ASTU General
9.12K subscribers
4.19K photos
109 videos
775 files
950 links
We are dedicated to truth information! For Advertisement and promotion contact us on : @suraf_ell
@samny_K
@hun_era
Lost and Found Materials Post here: https://t.me/astugeneral_lost_found
Download Telegram
➡️ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዮኒቨርሲቲ


አድራሻ

📚 በበረሃማዋ ከተማ በስምጥ ሸለቆ ዕንቁዋ በአዳማ ከተማ የሚገኝ አሪፍ ዮኒቨርሲቲ ነው ።


የአየር ሁኔታ

📚 ሞቃታማ በተለይ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ትንሽ ይሞቃል ፤ ይህን እንጂ ማታ ማታ ደግሞ ያልተጋነነ ብርድ ስለሚኖር ሹራብ ነገርም ያስፈልጋቹሃል ።

የካንፓሶች ብዛት

📚 በውስጡ ያለው ግቢ አንድ ለናቱ ነው አንድ ብቻ ነው ።

የሚሰጡ Fields and Departments


📚 ASTU ላይ ብዙዎቻቹህ እንደምታውቁት ሁለት የትምህርት መስኮች ብቻ ይገኛሉ።

Engineering &
Applied science ናቸው ።


📚 ከሌላው ግቢ ትንሽ ለየት የሚያደርገው pre- engineering የሚያስተምረው ሁለት ሴሚስተር መሆኑ ነው ( department and school የምትመርጡት ሁለተኛ አመት ላይ ነው ማለት ነው ።)


Pre-engineering courses

-General Chemistry(🙄)
- General Physics 1
- Applied Maths 1
- Communicative english.
- Introduction to computing( Python).
- Civic or Logical reasoning.
- HPE( 0 ch)

🎯 Second semister courses ፦


- Applied Maths 2
- Technical drawing
- General physics 2
- Computing ( c++)
- English writing
- Civic or Logic
- HPE(0 ch)

📚 Under Applied science pre-engineering courses ፦


Almost the same as Engineering except one course

🎯 Departments of Applied Natural Sciences are ፦

🎯 Applied Biology
🎯. Applied Chemistry
🎯 Applied Geology
🎯 Applied Mathematics
🎯 Applied Physics
➯ Pharmacy


📚Under Engineering there are 3 schools ፦

1. Electrical
2.Mechanical
3.Civil

📚 Under electrical engineering or CSE there are 3 streams ፦

A) Electrical and computer engineering
B) Electronics and communication engineering
C) Power and control engineering
D)Software Engineering

📚 Under Mechanical engineering
A. Chemical
B. Mechanical
C. Material

📚 Under civil and arc school.፦

A.Architecture
B. Civil
C. Water resource management and hydrolic Engineering
D. Geomatics (በቅርብ የሚጀመር ....!)


የካፌ ምግብ

📚 አንደኛ ነው ምንም አይወጣለትም ፤ በቃ ምርጥዬ ነው ለማለት ቢከብድም የእናታቹሁ ሽሮ ብዙም ትዝ አይላችሁም ።


ከካፌ ውጪ ያሉ ምግቦች

🎯 የምግብ ቤቶች ዋጋ ከ25-40 ብር ባለው range ይጠቃለላሉ። አሪፍ የሚባል ምግብ ያቀርባሉ ...!

አዲስ ነገር

📚 ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገባቹህ ደግሞ አሪፍ ሽልማት ይበረከትላቹሃል ፤ በ2011 ከ3.76 በላይ ላመጡ 59 ተማሪዎች PC💻 ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል። እምናና ካቻምናም በተመሳሳይ ብዙ ተማሪዎች ተሸልመዋል ፤ ከ3.5 በላይ ያመጡም የተሸለሙበት ጊዜ ነበር ። ብቻ እናንተ ጠንክሩ እንጂ ለሽልማቱ አለንላቹህ ። ይሄ ነገር 2012 ጀምሮ ቆሟል ይቀጥላል ተብሏል ።

📚 ሌላም surprise አለ Engineering ለምትገቡ የአምስት ዓመቱን ትምህርት በአራት አመት የመማር ዕድል ሊያጋጥማቹህ ይችላል ግን በጣም ትልቅ ጥረት ያስፈልጋል (ፈተና አለው) ለApplied science ተማሪዎችም የአራት ዓመቱን ትምህርት በሶስት ዓመት ማጠናቀቅ የሚችሉበት መንገድ በተመሳሳይ መልኩ ማለትም በቅድመ ፈተና ተፈትነው በማለፍ ብቻ pre Engineering ሳይማሩ መመረቅ ይችላል።


ውሃ ፤ መብራት እና wifi

📚 ምንም አያሳስብም ትንሽ ውሃው ሙቅ ነው እንጂ ሌላ ጣጣ የለም ፤ WIFI በሽ ነው .....!

ሽንት ቤት

📚 ምርጥዬ ነው ፤ በቃ አያሳስብም የገነት ቁልፍ በሉት ...!


======================
💡 Channel @fresh_astu
👍3😁1

ስለ ASTU መረጃዎች ሳፈላልግ ይሄን አገኘሁ
ይነበብ ATC ላይ ከ 2 አመት በፊት ነው የተለቀቀው።

ይሄን መልዕክት ለወንድም እህቶቻችን አድርስልን ያሉኝ የናንተን ችግር መስማት የማይፈልጉ የአስቱ seniors ናቸው


ASTU የሚገቡ ተማሪዎች ከጅብ ጋር ተቻችለው ለመኖር መዘጋጀት ይኖርባቸዋል ።እኛ ጋር ጅብ የልብ ጎረቤታችን ነው ማለት ይቻላል
ማታ ማታ Space ወይም lab አምሽታቹህ ስትመጡ መንገድ ላይ በግሩፕ ተሰልፈው የሚጠብቋቹህ የጅብ gangsters ናቸው።

ለማስፈራራት ምናምን ሳይሆን መረጃ ለመስጠት ያክል ነው በዛላይ ጅቦቹ ተማሪ ይወዳሉ በተለይ ቸካይ ተማሪ ውስጣቸው ነው በጣም ይመቻቸዋል coz daily ሰላምታ ስለሚያቀርቡላቸው😂

ሌላው ደግሞ ዋው የሚያስብሉ ውብ የሆኑ ወፎች አሉ ፓሮት ሁላ አለች ብቻ ምን አለፋቹህ ግቢው መለስተኛ ፓርክ ነው ሚመስለው የሆነ partu ጫካ ነገር ነው ጦጣ ምናምን ጨቅ አለ።
አንዳንዴ selfie መነሳት ምናምን ካማራቹህ ጌጤ የምትባለዋ 🐢 ኣሊ welcome ትላቹሃለች ።


አልፎ አልፎ ደግሞ ጦጣዎቹ ሴቶች ዶርም እየገቡ ኩኪስ፣ዳቦ፣ቆሎ፣ ብቻ ከሴቶች ዶርም የሚበላ ነገር እንደማይጠፋ ስለሚያውቁ ጎራ እንደሚሉ ከሴቶች የደረሰን መረጃ ያሳያል
ግቢ ውስጥ ጥንቸል ፣ ሚድቆ፣ጃርት፣ክረምት ሲገባ ደግሞ የተለያዩ ጥቃቅን ነፍሳት ...በቃ ባጭሩ በጣም ማራኪ zoo ነው ማለት ትችላላቹህ

ግንቦት እና ሰኔ ላይ ምናምን ግቢው በጣም በሚያማምሩ አበባዎች ያጌጣል ፤ ከዛ ውጭ ባሉት ወራት ብዙም አይስብም

አሁን ላይ ግን ግቢውን ለማሳመር በጣም እየተሰራ በመሆኑ ትልቅ መሻሻል አለው ።

ስለ ግቢው ብዙ ነገር ማውራት ይቻላል ቢሆንም ግን በትምህርት ጥራት በኩል በጣም ተስፋ ያለው ግቢ ነው ፤ ለወደፊት ምናልባትም ከሁለት ከሶስት አመት በኋላ ዩንቨርሲቲው Honour degree list ውስጥ የመግባት እድል አለው ተብሎ ይታመናል

አስተማሪዎቹ ደግሞ point ላይ በጣም አስቸጋሪ ናቸው ሽራፊ ነጥብ አይጨምሩም፤ መጨመር እንኳ እርሱት
ከሌላዉ ግቢ ትምሮ ላይ በጣም Hard ናቸው
ውጤት ለመስቀል ብዙም ላይቀላቹህ ይችላል

የጅቦቹን ነገር ምናምን ብዙም አያስጨንቃቹህ ፤ እናንተን ለማስፈራራት ሳይሆን just ለማስጠንቀቅ ያክል ነው።
ላብ ስታመሹ ተጠባብቃቹህ ለመሄድ ሞክሩ
ጅቦቹ ተማሪ አይንኩም ቢሆንም ግን መጠንቀቅ ይኖርባቹሃል ፤ ምናልባትም ብቻችሁን ሁናቹህ አስራ ምናምን ጅቦች ስታዩ እንደኔ ጀግና ብትሆኑ እንኳ ትሸበራላቹህ።
የፍሬሾች ዶርም ደግሞ ትንሽ ራቅ ስለሚል ጠንቀቅ በሉ።

@fresh_astu
@fresh_astu
second year ተማሪ የሆነው የቻናላችን አባል ስለ #Astu ምግብ Schedule ጠይቄው ነበር።
ይሄን ልኮልናል😁

#ክክ_ወይ_ምስር_ወይ_ሽሮ ግን የ ASTU Uniform ናት ዴ😄

#ሰኞ
ጠዋት: ፍርፍር
ምሳ: ሩዝ በስጋ
እራት: ክክ ወይ ምስር ወይ ሽሮ

#ማክሰኞ
ጠዋት: ማኮሮኒ
ምሳ: ከክ ወይ መሰር ወይ ሸሮ
እራት: therefore

#ረቡዕ
ጠዋት: ፍርፍር
ምሳ: ክክ ወይ ምስር ወይ ሽሮ
እራት: ሽሮ በ አልጫ ድንች ወጥ

#ሀሙስ
ጠዋት: ፍርፍር
ምሳ: ክክ ወይ ምስር ወይ ሽሮ
እራት: therefore

#አርብ
ጠዋት: ፍርፍር
ምሳ: ክክ ወይ ምስር ወይ ሽሮ
ራት: ሸሮ በ ደነች አልጫ ወጥ

#ቅዳሜ
ጠዋት: ሩዝ
ምሳ: ክክ ወይ ምስር ወይ ሽሮ
ራት: ክክ ወይ ምስር ወይ ሽሮ

#እሁድ
ጠዋት: ፍርፍር
ምሳ: ፓስታ
እራት: ክክ ወይ ምስር ወይ ሽሮ።

ጠዋት ሁሌ ሻይና ዳቦ ከነገርኩሽ ውጪ አሉ ቀንና ማታም ዳቦ በብዛት ተጨማሪ አለ።

@fresh_astu
@fresh_astu
Forwarded from , (zoog)
📌 AASTU እና ASTU ለምን ብዙ ተማሪ መግባት ይፈልጋል


📚 በተለይ አዲስአበባ የሞት ሽረት ትግል ነው የሚደረገው ለምንድነው ያላችሁን ልጆች በተቻለ አቅም ያለውን ዕድል እናያለን ።


📌 1. ረብሻ ወፍ አዳማ አንዳንዴ ቢንገጫገጭም አዲስአበባ ግን ከአፄው አብዮት በኅላ ረብሽ የናፈቀው ግቢ ነው ያለው ። በቃ አርፈህ ትማራለህ ፥ ስጋት የለ ጭንቀት የለ... ግሬድ እና ትምህርትህን ብቻ እያሰብክ መቸከል ነው ።

📌 2. ለብዙ ነገሮች ቅርብ መሆን ...በተጓዳኝ ስራ መስራት ብትፈልጉ ፤ ችሎታችሁ በትምህርት ማዳበር ብትፈልጉ ..ኢቨንት መሳተፍ ብትፈልጉ ...ለምንም ምቹ የሆነ circumstances አለ .!

💡 አንድ ድምፀ መረዋ ተማሪ ዘፈን መስራት ቢፈልግ ጎንደር ከሆነ ይከብዳል ምክንያቱም ከጎንደር ራሱ ሸገር እየመጡ ስለሚዘፍኑ ነገር ግን አዲስ አበባ የጊልዶን ስልክ ማግኘት አይከብድም ። ወይም ፊልም መስራት የምትፈልጉ ከሆነ የተለያዮ ስልጠናዎች ዋና ከተማ ላይ ይገኛሉ ። ትምህርት ቤቶች አሉ መማር ትችላላችሁ ። ስራ ብትፈልጉ ያደገች ከተማ ስለሆነች በእውቀታችሁ መስራት ትችላላችሁ ። ኤዲቲንግ ጎበዝ ከሆናችሁ ምናምን ስራ አይጠፋም ።

💡የተለያዮ ስልጠናዎች እንዲሁም ኢቨንቶችም ቅርብ ናቹሁ አሁን ወልቂጤ ቢደርስህ ትያኣትር አይደለም ሲኒማ የለም ...ነገር ግን በአዲስ ሁሉም አለ ። በፍላጎታችሁ ልክ የምትኖሩበት ከተማ ስለሆነ ምንም ብትፈልጉ acess እጦት የለም ።

📌 3. ለcv የሚሆን ሰርተፍኬት ፍለጋ ፤ ዘንድሮ አሸን ዲግሪ ሀገሪቷን አጥለቅልቋታል ስለዚህ ነጥብ መስቀል ብቻ ለስራ መፍትኤ አይደለም የሚያማልል CV መያዝ ይጠበቅብናል ። ማለትም የተለያዮ ስልጠናዎች ፤ የህይወት ክህሎት ወርክሾፖች ምናምን ...አጫጭር ኮርሶች ፥ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ፤ በመሳተፍ የተሳትፎ ሰርተፍኬት ይሰጣቹሃል ። ይሄም በድርጅቶች ተፈለጊ እንድትሆኑ ይረዳቹሃል ። በdistance ወይም weekend በመማር ሁለተኛ ዲግሪም መያዝ ትችላላችሁ ። ይሄ ስራ ለመቀጠር በጣም ወሳኝ ነገር ነው በውድድር አለም የተሻለ ሆኖ መገኘት ግድ ነው ።

📌 4. የስራ ነገር ...ሳትንቅ ከሰራ ስራ በሽ የሆነበት ሀገር ነው ። ጨላ ላለመቸገር ...ሸገር የሚሞሉ ደሞሞም አዳዲስ ነገሮች የሚሞከርባት እና የሚበለፅግባት ከተማ ነች ሸገር እና አዳማ ...እና ወዘተረፈ..

📌 5. ለመፍታታት ...ኮንሰርት ቢዘጋጅ ...የአሽኮለሌ ፕሮግራሞች..መዝናዎች በሽ ናቸው ። ታዲያ እነዚህ ሁሉ ነገር ተመቻችተው ዕድሉን መሞከር ምን ጣጣ አለው ።


ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !
======================
📚 JOIN : @z_campus
📚 JOIN : @z_campus
======================
Forwarded from , (zoog)
📌 ASTU እና AASTU ለምትፈተኑ መረጃ ❗️

📚 ፈተናው ለናቹራል ተማሪዎች ያለምደባ አዳማ እና አዲስአበባ ዮኒቨርሲቲዎች ለመግባት ይጠቅማል ።


📌 ፈተናው ክብደት

🔎 ፈተናው 30 ጥያቄዎችን በአምስት ትምህርት ይሰጣል ማለትም ፦

📚 ENGLISH
📚 MATHS
📚 PHYSCIS
📚 CHEMSTRY
📚 BIOLOGY

( Civic እና Aptitudes አያካትትም! )

💬 የፈተናው ይዘት ከባድ የሚባል አይደለም የ11 እና 12 የተማራችሁትን ጥያቄ ነው የሚወጣው ፤ የሚሞክር ተማሪ ያልፋል !


📌 ምን ያክል ተማሪ ይወዳደራል

📚 በመግቢያ ፈተናው ለመወዳደር እስከ 10ሺ ተማሪ የሚመዘገብ ቢሆንም ከግማሽ በላዮ ተማሪ ተመዝግቦ በሚሰማው አሉባልታ ምክንያት አይፈተንም ፤ ከተፈተነው ውስጥም አብዛኛው የሚፈልገው ሀገር ባይመደብም ያልፋል !

📚 አምና (2013 E.C) ወደ 5ሺ የሚጠጋ ተማሪ አልፎ ወደ ዮኒቨርስቲዎቹ ለመማር ገብቷል !


ኩረጃ

📚 ፈተና ባለበት ሁሉ ኩረጃ አለ ፥ ነገር ግን ትንሽ ጠበቅ ያለ የፈተና አሰጣጥ ነው ያለው ። ፈተናው በኦላይን ስለሆነ ለመኮረጅ ይከብዳል ። ሁሉም አንድ ኮንፒተር ይሰጠዋል በዛ የራሱን ይፈተናል ።

📌 ባላልፍስ

📚 የመግቢያ ፈተናውን ባታልፉ መንግስት ሌሎች ዮኒቨርስቲዎች ምደባ ያካሂድላቹሃል ፤ ካለፋችሁ እዛው ትቀራላችሁ ካልሆነ ደሞ መንግስት የመዳባችሁ ጋር ትሄዳላችሁ ።


📌 መስፈርቱ

📚 የመግቢያ ፈተናውን ለመፈተን የነጥብ መስፈርት አለው ( በ2013 E.C ) ለኢንጅነሪግ 410 እና ለአፕላይድ 400 ነበር ፤ መስፈርቱን ካሟላችሁ መሞከሩ ጥሩ ነው ።


❤️ መልካም ዕድል ።


ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !
======================
📚 JOIN : @z_campus
📚 JOIN : @z_campus
======================
📌 ስለ ASTU ሙሉ መረጃ !

📌ስለ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተሟላ መረጃ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች

📚 አዳማ የሚማር 2nd year ተማሪ የተናገረው የግድ ማዳመጥ ያለባችሁ ...!

📌 ነጥብ አይሰጥም
📌 Software engenring የለም
📌 ሁለት ዲግሪ ይዞ መውጣት ይቻላል


💭በጣም ብዙ ጥያቄዎች የተመለሱበት ከተመዘገባችሁ የግድ መስማት ያለባችሁ info ..!

1ሜጋባይት ብቻ ነው ። (20 ሳንቲም)
👍1
ASTU ለመግባት ያሰባችሁት ልጆች ማወቅ ያለባችሁት ነገር:-
1.ASTU Elective Course ና free elective course የሚባል ነገር አለ።
Elective course ማለት ለምሳሌ 3ኛ አመት 2ኛ ሴሚስተር ላይ በ CSE 5 course ዎች ሲኖሩ፤እነሱም
1.Data communication and computer networks
2.Operating systems
3.Introduction to AI
4.Elective
5.Elective
Elective:-Web programming
-Software requirement
engineering
-Advanced programming
Elective course የሚለውን ከእነዚህ 3 ምርጫዎች መርጠን እንማራለን ማለት ነው።
Free Elective Course የሚለው ደግሞ በራሳችን ፍላጎትና ምርጫ መርጠን የምንማረው course ማለት ነው ።ለምሳሌ 3ኛ አመት 1ኛ ሴምስተር ላይ ፤
1.Algorithms
2.Probability and random process
3.Fund. of software engineering
4.Computer architecture and organization
5.Free elective
እዚህጋ ከፈለግን Java,C#,Python ደስ ያለንን መርጠን መማር እንችላለን ማለት ነው ።
2.ስለ Apparentship ነው
Apparent የሚወጣው ክረምት ላይ መሆኑን ማወቅ ይኖርባችኋል።ይህ ማለት ሌላ ግቢ ብሆን 4ኛ አመት 1ኛ ሴሚስተር ወይ 2ኛ ሴሚስተር ላይ ሲሆን ወደ ግቢ ስትመለሱ present ታደርጉና grade ይሰጣችኋል፤ASTU ግን ክረምት ላይ ነው የምትወጡትና ምንም grade የለውም pass or fail ነው ።
Internship 3ኛ አመት መጨረሻ ላይ ለ አንድ ወር እና 4ኛ አመት መጨረሻ ላይ ደግሞ ለአንድ ወር ከሁለት ሳምንት ነው ።

========================
Join our channel
========================
@fresh_astu
@fresh_astu
👍2
የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጽን ይመለከታል ፦

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር ከቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለወንድ 293,865 ሴት 250,703 ድምር 544,568 ተማሪዎች የተሰጠ ሲሆን ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በመጀመሪያው ዙር ሳይፈተኑ ለቀሩ ለወንድ 27,979 ሴት 26,456 ድምር 54,435 ተማሪዎች ደግሞ ከጥር 24-27/2014 ዓ.ም በሁለተኛው ዙር ፈተናው ተሰጥቷል። በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ከተመዘገቡት 617,991 ተማሪዎች ውስጥ ወንድ 321,844 ሴት 277,159 ድምር 599,003 (96.9%) ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ችለዋል።

የፈተና እርማቱ ደህንነታቸው አስተማማኝ በሆኑና ከንክኪ ነጻ በሆኑ የማረሚያ ማሽኖች አስፈላጊው የደህንነት ጥበቃ በፌደራል ፖሊስና በሴኩሪቲ ካሜራዎች ታግዞ በጥንቃቄ ተከናውኗል። ከዚህ በተጨማሪም የፈተናዎች ውጤት በትምህርት ዓይነት፣ በትምህርት ቤትና በተማሪ ደረጃ ሰፊ የውጤት ትንተና በማካሄድ የእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት ውጤት ተገምግሟል።

በዚሁ መሰረት የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል ተወስኗል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል። ነገር ግን በተናጠል የፈተና ደንብ ጥሰት የፈጸሙ 141 ተማሪዎች ላይ ከውጤት መሰረዝ ጀምሮ በየደረጃው የተለያየ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።

ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ። ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።

ስለሆነም ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።
1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et
3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot - በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባትና Exam Result የሚለውን በመጫን በመልክት መጻፊያው ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት እና የ ምልክት በመጫን መላክና ውጤታቸው ማየት ይችላሉ።
4) በ9444 የ ኤስ ኤም ኤስ (9444 SMS) ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

(የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ)

፨ለጥቆማ 👇
@atc_newsbot
🔔ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
ለ12ኛ ክፍል የመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል ተወስኗል።

ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።
1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et
3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot - በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባትና Exam Result የሚለውን በመጫን በመልክት መጻፊያው ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት እና የ ምልክት በመጫን መላክና ውጤታቸው ማየት ይችላሉ።
4) በ9444 የ ኤስ ኤም ኤስ (9444 SMS) ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

(የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ)

፨ለጥቆማ 👇
@atc_newsbot
🔔ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
@atc_news @atc_news
@atc_news @atc_news
የ አምና የ ASTU መግቢያ ነጥብ ለጠየቃችሁኝ
የ ዘንድሮ የ ASTU መግቢያ ነጥብ ስንት እንደ ሆነ ገምቱት እስቲ
በትክክል ለ ገመተ:climb ur hand😂😂😂
የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡት እነማን ናቸው?

° ተማሪ አላዛር ተካ (ወ)
ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ሚኒሊክ I ሳይንስ ሼር ካምፓስ (አዲስ አበባ)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 659
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 563

(🎯 ሒሳብ 100/100 ፤ 🎯 ፊዚክስ 100/100)
-------------------------------

° ተማሪ ተመስገን ገብረወልድ (ወ)
ሊቃ ትምህርት ቤት (ዎላይታ)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 651
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 555

(🎯 ሒሳብ 100/100 )
-------------------------------

° ተማሪ ሙሴ ፊሊጶስ (ወ)
ሊቃ ትምህርት ቤት (ዎላይታ)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 647
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 551
-------------------------------

° ተማሪ ኮኬት ተስፋዬ (ወ)
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት (ODA)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 643
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 548

(🎯 ፊዚክስ 100/100 )
-------------------------------

° ተማሪ አብዱላዚዝ ዜኑ (ወ)
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት (ODA)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 644
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 547
-------------------------------

° ተማሪ ሲፈን ፊጣ (ሴ)
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት (ODA)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 639
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 542

(🎯 ሒሳብ 100/100 )

NB፦
- በ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሲቪክ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ እንደማያገለግል መገለፁ ይታወቃል።
- መረጃው ከተላኩልን መልዕክቶች የተሰበሰበ መሆኑና የጸና መረጃ አለመሆኑ ከግምት ውስጥ ይቀመጥ።
Credit : Ethio Students
👍1
#NEAEA

" ይሄ አዲስ ውሳኔ አይደለም። ለዓመታት ሲሰራበት የቆየ ነው። ማንኛውም ተማሪ ለማለፍ ከግማሽ በላይ ውጤት ማምጣት አለበት " - አቶ ተፈራ ፈይሳ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ከሆነ ሰዓት ጀምሮ ከተማሪ ወላጆች እንዲሁም ከተማሪዎች በርካታ ጥያቄዎች ደርሰውን ተመልክተናል።

ከጥያቄዎቹ መካከል ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገብቶ ለመማር የተላለፈው 50% ማስመዝገብ ውሳኔ ከነበርንበት ሁኔታ አንፃር፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ የጦርነቱ ጫና ተዳምሮ ትክልል አይደልም ይህ ሊታይ ይገባል የሚል ነበር።

የተላኩትን ቅሬታዎች በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአገር አቅፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አቅርቦ ምላሽ አግኝቷል።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ " ማንኛውም ተማሪ ብሔራዊ ፈተናውን ለማለፍ ቢያንስ 50 በመቶ ውጤት ሊያመጣ እንደሚገባ " ገልጸውልናል።

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው ለመማር የተፈተኗቸው የትምህርት አይነቶች አጠቃላይ አማካይ ውጤት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

" ይሄ አዲስ ውሳኔ አይደለም። " ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ " ለዓመታት ሲሰራበት የቆየ ነው። ማንኛውም ተማሪ ለማለፍ ከግማሽ በላይ ውጤት ማምጣት አለበት " ብለዋል።

ከተማሪዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን እየተቀበሉ መሆኑን የገለጹት ም/ዋና ዳይሬክተሩ ፤ አጠቃላይ አማካይ ውጤታቸው ከ300 በታች ያመጡ ተማሪዎች ቁጥር ገና አለመታወቁን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

የዩኒቨርሲቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ የመግቢያ ነጥብ ወደፊት በትምህርት ሚኒስቴር የሚገለጽ መሆኑም ታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#ASTU #AASTU

የኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ አውጥተዋል።

የመመዝገቢያ መስፈት የሲቪክስ ትምህርትን ሳይጨምር የስድስት ትምህርት ድምር ውጤት ነው።

• ለታዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤ/ጉሙዝ ፣ ጋምቤላ)

- ኢንጂነሪንግ ለወንድ 395 ለሴት 390
- አፕላይድ ሳይንስ ለወንድ 385 ለሴት 380

• ለሌሎች ክልሎች

- ኢንጂነሪንግ ለወንድ 400 ለሴት 395
- አፕላይድ ሳይንስ ለወንድ 390 ለሴት 385

የምዝገባ ጊዜው ከየካቲት 21 /2014 ዓ/ም እስከ የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ሲሆን ምዝገባው የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ከለሊቱ 6 ሰዓት ይጠናቀቃል ተብሏል።

የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት www.aastu.edu.et እና www.astu.edu.et ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

ፈተናው መጋቢት 7/2014 ዓ/ም ይሰጣል።

@fresh_astu
@fresh_astu