማይመለከት መሆኑን ለዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በሙሉ ለማሳወቅ እንወዳለን!

🔗 የመረጃው ሊንክ 🔗
https://t.me/meseretmedia/890


|| @ASTU_Network
👍2👏1
ASTU Network ®️
|| @ASTU_Network
#ዜና

ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና የሁዋዌ ቴክፎርጉድ ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸነፉ።

            ------------------------------------

(ሚያዝያ 4፣ 2017) የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ቴክ ፎር ጉድ ግሎባል ውድድርን አንደኛ በመሆን አሸንፈዋል።

ውድድሩ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በሚቆየውና በቻይና ቤጂንግ እና ሼንዘን የሚገኙ የቴክኖሎጂ ማዕከሎችን ጉብኝትና የተግባር ስልጠናዎችን ካካተተው ዝግጅት ጋር የተካሄደ ሲሆን ውጤቱ ይፋ የተደረገው ሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም ነው።

በስድስት ተማሪዎች የተወከለው የኢትዮጵያ ቡድን ተማሪዎቹን ከአዲስ አበባ፣ ሃራማያ፣ ጅማ፣ ወልቂጤ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች አሰባስቧል። በውድድሩም ከሞሮኮ፣ ደቡብ አፍሪካ፤ አርጀንቲና አየርላንድ፣ ማላዊ፣ ቬትናም፣ አረብ ኤምሬትስ እና ሌሎችንም ጨምሮ ከዓለም ዙሪያ ከተውጣጡ 12 ልዩ ቡድኖች ጋር ተወዳድሯል። የሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ግሎባል አምባሳደር የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ተማሪ አሲያ ከሊፋም በዝግጅቱ በእንግድነት ተገኝታለች።

ተማሪዎቹ የእንስሳትን ህመሞች አስቀድሞ ለመለየት በተዘጋጀውና በአርተፊሻል አስተውሎት በጎለበተው ኤርሊ ቬት (EarlyVet) በተሰኘው ፕሮጀክታቸው የተወዳደሩ ሲሆን በዚህም ትኩረት ለመሳብ ችለዋል።

ይህ የፈጠራ ፕሮጀክት ከተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) በተለይም ግብ 2 "ዜሮ ርሃብ" እና ግብ 15 "ህይወት በምድር" ከሚለው ጋር የተጣጣመ መሆኑና በግብርና እና በእንስሳት ጤና ላይ ያሉ ወሳኝ ተግዳሮቶችን ይፈታል ተብሎ እንደሚታመን በውድድሩ ተብራርቷል።

የሁዋዌ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሚስተር ሊሚንግ ዬ በቡድኑ ስኬት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው ድሉ የኢትዮጵያውያን ወጣቶች ልዩ ችሎታ እና ፈጠራ የታየበት ነው ብለዋል። አክለውም መጪው ትውልድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመጣው የቴክኖሎጂ ገጽታ ውስጥ እንዲበለጽግ በሚያስፈልገውን ድጋፍ እና እድሎች ማመቻቸቱን ለማስቀጠል ሁዋዌ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ቡድኑ ለዓለም አቀፋዊ ውድድር እድል ያገኘው በግንቦት 2016 ዓ.ም በኤሳውራ ሞሮኮ በተካሄደው የክፍለ አህጉራዊ የቴክፎርጉድ (Tech4Good) ውድድር ወቅት ከ17 የአፍሪካ ሀገራት ከተውጣጡ 28 ቡድኖች ጋር ተወዳድሮ አንደኛ በወጣበት ወቅት መሆኑ ይታወሳል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2008 የተጀመረው የሁዋዌ ሲድስ ፎር ዘ ፊውቸር ፕሮግራም በአገር ውስጥ ያለውን ውድድር ከኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚያዘጋጅ ሲሆን ለተሳታፊ ተማሪዎች ከውድድር ባለፈ የሰዉ ሰራሽ አስተዉሎት (AI)፣ ክላዉድ ኮምፒዉቲንግ፣5ኛ ትውልድ: ሳይበር ደህንነት፣ አይኦቲ እና ቢግ ዳታን ጨምሮ በቴክኖሎጂዎች ላይ አጠቃላይ ስልጠና የሚወስዱበት እድል ያመቻቻል።

መረጃውን ያገኘነው ከትምህርት ሚኒስቴር ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ነው።

|| @ASTU_Network
🔥9👍1
#Urgent‼️

Anyone looking to buy a WiFi router at a low price, DM us below!

DM: WiFi 📶
#ዜና

"ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዘው እንዳይሄዱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል" - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ የሚባል ነገር ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሚመሩት የትምህርት ዘርፍ ላይ ስለአፈጻጻምና ስለታቀዱ እቅዶች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሰጡት ማብራሪያም በሚቀጥለው ሳምንት ከትምህርት ቢሮዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል።

በዚህም ወቅት ተማሪዎች ስልክ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ ስለሚደረገው እንቅስቃሴ እንደሚመከር ገልጸዋል።

"የጋራ ስምምነት ላይ ከደረስን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርት መከታተል ነው እንጂ ከስልክ ጋር የሚጫወቱበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ይደረጋል " ብለዋል።

|| @ASTU_Network
😁5👍3🗿3
ASTU Network ®️
Photo
#MoE

"ከ2019 ጀምሮ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

በዩኒቨርሲቲ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ ዓመት ሳይገቡ በፊት የአንድ ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የተጀመረው እንቅስቃሴ ከ2019 ዓ/ም ጀምሮ ተግባር ላይ እንደሚውል የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ጠቁመዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፤ " በሚቀጥለው ዓመት ላይደርስልን ይችላል ግን ህጋዊ ስርዓቱን በሙሉ ጨርሰን በ2019 ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚማሩ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች ከ2019 ጀምሮ 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይድረጋል " ብለዋል።

"ከዚህ በፊት የነበረ ነው አዲስ አይደለም በጃንሆይ ጊዜ (በአጼ ኃይለስላሴ ጊዜ ማለታቸው ነው) የነበረ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።

"ሁለት ጥቅም አለው ብለን ነው ይሄን የምናደርገው አንደኛ ልጆቹ ዝም ብሎ የቀለም ትምህርት ብቻ ተምረው ሳይሆን ተግባራዊ የሆነ ትምህርትም ለአንድ ዓመት ሄደው የሚሰሩበት ከማህበረሰቡ ጋር የሚተዋወቁበት ነው። ሁለተኛ የአስተማሪዎች እጥረትም ስላለ ልጆችን ወደ አስተማሪነት ለአንድ አመት ቢሆንም ለማስገባት ነው " ብለዋል።

|| @ASTU_Network
🤬6👏3💔3👍21🤨1😭1
ASTU Network ®️
Photo
በዚህ ጉዳይ ከአንድ ደቂቃ ያነሰ ማብራሪያ የተሰጠበትን አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ 👇

https://t.me/ASTU_Network/1286


||
@ASTU_Network
😢3👍1👎1
ASTU Network ®️
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዘው እንዳይሄዱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል" - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

||
@ASTU_Network
🤣7🤷‍♀1
ASTU Network ®️
Photo
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ከ2019 ጀምሮ 3ኛ ዓመት የጨረሱ ተማሪዎች 4ኛ አመት ከመግባታቸው በፊት የ1 ዓመት አገልግሎት እንዲሰጡ ይደረጋል " - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

|| @ASTU_Network
👎18👍3😡3😭2
#NOTICE‼️
If you are interested in becoming a parlama member for the 2018 E.C, this notice is for you!

|| @ASTU_Network
😁7