Africa medical students councils official page
540 subscribers
122 photos
11 videos
24 files
44 links
Dear students
This channel helps you to get Books,Videos and Pictures which are reliable to the medical courses we are taking and aid us to get credible news about our college.which also promote extra academic performance of student's
👉 @AMCstudentsbot
Download Telegram
ሰበር ዜና

11ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ገባኤ
እንደተጠበቀው
ዶ/ር አብይ አህመድን የድርጅቱ ሊቀመንበር እንዲሁም
አቶ ደመቀ መኮነን ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ ሾሟል።
የ2011 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ በትምህርት ፍኖተ- ካርታ ውይይት ምክንያት #መራዘሙን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ-ካርታ በሚደረገው ውይይት ምክንያት የ2011 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የሚኒስቴሩ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሮ #ሀረግ_ማሞ አስታውቀዋል።

መንግሥት በቅርቡ አዲስ ባዘጋጀው ረቂቅ የትምህርት ፍኖተ-ካርታ ላይ የተጀመረው ውይይት ላይ ተጨማሪ ግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት ስለሚደረግ ቀደም ብሎ ተላልፎ የነበረው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥሪ መራዘሙን ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ከመምህራኖቻቸው እና ከአስተዳደር ሠራተኞቻቸው ጋር በረቂቅ ፍኖተ-ካርታው ላይ ውይይት አድርገው ሲያበቁ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ አንስቶ እንደ የዩኒቨርሲቲዎቹ መርሀ-ግብር የተማሪዎች መግቢያ ጥሪ ይደረጋል ተብሎ የቆየ ቢሆንም ውይይቱ እየተካሄደ በመሆኑ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ባለፉት ሁለት ወራት ውይይት ሲደረግበት የቆየው የትምህርት ፍኖተ-ካርታ ረቂቅ ጥናት ግብዓት ማሰባሰብ ሂደት ከአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማኅበረሰብ አባላት ጋርም በዛሬው ዕለት በመላ አገሪቱ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

በመሆኑም ውይይቱ ሲጠናቀቅ በማዕከል በኩል ለሁሉም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች #ጥሪ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በአገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀው የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ያለመ ሲሆን ለተግባራዊነቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር #ውይይት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል።

ምንጭ፥ኢዜአ


@AMCs
በኢፌዴሪ ጤና ጥበቃ ስር የሚገኙ አምስት የፌዴራል ሆስፒታሎች አዳዲስ ስራ አመራር የቦርድ ሰብሳቢዎችን እናስተዋውቃችሁ

1. ክብርት ዶ/ር ሂሩት ወልደማሪያም የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር - አማኑኤል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

2. ክቡር ዶ/ር ጥላዬ ጌጤ
የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር - ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ

3. ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ከፈለ የትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ - አለርት የህክምና ማዕከል

4. ክብርት ዶ/ር አየለች እሸቴ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ - ኢካ ኮተቤ ጠቅላላ ሆስፒታል

5. አቶ አህመድ ቱሳ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ - ቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ::
#እንደምነሽ #ሸገር

በውቀቱ ስዩም ከአሜሩካ

እንደምነሽ ሸገር የቤት አከራዬ የጋሽ ጣሰው አገር የምትተከዪ የምትነቀዬ የዘመቻ ድንኳን
ብጉርና ችግር ከአባቴ ወርሼ ብኖርብሽ እንኳን
የማልቀያምሽ ሁሌ የማልምሽ
ኦ ማይ ጎድ ይመስገን እኔ እንዳለሁ አለው
ግማሽ እሩዝና ግማሽ ጤፍ በልቼ
አዋጅ እና ዜና ከአደባባይ ሳይሆን ከአይፎኔ ሰምቼ
ሀሜት ሲናፍቀኝ በስካይፒ አምቼ
ጥቃት ሲሰማኝ ፊስቡክ ላይ ሸፍቼ
በኮመንት እሩምታ ጠላቴን ደፍቼ
እኔ እንዳለው አለው
እንደምነሽ ሸገር እንደምነሽ ሸገር
የማይበገረው ወር እየጠበቀ የሚያገራግረው
የቤት አከራዬ የጋሽ ጣሰው አገር
የከሰመው ወንዝሽ የሚታየው ነጥፎ
እንደምነው ጣፎ እንዴት ነው ቀበና
እስቲ ድንጋይ ላጥምድ መረብ ልጣልና
ልክ እንደነ ፓሪስ እንደለንደን ሁላ
ፋፋቴም ባይኖርሽ ሽቅብ የሚፈላ
ምንጭሽ ከማን ያንሳል
ከፈነዳ ትቦ የወጣ ሰገራ ሰንጥቆሽ ይፈሳል
እንደምነሽ ሸገር የቅጠላቅጠል የፍራፍሬ አገር
አንድ ዘለላ ሙዝ ልጠሽ ባታበይኝ
በሙዝ ልጣች ጠልፈሽ የምታከባልይኝ
አሳድገሽኛል አሳድገሽኛል በማርና ወተት
የተሞላ ተረት እየተረክሽልኝ
ጥማቴን በጥማት እያረካሽልኝ
እንደምነሽ ሸገር ኦ ማይ ጎድ ይመስገን
እኔ እንዳለው አለው ሰርቼ ቀፍዬ
ሲነጋ ቀፍዬ ሲመሽም ከፍዬ
ስጋ ምታወፍር ነብስ የምታሳሳ
ዘናጭ አልጋ ሰታ እንቅልፍ የምትነሳ
አገር ላይ ተጥዬ
የወር አበባሽ ተዛብቶብሽ ይሆን?

(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)

የወር አበባ ዑደት ተዛባ የምንለው አንዲት ሴት ወትሮ ከምታየው የተለየ ጠባይ ሲገጥማት ነው፡፡

1) የወር አበባ መዛባት ዓይነቶች፦
※ የፍሰት መጠን መብዛት
※ የፍሰት መጠን ማነስ
※ መቅረት
※ የቀኑ መዛባት
※ ቶሎ ቶሎ መምጣት።

2) የወር አበባ መዛባት መገለጫዎች፦

✔ የፍሰት መጠን መብዛት፦ ከዚህ በፊት ይፈስሽ ከነበረው መጠን በላይ ሲበዛ፣ ከ7 ቀናት ባላይ ሲፈስሽ፣ ብዙ የንጽሕና መጠበቂያ ለመጠቀም
ስትገደጂ፣ ሲፈስሽ የሚረጋ ከሆነ፣ የድካ ስሜት ካለሽ፣ የማዞር ስሜት ካለሽ እና ራስን እስከ መሳት ስትደርሺ ፍሰቱ ተዛብቷል ማለት ነው፡፡
※ መንስኤዎች፡- ማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣ ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የደም መርጋት ችግር ሊሆን ይችላል።

✔ የፍሰት መጠን ማነስ፡- ከ35 ቀናት በላይ እየቆየ የሚመጣ ከሆነ፣ ከሁለት ቀናት ባነሰ ጊዜ ብቻ በመጠኑ የሚፈስሽ ከሆነ ይሄ የማነስ ምልክት ነው።
※ መንስኤዎች፡- የእንቁላል አመራረት ሂደት መዛባት (PCOD)

✔ መቅረት፡- ለ3 ተከታታይ ዑደት ወይም ለ6 ወራት የወር አበባ መቅረት፤
※ መንስኤዎቹም፦ · እርግዝና፣ የማኅጸን ጠባሳ፣ የማኅጸን ኢንፌክሽን፣ የሆርሞን መዛባት · ጭንቀት፣ ከባድ የሆነ የስፖርት እንቅስቃሴ ወይም ማረጥ ሊሆኑ ይችላሉ።

✔ ቀኑን ማዛባት፡- ወቅቱን ጠብቆ የማይፈስ የወር አበባ ዑደት
※ መንስኤዎች፡- የማኅጸን ዕጢዎች፣ የማህጸን ጫፍ ካንሰር

✔ ቶሎ ቶሎ መጣ የምንለው፡- ከ21 ቀናት በታች ተደጋሞ የሚመጣ ከሆነ ነው።
※ መንስኤዎች፡- ማህፀን እጢዎች፣ የሆርሞን መዛባት፣ ጭንቀት፣ መድሀኒቶች፣ የማረጥ እድሜ ላይ መድረስ ሊሆኑ ይችላሉ። መፍትሔዎች እንደ መንስኤዎች ዓይነት ይለያያል። ቸር እንሰንብት

መልካም ጤንነት!!

@AMCs
Africa medical students:
ዘፈን ለመጋበዝ 🎧

👨 ሄሎ 101.1 ነው
.
👨‍💼አዎ የህለቱ ተረኛ ባሒ ነኝ
.
👨 ዘፈን ለመጋበዝ ነበር
.
👨‍💼ምን የሚለውን ዘፈን
.
👨ነይልኝ ነይልኝ የሚለውን
.
👨‍💼ለማን ነው ምጋብዘው
.
👨ለመብራት ሀይል 💡💡
😳😳😳
@AMCs
Human Teeth Facts:
-Your teeth start growing 6 months before you are born.
-The Romans used to clean and whiten their teeth with urine.
-Brushing your teeth regularly has been shown to prevent heart disease.
-The tooth is the only part of the human body that cannot heal and repair by its own.
-Enamel, found on our teeth, is the hardest substance in the human body.
-Human teeth are almost as hard as rocks.
-Plaque begins to form 6 hours after brushing our teeth.
@AMCs
Sleep and Dreaming Facts:
-You have no sense of smell when you're sleeping.
-You burn more calories while sleeping than you do when watching television.
-Sleeping less than 7 hours each night reduces your life expectancy.
-The colder the room you sleep in, the better the chances are that you'll have a bad dream.
-Babies start dreaming even before they're born.
-The three things pregnant women dream most of during their first trimester are frogs, worms and potted plants.
-Scientists say the higher your I.Q. the more you dream.
-You can go without eating for weeks without succumbing, but eleven days is tops for going without sleep.
-In a year on an average person sleeps for 122 days out of 365 days.
-When we go to sleep and enter REM (Rapid Eye Movement),our bodies become completely paralyzed as areas of the brain that control movement are de-activated.
-An average person has over 1,460 dreams a year which is about 4 dreams every night.
-The average person falls asleep in seven minutes.
-By 60 years of age, 60% of men and 40% of women will snore.
-The human body releases growth hormones during sleep.
t.me/@AMCstudents
ትናንት ማታ የሆነ ሌባ ክሊኒክ ይገባና የሚዘረፍ ሲያጣ በንዴት ገመድ ላይ የተንጠለጠለ ቋንጣ ያያል... እምሽክ አርጎ ከበላና ከጨረሰ በኋላ ሲወጣ በሩ ላይ ያለው ጽሑፍ ተመለከተ 😳
..
.
..
"ግርዛት ክፍል" ይላል፡፡😳😂😂

ምን እንደበላ አስቡት፡፡🤮🙈
በምሽት በታክሲ እየተጓዝኩ ሳለ ከሁዋላዬ
<<ምን አይነት ዘመን ላይ ደረሰን? ውይ የዘንድሮ 'ሐኪም' ተብዬ... ጥርሴን ታምሜ ለሄድኩ የአሜባ መድኃኒት ይዘዘልኝ! ጉድ 'ኮ ነዉ ለጥርስ ህመም የህመም ማስታገሻና የወስፋት መድኃኒት የሚያሸክሙ የጤና ባለሙያዎችን እንጀ አሸን ፈሉልን።>> የሚል ትችት እንደ መስማት የሚያበሽቅና ደግሞም ዘና የሚያደርግ ነገር ከቶ የት ይገኛል¡¡¡???
~
'አለማወቅ ደጉ' አለች አክስቴ!
what kind of medical drug has been administered for first person who answered will have 25etb recharge via @zabule
#ForMedicalPersonnel
APPLY NOW🎓🎓🎓🎓:
✳️Full tuition fee scholarship in One of the top universities of Jiangxi Province✳️
🔷Jiangxi University of science and technology🔷 ❇️ location:Ganzhou, Jiangxi 🌎Within 5 days admission notice and JW202 will be published at November🌎

🌎English taught programs

🌍 March intake 2019

🎓🎓 Majors:

1.Civil Engineering

2.Computer Science & Engineering

3.Electrical Engineering

4.Mining Engineering

5.Business administration

6.International trade and economy

✅Type of Scholarship
✅tuition fees:Free
✅Hostel fee : 2800 RMB

👉 No Countries restriction except pakistan
👉 Age limit 18-23 via
@OiLife
ጉበት በአካላችን ትልቁ ኬሚካል አመንጪ አካል ነው። ጥቅሞቹ
ብዙ ናቸው። 3 ዋና ጥቅሞች አሉት። ባይል የሚባል ምግብን
ለመፍጨት የሚያግዝ አረንጓዴ ኬሚካል ያመነጫል።
በሰውነታችን ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ያጸዳል። የሰውነታችንን
ሃይል ፍላጎት ላማሟላት ግሉኮስ ያመነጫል። ከጉበት አስፈላጊ
ጥቅሞች አንጻር ጤናውን መከታተል ለሰውነታችን ጤና አስፈልጊ
ነው። ጥሩ አመጋገብ፣ አካል ብቃት እንቅስቅሴ እና በቂ እንቅልፍ
ማግኘት ለጉበት ጤና አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። አልኮል እና ቡና
ማብዛት የጉበታችንን ጤና አደጋ ላይ ይጥሉታል።
ጉበታችን ሲታመም ህመሙ በብዙ ሰውነት አካላታችን ላይ
ይንጸባረቃል። የተለያዩ የጉበት በሽታዎች አሉ። የተለመዱት
ሲሮሲስ፣ ሲስቲክ ህመም፣ የጉበት ፋቲ ህመም፣ የሃሞት ጠጠር
እና ሄፕታይተስ ናቸው። ጉበትዎን ሁሌ የሚንከባከቡ ከሆነ ጤናዎ
ላይ ለውጡን ያዩታል። የጉበት ጉዳት ካለዎ አስቀድሞ በመታከም
የመዳን እድልዎን ያሰፋሉ።
የጉበት ጉዳት ምልክቶች
1) ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ
derneuemann / Pixabay ብዙ ሰው የማቅለሽለሽ ስሜት እና
ማስመለስን እንደ አደገኛ የበሽታ ምልክት አይቆጥራቸውም።
ያለምንም ምክንያት የማቅለሽለሽ ስሜት ወይም ማስመለስ
ካጋጠመዎ የእኩላሊት ወይም የጉበት ህመም ያመላክታል።
ስሜቱ የተሰማዎ ግን በምግብ መመረዝ ወይንም በሌላ የተያያዘ
ህመም ከሆነ የጉበት ጉዳት የመሆን እድሉ ትንሽ ነው። የጉበት
ጉዳት ያጋጠማቸው ሰዎች የማይለቅ የማቅለሽለሽ ስሜት
ይሰማቸዋል። ይህ ስሜት የሚመጣው የጉበታችን መርዛማ ንጥረ
ነገሮችን የማስወገድ ሃይል ስለተዳከመ ነው። የምግብ አፈጫጭ
ለውጥም ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ያስከትላል። በየግዜው
የማቅለሽለሽ እና የማስታወክ ስሜት ጤናችንን በከፍተኛ ደረጃ
ስለሚያውክ የዶክተር ክትትል ያስፈልገዋል።
2) የድካም ስሜት
የማይለቅ የድካም ስሜት የጉበት ጉዳት ምልክት ሊሆን ይችላል።
የምንመገበውን ምግብ አፈራርሶ ወደ ሃይል የሚቀይረው ክፍል
ጉበት እንደመሆኑ ሲጎዳ ስውነታችን ሃይል ያንሰዋል። ከዛም አልፎ
ጉበት ለማጣራት የሚቸግረው መርዛማ ንጥረ ነገሮች ሰውነታችንን
ያዳክሙታል። የድካም ስሜት ሌላ እዚህ ከተጠቀሱት ስሜቶች
ጋር አንድላይ ከተሰማዎ ዶክተርዎን ማማከር አለብዎ።
3) የምግብ ፍላጎት መቀነስ
የምግብ ፍላጎት መቀነስ ሌላ የጉበት ጉዳት ምልክት ሊሆን
ይችላል። የምግብ ፍላጎትዎ ከቀነሰ እና እዚህ ከተጠቀሱት አንድ
ሌላ ስሜት ካለው ዶክተር ማማከር አለብዎ። የጉበት ጉዳት
ያጋጠማቸው ሰዎች የምግብ ፍላጎታቸው ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ
ይችላል። ይህም የሚሆነው ጉበታችን ሃሞት ማምረት ሲከብደው
ነው። ሃሞት ምግብ እንዲፈጭ የሚያደርግ ንጥረ ነገር ሲሆን የሱ
ምርት መቋረጥ የምግብ ፍላጎታችን እንዲጠፋ ምክንያት ይሆናል።
የምግብ ፍላጎት መቀነስ እራሱ ድካም ስሜት እንዲሰማን
በማድረግ ለማገገም እንድንቸግር ይሆናል።
4) ምግብ አለመፈጨት
ሊቨር የሚያመርተው ሃሞት ለሆድ መፍጨት አስፈላጊ ንጥረ ነገር
እንደመሆኑ፣ ጉበት ሲጎዳ የሚያጋጥመን የመፍጨት ችግር
ለተቅማጥ ሊያጋልጠን ይችላል። የሃሞት መመረት ችግር ሃሞት
ጠጠር፣ የሆድ መነፋት፣ የሆድ ድርቀት እና አጣዳፊ ተቅማጥ
ሊያመጣብን ይችላል። ጉዳቱ ከፍተኛ ሲሆን ከፍተኛ የሆድ ህመም
ስሜት እንዲሰማን ምክንያት ይሆናል።
5) የሽንት ቀለም መቀየር
በቂ ፈሳሽ እየወሰድንም ሽንታችን የጠቆረ ቀለም ካለው የጉበት
ችግር ምልክት ሊሆን ይችላል። ሽንት ሲጠቁር ወደ ብርቱካናማ
ወይም ወደ ቡኒ ቀለም ያጋድላል።ጥቁረቱ የሚከሰተው ደማችን
ውስጥ የቢሊሩቢን መጠን ሲጨምር ነው። ይህም የሚከሰተው
ጉበታችን ንጥረ ነገሩን ለማስወገድ በመቸገሩ ነው
ሁሉ በጤና የሞባይል መተግበሪያ ቴክኖሎጂ ይፋ ሆነ
________________

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እና በጆን ሆፕኪንስ ዩንቨርሲቲ የጤና ኮሚዩኒኬሽን ፕሮግራም ትብብር ለኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች የተዘጋጀው የሞባይል መተግበሪያ ቴክኖሎጂ አምስት የተለያዩ ክፍሎች የያዘ እንዲሁም በእያንዳንዱ ክፍል ውስጥም የተለያዩ ተያያዥ የጤና መልዕክቶች በማካተት የእናቶች፣ የጨቅላ ህጻናት እና የልጆችን ጤና ለመጠበቅ የሚያግዙ ናቸው፡፡

በፕሮግራሙ ይፋዊ ስነ-ስርዓት የተገኙት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ተወካይ ዶ/ር አብርሃም ታሪኩ የህብረተሰቡን ንቃተ ጤና የበለጠ ለማጎልበት አጋዥ መሆኑን ተናግረው ወደ ተጠቃሚው ማህበረሰብ ወርዶ ተግባራዊ እንዲደረግ ሚኒስቴር መ/ቤቱ እንደሚሰራ ተናግረው ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ቴክኖሎጂውን ተደራሽ በማድረግ በትብብር መስራት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ወ/ሪት እመቤት መሸሻ በአሮሚያ ክልል ሁዴ ጤና ኬላ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ ነች፡፡ ሁሉ በጤና የሞባይል መተግበሪያ የመልዕክት ማስተላለፊ ቴክኖሎጂን መጠቀም ከጀመረች 15 ቀን እንዳለፋት ትናገራለች፡፡ ለስራ ቤት ለቤት ስትንቀሳቀስም የሞባይል ቴክኖሎጂውን በመጠቀም እያዳመጠች ለመሄድና ዘወትር ስለምታዳምጠው ለማስታወስ ረድቷታል፡፡ ለተለያዩ የጤና አገልግሎት ወደ ጤና ኬላ ለሚመጡ እናቶች አገልግሎት ከመስጠቱ ጎን ለጎንም በሞባይል የተጫነውን መልዕክት ድምጽ ከፍ በማድረግ እናቶች እንዲያዳምጡት በማድረግና ግንዛቤ በመፍጠር ስለሚግዛት የስራ ጫና እንደቀነሰላት ተናግራለች፡፡ የሞባይል ቴክኖሎጂው ለሚያነቡት አንብበው እንዲረዱና ማንበብ ለማይችሉ ደግሞ በድምጽ መስማት እንዲችሉ ሆኖ የተዘጋጀ ስለሆነ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነም እመቤት አስረድታለች፡

ቴክኖሎጂው ያለአስተማሪ የጤና መልዕክቶችን ለማዳመጥና ለማንበብ የሚጠቅም እንደሆነ የገለጹት ደግሞ አቶ ፊሊጶስ ኤርጋ በደቡብ ክልል የጃራ ገለልቻ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ አቶ ፊሊጶስ በአካባቢያቸው ቀደም ሲል አባቶች የትዳር አጋሮቻቸውን በስራ የማገዝ ባህላቸው ዝቅተኛ እንደ ነበር ገልጸው ይህ ቴክኖሎጂ ግን በዕቅድ እንዴት መውለድ እንደሚገባቸው፣ በእርግዝና እና በወሊድ ጊዜ የእናትና አባት ድርሻ ምን ሊሆን እንደሚገባ ስለሚያስረዳ ብዙ ተምሬበታለሁ ይላሉ፡፡ ይሁንና አሉ አቶ ፊሊጶስ የሞባይል መልዕክቱ በማህበረሰቡ አካባቢያዊ ቋንቋ ተዘጋጅቶ ተደራሽ እንዲሆን መሰራት አለበት፡፡ ይህም አማርኛን መስማትና ማንበብ የማይችሉ የአካባቢውን ህዝቦች ለመድረስ ያግዛል ብለዋል፡፡

የሞባይል መተግበሪያ መልዕክቶቹ በአማርኛ፣ በትግርኛ እና በኦሮሚኛ የተዘጋጁ ሲሆን ፕሮጀክቱ በትግራይ፣ በደቡብ፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ለአምስት ዓመታት የሚተገበር ይሆናል፡፡
ለጠቅላላ እውቀት ፨፨ #የሰውነታችን__ብዛት ፨፨፨

※ የአጥንታችን ብዛት ~ 206
※ የጡንቻዎቻችን ብዛት ~ 639
※ የኩላሊቶቻችን ብዛት ~ 2
※ የወተት ጥርሶቻችን ብዛት ~ 20
※ የጐን አጥንቶቻችን ብዛት ~ 24 (12 ጥንዶች)
※ የልባችን ውስጥ ክፍሎች ብዛት ~ 4
※ ትልቁ ደም ቅዳ ~ አኦርታ
※ ጤናማ አማካይ የደም ግፊት መጠን ~ 120/80
※ የደም ፒ ኤች (PH) መጠን ~ 7.4
※ አዲስ የተወለደ ህፃን የአጥንት ብዛት ~ 300
※ በጀርባ ላይ የሚገኙ የአከርካሪዎች ብዛት ~ 30
※ በአንገት ላይ የሚገኙ የአከርካሪዎች ብዛት ~ 7
※ በፊት ላይ የሚገኝ የአጥንት ብዛት ~ 14
※ በጭንቅላት ላይ የሚገኝ የአጥንት ብዛት ~ 22
※ በደረት ላይ የሚገኝ የአጥንት ብዛት ~ 25
※ በክንድ ላይ የሚገኙ የአጥንት ብዛት ~ 6
※ በሰው እግር ላይ የሚገኙ የአጥንቶች ብዛት ~ 33
※ በእያንዳንድ የእጅ አንጓ (wrist) ላይ የሚገኙ የአጥንቶች ብዛት ~ 8
※ በእጅ ላይ የሚገኙ የአጥንቶች ብዛት ~ 27
※ በእያንዳንድ ጆሮአችን ላይ የሚገኙ የአጥንቶች ብዛት ~ 3
※ በክንድ ላይ የሚገኙ የጡንቻዎች ብዛት ~ 72
※ ትልቁ ኦርጋን ~ ቆዳ
※ ትልቁ ዕጢ ~ ጉበት
※ ትንሹ ሴል ~ የደም ሴል
※ ትልቁ ሴል ~ የዕንቁላል ሴል
※ ትንሹ አጥንት ~ ሰታፕስ (stapes)
※ የመጀመሪያው ንቅለ ተከላ የተደረገው የሰውነት ክፍል ~ ልብ
※ አማካይ የትንሹ አንጀት ቁመት ~ 7 ሜትር
※ አማካት የትልቁ አንጀት ቁመት ~ 1.5 ሜትር
※ አዲስ የተወለደ ህፃን አማካይ ክብደት ~ 2.6 ኪሎ ግራም
※ የልብ ምት በአንድ ደቂቃ ውስጥ ~ 72 ጊዜ
※ የሰውነት ሙቀት ~ 36.9 ዲግሪ ሴንቲግሬድ (98.4 ዲግሪ ፋራናይት)
※ አማካይ የደም መጠን ~ ከ 4-5 ሊትር
※ ቀይ የደም ሴል በህይወት የሚቆዮበት ጊዜ ~ 120 ቀናቶች
※ የእርግዝና የጊዜ ቆይታ ~ 280 ቀናቶች
※ ትልቁ የኢንዶክራይን ዕጢ ~ ታይሮይድ
※ ትልቁ የሊምፋቲክ (lymphatic) ዕጢ ~ ጣፊያ
※ ግዙፉ ሴል ~ ነርቭ ሴል
※ ትልቁ የአእምሮ ክፍል ~ ሰርብረም
※ ትልቁና ጠንካራው አጥንት ~ ፌሙር (Femur)
※ ትንሹ ጡንቻ ~ ስታፒደስ (Stapedius) (የመካከለኛው ጆሮ)
※ በሴል ውስጥ ያለ የክሮሞዞም ብዛት ~ 44 (23 ጥንዶች)
※ ትልቁ ጡንቻ ~ መቀመጫ
ምንጭ፦ Anatomy -75/109
Share @AMCstudents
Just for Fun!!
...
የጓደኛዬን ስልክ የሰረክ ልጅ እድሜህ ከሚስኮል ይጠር
ኑሮህ ቫይብሬት ሞድ ላይ ይሁን ችግሮችህ እንደ ኮንታክት ሊስቶቼ ይብዙ
ፎቶ አይውጣልህ
የድሮ ቴሌ ያስተዳድርህ!"
Amazing surgery in saint peter paul
What a news!
ምን አይነት ዜና ነው!
An operation done at St.Peter Hospital Emergency Operating Theater today and the following materials were found and removed from the abdomen of a client
-127 Nails/ሚስማር
-2 Needles/መርፌ
-2 broken glasses
The patient is currently in Surgical ICU
Good Job Dr.Dawit and team, The surgery tooks around 6:30
Hope the patient will be stable soon!
join @AMCstudents