የጥያቄዎቻችሁ መልስ
19.8K subscribers
358 photos
78 videos
246 files
314 links
የዚህ ኦርቶዶክሳዊ ገጽ ዋና ዓላማ የወጣቱን ጥያቄ መመለስ ነው። ወጣቶች ማንኛውም በሕይወታቸው የገጠማቸውንም ይሁን መንፈሳዊ ጥያቄ በሚረዱት መልክ መልስ ይሰጥበታል

YouTube
https://www.youtube.com/channel/UCPLJimNlqTFBnlbsh_vccgg


ለጥያቄዎችና ለአስተያየቶች
@AbuNak
@Rhripsime
Download Telegram
ከመፅሐፈ ምስጢር የተነበበ
ምዕራፍ ፲፯
(የዓርብ ስቅለት ምንባብ የዘጠኝ ሰዓት ምነባብ)
@APOSTOLICsuccession
ከሕማማት መፅሐፍ የተነበበ
ከምዕራፍ ፭
"የሠላሳ ሦስት ዓመታት ኀዘን" እና
"ሠቆቃወ ድንግል "
"ድንግል ሆይ የራሔል እና የልያ ልጆች ልጅሽን በሰቀሉት ጊዜ በእሳት እንባ ለተቃጠሉት ጉንጮችሽ ሰላምታ ይገባል"

"መልክዐ ማርያም ለመላትህኪ"
@APOSTOLICsuccession
ማክፈልማ ግድ ነው የምን ምክንያት መደርደር ነው?

ሁላችንም ወጣቶች ማክፈል አለብን
@ApostolicSuccession
Forwarded from የጥያቄዎቻችሁ መልስ (አቡ (ወንዴ))
ሰላም ሰላም ተወዳጆች እንዴት ናችሁ?

ከዚህ ቀደም በቻናላችን አመታዊ በዓል ላይም በተለያየ ወቅት በውስጥም ሲደርሱን ከነበሩት በርካታ አስተያየቶች ውስጥ አንዱ ይህንን መንፈሳዊ ቻናል ይህንን መንፈሳዊ ህብረት በማስተባበር የተለያዩ በጎ ምግባራትን እንድናከናውን የተሰጠ ነበር። ብዙዎችም በውስጥ ልትረዱ የምትችሉት የበረከት ሥራ ካለ እንድናሳትፋችሁ በተደጋጋሚ ትጠይቁን ነበር። እኛም ብዙ ጊዜ ከሳንቲም ጋር የሚያያዝ ነገር መጥፎ ጎን ስላለው ፈርተን እንዲህ አይነት ነገሮችን አቅደንም ጠይቀናችሁም አናውቅም።

ዛሬ ላይ ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ በዚሁ ቻናልም መንፈሳዊ ፍሬ ምክንያት በአካል ተሰባስቦ የተቋቋመ መንፈሳዊ ጽዋ ማኅበር እንዳለ በቅርቡ አሳውቀናችሁ ነበር። ስለዚህ የመድኃኔዓለም ጽዋ ማኅበር ግሩም ዓላማዎችና ዕቅዶች ከዚህ ቀደም በሰፊ ማብራሪያ ስለነገርናችሁ መድገም አያስፈልግም። በዚህ ጽዋ ማኅበር የሚደረጉ በጎ ምግባራትንም አስመልክቶ ባለፈው የድምፅ ማብራሪያ ላይ እንደተናገርነው ለደካሞች ሥጋዊ መብልን ምድራዊ ርዳታን ብቻ ሳይሆን የነፍስን ሰማያዊ ምግብም የመመገብ ወደ መንፈሳዊ ማንነትና ጥንካሬ የማምጣት የማጥመቅና የማቁረብ ዓላማዎችንም እንደያዘ አጫውተናችሁ ነበር። ታድያ ግን የተሰባሰበው የጽዋ ማኅበር አብዛኛው ተማሪ ስለሆነ እናንተንም ሌሎችንም በበረከት ሥራው ላይ ማሳተፍ ግድ ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔር ቢፈቅድና ቢረዳን የአጭር ጊዜ እቅዶቻችን
:- በጾም መፍቻ ወቅት በዳግመ ትንሳኤ ለበርካታ ነዳያን ምግብን ከወንጌል ጋር ልናደርሳቸው
:- እንዲሁም በዚሁ የጾም ፍቺ የዳግመ ትንሳኤ ቀጣይ ሳምንት ደግሞ በማረሚያ ቤት በመሄድ ለታሰሩት መጽናናትን ልንሰብክና ልብስም ምግብ ልንመግባቸው
:- እንዲሁም ሦስት እጅግ ችግር የገጠማቸው የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን በቻናልነው አቅም ልናግዝ ዕቅድ አለን።

ሌላኛው ክረምት ላይ ያቀድነው ይቆያችሁና (ጊዜው ሲቀርብ የሚያስፈልጉንን ሁሉ እናሳውቃችኋለን) እነኚ ግን የአጭር ጊዜ እቅዶቻችን እንዲፈጸሙ እዚህ ካሉት ተማሪዎች የሚሰበሰበው ሠላሳና ሃምሳ ብር በቂ ስላልሆነ በቻላችሁት እናንተም በበረከት ሥራው ብትሳተፉ ለእናንተው ነውና ዋጋ የምትችሉ ሁሉ ከራሳችሁም እንዲሁም በበረከት ሥራው መሳተፍ ከሚችሉ ከምታውቋቸው ሰዎችም ሼር በማድረግና በማስተባበር ይህን የበረከት ሥራ እንድትሳተፉ በእግዚአብሔር ሥም በድንግል ማርያም ሥም ( "በጥያቄዎቻችሁ መልስ ቻናል ሥም"ም ) እንጠይቃችኋለን።

የመድኃኔዓለም ጽዋ ማኅበር በቤተክርስቲያን የተመዘገበ የቤተክርስቲያን አባት ያለው ሲሆን የባንክ አካውንቱም የግለሰብ ሳይሆን ሁለት ሙሴዎች ( መሴ እና ግልገል ሙሴ) እንዲሁም እኔም ሆነን በሦስት ሰዎች የተከፈተ ነውና ለመሳተፍ እንዳትሰጉ ለማለትም እንወዳለን። የሚሰበሰበው ከዚህናው የአጭር ጊዜ የበረከት ሥራ ቢተርፍ እንኳን ለቀጣዩ የክረምት እጅግ ትልቁ እቅድ የሚቀመጥ ስለሆነ ያንን በማሰብ እናንተ ብቻ በቻላችሁት በትንሹም ብቻ ከበረከቱ ተሳተፉ ለማለት እንወዳለን። አካውንቱን ከታች ፎቶ አንስቼ አስቀምጥላችኋለሁ። ልታወሩን ደግሞ ያው ከፈለጋችሁ በ @AbuNak ታገኙኛላችሁ። በተለይ በበረከት ሥራው የምትሳተፉ የክርስትና ስማችሁን በውስጥ ብታሳውቁን እጅግ መልካም ነው።

@ApostolicSuccession
ሰላም ለእናንተ ይሁን ተወዳጆች ለበዓሉ መዝሙር፣ግጥም፣የእንኳን አደረሳችሁ እንዲሁም ስለ ትንሳዔው የተነገሩ ብሂለ ዓበው እንዲሁም ሌሎች መንፈሳዊ ይዘታቸውን ያለቀቁ መርኃግብሮች ያሏችሁ ላኩልን እና አብረን የጌታችንን ቅድስት ውድስት ክብርት ትንሳዔውን አብረን በፍቅር በመማማር እናሳልፍ🙏
የምትልኩበት መንገድ
@Aklil1
@Abunak
@Rhripsme
@Ashu2927
ላይ ላኩልን
ሰሙነ ሕማማት ዕለተ ቅዳሜ
:- ቀዳሚት ስዑር

ማክፈል ካልቻልኩስ?
@ApostolicSuccession
በስመአብ ወ ወልድ ወ መንፈስቅዱስ ፩ አምላክ አሜን
ክርስቶስ ተንስዐ እሙታን
በዐብይ ኃይል ወስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እም እዝየሰ
ኮነ
ፍስሀ ወ ሰላም
"ከሲዖል እጅ እታደጋቸዋለሁ ከሞትም እቤዣቸዋለሁ ሞትሆይ ቸነፈርህ ወዴት አለ? ሞትሆይ ማጥፋትህ ወዴት አለ? ርህራሄ ከዓይኔ ተሰወረች" ሆሴ ፲፫፡፲፬

"እንደተናገረ ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም" ማቴ ፳፰ እስከ ፍፃሜው ይነበብ

"እርሱ ግን አትደንግጡ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ ተነስቶአል በዚህ የለም" ማር ፲፮ እስከ ፍፃሜው ይነበብ

"ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ እንዲህ አሉአቸው ሕያውን ከሙታን ስለምን ትፈልጋላችሁ? ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም" ሉቃ ፳፬ እስከ ፍፃሜው ይነበብ

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርት ውድስት ቅድስት በዓለ ትንሳዔው በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን

"ለመስቀልከ ንሰግድ ወለ ትንሳዔከ ቅድስት ንሴብህ ኩልነ ይእዜኒ ወዘልፈኒ"

ጌታዬ ሆይ ክቡር የሚሆን የመቃብርህ ጠባቂዎች ከድንጋፄ የተነሳ የትንሳዔህ ግርማ የገለባበጣቸው በሦሥተኛው ቀን ከሙታን ተለይተህ ለተነሳኽው ትንሳዔህ ሰላምታ ይገባል" (መልክዐ ኢየሱስ ለትንሳዔከ ቀዳማይ)

"ስለፍፁም ሃይማኖት በክብር ለሞቱ ቅዱሳን ሁሉ የትንሳዔያቸው መተማመኛ ለሆነው ትንሳዔህ ሰላምታ ይገባል"(መልክዐ ኢየሱስ ለትንሳዔከ ካልዕ)

"በአርብ ሙታን እና ህያዋን በድኅነታቸው ተደሰቱ በእኁድ ደግሞ በህይወት ያሉ አረጋገጡ እናም ትንሳዔያቸው በክርስቶስ ስጋ እንደሆነ አወቁ" (የኮፕቲክ ቤተክርስቲያ የመጋቢት፳፱ ስንክሳር )

"በእውነት እኛ ኦርቶዶክሳውያን የዘመናት ንጉስ ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ ብለን እናምናለን ከእኛ ንጉስ አማኑኤል ከሞት መነሳት በኋላ ሁሉን ደስታ እና ሀሴት እግዚአብሔር"(የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የበዓለ ሃምሳ የሌሊት ምስጋንና)

"የእኛ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እና ጥበቡን እኛ ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ ብለን እናመሰግነዋለን እናም እሱ እንደተናገረው ነብያትም እንደተናገሩት በመቃብር ተቀበረ ከሦስት ቀንም በኋላ ተነሳ" (የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የበዓለ ሃምሳ የሌሊት ምስጋና)

"የደስታ እናት ድንግል ማርያም ተደሰቺ በእውነት ያንቺ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷልና ዛሬ ሁላችን እንደሰት ደስተኛም እንሁን ምክንያቱም የንጉሦች ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷልና"(የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የበዓለ ሃምሳ የሌሊት ምስጋና)

"ጥበበኛው ሉቃስ እና ተወዳጁ ዮሐንስ ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷልና በእውነቱ ወንጌልን ስበኩ ክርስቶስ ሆይ የማጠልቅ ፀሀይ ሆይ ና እኛም ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተነስቷል ብለን እናመስግንህ"(የኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የበዓለ ሃምሳ የሌሊት ምስጋና)

" ሞት በሞት ተያዘ ክርስቶስ ከሙታን ተነሳ እሱ በመቃብር ሆኖ ህይወትን ሰጠ"(የምስራቅ ኦርቶዶክሳውያን ስንክሳር የፋሲካ ስንክሳር)

"ይሄ የትንሳዔ ቀን ነው ሁላችንም በበዓሉ እናብራ(እንድመቅ) ሁላችንም እርስ በእርስ እንተቃቀፍ ሁላችንም የጠላነውንም ቢሆን እንኳ በትንሳዔው ይቅር እንበል ወንድሞቼ ተባብለንምእንጠራራ"(የምስራቅ ኦርቶዶክሳውያን ስንክሳር የፋሲካ ስንክሳር)

"ሞትሆይ መያዝህ የትአለ? መቃብር ሆይ ድል መንሳትህ የትአለ? ክርስቶስ ሲነሳ እና ሲነግስ ከስልጣንህ ተሻርክ፣ክርስቶስ ሲነሳ አጋንንት ወደቁ፣ ክርስቶስ ሲነሳ መላዕክት ተደሰቱ"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

"ትላንት ከእርሱጋ ተሰቅዬ ነበር ዛሬ ከእርሱጋ እከብራለሁ ትላንት ከእርሱጋ ሞቼ ነበር ዛሬ ከእርሱጋ ህያው እሆናለሁ ትላንት ከእርሱ ጋ ተቀብሬ ነበር ዛሬ ከእርሱ ጋር እነሳለሁ"
(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናንዙ

"ምድር በክርስቶስ ደም ታጥባለችና ፋስካን ታደርጋለች"
(ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊ)
ለሁላችሁም መልካም የፋሲካ በዓል ወንድሞቼ እኅቶቼ።
@APOSTOLICsuccession
ይሄ ቦታ ጌታችን ኢየሱስ ተቀብሮበት የነበረው ቦታ ሲሆን ቦታው ላይ ክርስቲያኖችበየዓመቱ የጌታን ትንሳዔ ያከብሩበታል።
በቦታው ላይም ለዓመታት ሳይቋረጥ ወደፊትም የሚቀጥል ተዓምር ይፈፀምበታል ምንድነው አትሉም ምን መሰላችሁ በጌታ ትንሳዔ የታየውን ብርሃን ለማሰብ ሻማ ሊያበሩ ሲሉ መጀመሪያ ፓትሪያሪኩ ከጌታ መቃብር ያልበራ ሻማ ይዞ ይገባና ጸሎት አድርጎ ሲጨርስ ብርሃን ከሰማይ ወርዶ ሻማው መቀጣጠል ይጀምራል ይሄን ጊዜ የተቀጣጠለውን ሻማ ፓትሪያሪኩ ወደውጭ አውጥቶ በመቅደሱ ለተሰበሰበው ምዕመን ሁሉ ያሰራጩታል።
ምዕመናኑም በታላቅ ደስታ እና ፍቅር ይሄንን ቅዱስ እሳት በያዘው ሻማ ይቀባበሉታል።
የጌታንም ትንሳዔ በፍቅርና በአንድነት ያከብራሉ።
@APOSTOLICsuccession
ስለ በዓለ ትንሳዔ መንፈሳዊ ግጥም በእኅታችን ፅጌማርያም
@APOSTOLICsuccession
እኛ እኮ ምስኪን ነን የተሰኘ ከአንድ እኅታችሁ የተላከ መንፈሳዊ ግጥም
@APOSTOLICsuccession
መንፈሳዊ ግጥም በእኅታችን ፅጌ ማርያም
@APOSTOLICsuccession
እንኳን አደረሳችሁ ሰዎች😊

ደሞ ደሞ ደሞ be Careful እንዳንጠላ እሺ? ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉት
@ApostolicSuccession
Forwarded from ማኅሌት ሚዲያ
+++##ትንሣኤን_በውድቀት##+++

በዓለ ትንሣኤ ከዐበይት በዓላተ እግዚእ መካከል ነው። ይህን በዓል የክርስቶስን ነገረ ትንሣኤ በማሰብና እርሱ በተነሣበት ጊዜ እንዳሉ አድርጎ ማክበር በእጅጉ ተገቢ ነው። በጣም አስደናቂውና አሳፋሪው ነገር፥ የክርስቶስን በዓል ከክርስቶስ ውጪ ኾኖ ማክበር ነው! በዓለ ትንሣኤን በዘፈን እናክብር የሚሉ ለበዓል ብለው ዘፈን የሚዘፍኑና የሚያዘፍኑ ከዘፋኝነት ኃጢአታቸው በተጨማሪ ክርስቶስን በፍጹም መጻረር ነው። ከትንሣኤው ብርሃን ይልቅ የዘፈንን ጨለማ መምረጥ ነው።

+++ +++ ++++ ++++ +++++++

የትንሣኤን በዓል በዘፈን ማክበር ማለት ክርስቶስን መናቅና፥ አምላክነቱን ቸል ማለት ነው። አንድ መንፈሳዊ ሰው እንኳን የራሱን የልደት ዕለት በመዝሙር ማክበር ይፈልጋል፥ እንግዲያውስ የፍጥረታት ፈጣሪ ሞትን ድል አድርጎ በተነሣበት ዓለት በዘፈን ሊከብር ይችላልን? ለመኾኑ በዓሉ የማን በዓል ነው? የክርስቶስ በዓል አይደለምን? ታዲያስ የአምላካችንን በዓል እንዴት ነው የዘፈንን መሥዋዕት በመሠዋት ልናከብር የምንችለው? የበዓሉ ባለቤት በሚፈልገው መንገድ የማናከብር ከኾነ ወይ እንተው! ካልኾነ የባለ ቤቱን በዓል ከባለ ቤቱ ፈቃድ ውጪ የምናከብር አይምሰለን።

+++ +++++ ++++ ++++ +++++

ትንሣኤን በዘፈን አከብራለው ማለት ክርስቶስን በዲያብሎ አመሰግናለሁ፥ አንድም ክርስቶስን በኃጢአት አከብራለሁ እንደ ማለት ነው። ክርስቶስ ጻድቀ ባሕርይ ስለ ኾነ በኃጢአት ይከብር ዘንድ አይችል። በመኾኑም በትንሣኤ ዘፈንን መስማት ወይም መዝፈን ሰይጣንን ከክርስቶስ ጋር እንደ ማወዳጀት ነው። በሌላ አባባል ክርስቶስ ሰይጣንን ድል አላደረገም፥ ሰይጣንም ድል አልተደረገም፥ እኩል ኾነዋል እንደ ማለት ነው። እንግዲህ ከዚህ የበለጠ ምን ጽርፈት ወይስ ስድብ አለ?

+++ ++++ ++++ ++++ +++++

በትንሣኤ ዕለት የዘፈን ኮንሰር ማዘጋጀት ማለት በቀጥታ አይሁድን መምሰል ነው። አይሁድ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱን እያወቁ፥ ተሰርቋል ብለው የውሸት ወሬ እንዳስወሩና መነሣቱን እንዳጠራጠሩ፥ የዘፈን ኮንሰርትም ማዘጋጀት የክርስቶስን የትንሣኤ ብርሃን ለመጋረድና ሰውን በትንሣኤ በዓል ከትንሣኤ ውጪ ለማድረግ የተሠራ ክፉ ወጥመድ ነው። ዘፈንን የሰውን ልብ የመማረክና ወደ ስሜታዊነት የመክተት ኃይሉ ከፍተኛ ነው፥ ትንሣኤው ደግሞ ከሥጋዊነትና ከስሜታዊነት አውጥት ወደ መንፈሳዊነት የማሸጋገር ታላቅ ኃይል አለው። እንግዲህ በትንሣኤ ዘፈንን ማቅረብ ወይም መስማት ማለት ትንሣኤውን ለማስረሳት ወይም ስሜታዊ ለማድረግ መጣር፤ መፈለግና መምረጥ ማለት ነው።

+++ ++++ +++ +++++ +++++

በትንሣኤ ዘፈን ማቅረብ ማለት “ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይኾናሉ" ለሚለው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳብ ፍጻሜ መኾን ማለት ነው። 2ጢሞ 3። ድል ካደረገው ከክርስቶስ ይልቅ ተሸናፊውን ዲያብሎስን መምረጥ ነው። በሌላ አባባል ክርስቶስ ኾይ እኔ የምፈልገውነሰ ተቀብል እንጂ አንተ የምትፈልገውን አትጠይቀኝ እንደ ማለት ነው!! በዚህ ድርጊታችን ሳናውቀውም ቢኾን የክርስቶስን ንጹሐ ባሕርይነት እንጠራጠራል። መስማት የሚገባን እኛ ስንኾን እርሱን ስማን እንለዋለን። ይህ ኹሉ ትንሣኤውን ባልተነሣ አስተሳሰብ ከመያዝ የሚመጣ ጽኑ ሕማም ነው።

++++ +++++ ++++ +++++++

በትንሣኤ ዘፈን መስማት ማለት በክብር ቀን የሞተ መሥዋዕት ማቅረብ ማለት ነው። አቤል ተጨንቆና መርጦ ያማረውን መሥዋዕት በማቅረብ የእምነት ትምህርት ቤት ኾነ (The School of Faith)፤ ቃየን ግን በቸልተኝነትና በፍልስፍና የማይረባውን መሥዋዕት በማቅረቅ የምድራዊ ዕውቀት ትምህርት ቤት ኾነ (The School of Knowledge)። ስለዚህ በትንሣኤ ዘፈንን መሠዋት ማለት በቀጥታ የቃየንን ዘር ማርባት ማለት ነው። ከሕይወት ይልቅ ሞትን፣ ከእምነት ይልቅ ፍልስፍናን፣ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን፣ ከመዳን ይልቅ ጥፋትን፣ ከሰላም ይልቅ ኹከትን፣ ከደስታ ይልቅ ኀዘንን፣ ከእውነት ይልቅ ውሸትን መምረጥና መውደድ ነው።

++++ +++++ ++++ ++++++++

በትንሣኤ ዘፈን መዝፈን ማለት ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ከማለት ይልቅ ዘፈን ከሞት ተነሣ (መዝፈን ተወደደ) እንደ ማለት ነው። አሰሮ ለሰይጣን ከሚለው ይልቅ እውነተኛን ምስጋና አሰረ፥ አግአዞ ለአዳም ከማለት ይልቅ ዘፈን ይዘፈን ዘንድ ተፈቀደ እንደ ማለት ነው። ይህም ማለት ድኅነተ ሰብእ ቀረ በሰው ላይ ዘፈን ተሾመ ማለት ነው። የፍቅርን አቅጣጫ ከእግዚአብሔር ይልቅ ወደ ዘፈን ማውረድ ነው። እግዚአብሔርን ከማየት ይልቅ ዘፈንን ማየት ነው!! እንግዲህ ይህ ኹሉ ወድደን ፈቅደን የምንገባበት የባርነት ሕይወት ነው። ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሣውን እኛን ለማክበርና፥ ሰይጣን ከጣለን ጉድጓድ አውጥቶ የትንሣኤ ማማ ላይ ለማስቀመጥ ነው። እኛ ግን ካነሣን ይልቅ የሚጥለንን በመምረጥ ከቀደመው ወደ ሚበልጥ ገደል ውስጥ በዘፈን በኩል መግባትን ወደድን። ዘፈንን ወድደን ክርስትናችንን ጠልተን፥ በተመስጦ የሚከበረውን በዓል በጭፈራ ማድረጋችን በሕማማት ጊዜ እያስመሰልን እንጂ ክርስቶስን እያየነው እንዳልነበረ ያሳብቅብናል። ተወዳጆቼ ሆይ የዚህ ኹሉ ዋናው ምክንያት የኃጢአትን ጣዕም ከጸጋ ጣዕም ይልቅ በደንብ መቅመሳችን ነው። ኃጢአትን በላናት ጠጣናት፣ ለበስናት ወደድና፣ በእርሷ ውስጥ ገባን እርሷንም በእኛ ሰውነት ውስጥ አሠለጠንናት። ስለዚህም በቀላሉ ድል ተደረግን። እንግዲህ ቸሩ አምላክ ከገባንበት ገደል አንሥቶ ወደ ሰብአዊነት ክብር ከፍ ያድርገን አሜን!!

Dn yohannis getachew
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንዴት ያለ ልብን የሚሰብ ጥዑም ጸሎት ነው? የእናቶቻችን የእምነት ጸሎት ሁላችንንም ይጠብቅ
@ApostolicSuccession