Africa medical students councils official page
540 subscribers
122 photos
11 videos
24 files
44 links
Dear students
This channel helps you to get Books,Videos and Pictures which are reliable to the medical courses we are taking and aid us to get credible news about our college.which also promote extra academic performance of student's
👉 @AMCstudentsbot
Download Telegram
next saturday there is a visiting program in ሰለ እናት የህፃናት መርጃ anyone intersted contact me
What is Kiss?
In maths : It is the shortest distance between two lips.
.
In Biology: kiss is just exchange of germs from one mouth to another.
.
In Chemistry: Kiss is a process of testing the PH of lips.
.
In Physics: It is a process of charging human body.
.
In Computer: It is a local area network in which two bodies are connected without data cable.
.
In Economics:
It is a process in which demand is higher than supply....
.
In Accounting:- It is a systematic process of identifying, recording, measuring, classifying, verifying, summarizing, interpreting and communicating LIPs information. It reveals profit or loss for a given kissing time, and the value and nature of a lips assets, liabilities and owners' of lips equity.
Are you at risk of developing breast cancer?
You have an increased chance of having breast CA if you are
=>Female
=>Older(above 50)
=>Obese
=>Alcoholic
=>Smoker
=>Nullipara ,early menarch(before12), late first pregnancy (above 35 yrs), and late menopause(above 50)
=>Have family history of breast or ovarian cancer ( parent and siblings)
=>Exposed to radiation (as
x-rays)
=>Use oral contraception(more than 5 yrs) or hormone replacement therapy.

Comment @AmyBetty
አስማ(Asthma )
አስም ምንድን ነው?
አስም የሥርዓተ መተንፈሻ አካላት የሚያጠቃ በሽታሲሆን የአየር
ቧንቧዎች መጥበብን(constriction) በማስከተል በአተነፋፈስ ላይ
ችግር ያመጣል፡፡የአየር ቧንቧችን በተፈጥሮ ከባዕድ አካላት እራሱን የሚጠብቅበት ተፈጥሯዊ መንገድ አለው ፡፡ ጤናማ ሠው
ለባእድ ነገር የምያሳየው ግብረ መልስ በአስም በሽተኞች
ላይ የተጋነነ ነው፡፡ ስለዚህ በሌላ ጤነኛ ሰው ላይ
የማይታዮ ምልክቶች በእነሱ ላይ ይታያል፡፡ በተለይ ይሕ ወቅት የቅዝቃዜ ስለሆነ እንደ አነሳሽ ምክንያት በመሆን ይጠቀሳል፡፡ ስለዚሕ ይሕ ችግር ያለበት ቀድሞ ከአለባበስ እና አመጋገብ ጥንቃቄ ማድርግ አለባቸው ፡፡ በተጨማሪም
እንደ የአበባ ብናኝ፣ አዋራ፣ የእንስሳት
ፀጉር የመሳሰሉ ነገሮች አስም ባለባቸው ሰዎች ላይ
ከበድ ያለ ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሎ ውስጥ ተጠቃሽ፡፡ አስም
ከላይ ለተጠቀሱትና ሌሎችም ነገሮች አለርጂክ
መሆንና ለእነሱም ተገቢውን በአለርጂክ ጊዜ የሚኖር
መልስ ማሳየት ነው፡፡
እነዚህ ባእድ ነገር ሲኖር የሚኖሩ መልሶች ጊዜያዊ
የሆነ የአየር ቱቦዎች መጥበብ ፣ የትንንሽ ቱቦዎች
(bronchial tubes) ማበጥ ፣ በሰውነታችን
የሚመረተው የአየር ቱቦ ፈሳሽ(mucus)
ከተለመደው በዛ ብሎ መመረት የመሳሰሉ ክስተቶችን
ያጠቃልላል፡፡ የትንንሽ ቱቦዎች (bronchial tubes)
ማበጥ ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ጉዳት ከሚያመጡት
ለውጦች ውስጥ ይመደባል፡፡ በዚህም ምክንያት
ለተወሰነ ጊዜ አየር ማስገባትና ማስወጣት አስቸጋሪ
ይሆናል፡፡ ስለዚህም ሠውነት ኦክስጅን ወደ ውስጥ
ለመሳብ ብዙ ይቸገራል በዚህም ቶሎ ቶሎ ለመተንፈስ ይገደዳል፡፡በአስም
በሽታ ጊዜ የሚከሰተው የአየር ቱቦዎች መጥበብ
ጊዜያዊ፣ዘለቀታዊ እና ወቅት እየጠበቀ የሚመጣ የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች መሆኑ ይለያዋል፡፡ ነገር ግን ለረዥም ጊዜ የቆየ በሽታ
ያለበት ሰው የአየር ቧንቧው መጥበብ ጊዜያዊነቱን
ትቶ ለሁልጊዜም ሊሆን ይችላል፡፡አስም ወቅትን፣
የአየር ሁኔታን ፣ ቦታን እንዲሁም እድሜን የሚመርጥ
በሽታ ነው፡፡
የአስም በሽታ የአንድ ሰውን የእንቅስቃሴንና ስራ
የመስራት አቅሙን የሚያደክም እንዲሁም ለብዙ
ሰዎች ሆስፒታል ጉብኝት ምክንያት የሆነ በሽታ ነው፡፡
በልጅነት የሚኖር አስም በጎልመሶች ላይ ካለው
በበለጠ በብዛት የሚታይ ሲሆን እድሜ እየጨመረ
በሄደ ቁጥር በሽታው የመጥፋት አዝማሚያ አለው፡፡
አሰምን የሚያመጡ ነገሮች ምንድን ናቸው?
ረዘም ላለ ጊዜ የቆየ ሳል፤ አየር ማጠርና ፤ በቤተሠብ ታሪክ እና ከበባዊ ሆኔታ እንዲሆም በግልፅ አይታወቅም ፡፡ ቀድሙ ካለ
በሚተነፍሱበት ጊዜ የሚሰማ ሲር ሲር የሚል ድምፅ
(wheezing) ዋነኞቹ የአስም መገለጫ ምልክቶች
ናቸው፡፡ ሳሉ ከብዙ እንቅስቃሴ እና ከሳቅ ጋር ተያይዞ
የሚባባስ ሲሆን የታፈነ አይነት ድምፅ ይኖረዋል፡፡
እነዚህ ምልክቶች ባልተጠበቁበት ሰአት የሚነሱ
ሲሆን ብዙ ጊዜ ማታ ማታ እና ጠዋት ይብሳሉ፡፡
ከዚህ በተጨማሪ አክታ፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስና ፊት
እና ጀርባ ላይ የማሳከክ ስሜት ይኖራል፡፡ በአይየር
ቱቦዎች መጥበብ የተነሳ የመተንፈሱ ስራ ተጨማሪ
ጡንቻዎችን ሊፈልግ ይችላል፡፡ በዚህም ምክንያት
የጎድን ጡንቻዎች አተነፋፈስን ተከትሎ ገባ ወጣ
ማለት እና የአንገት ጡንቻዎች መገታተርን
ልታስተውል ትችላለህ፡፡ ድካም እና የአቅም ማነስም
ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ናቸው፡፡ የነዚህ
ምልክቶች መኖር የአስም በሽተኛነትን አያረጋግጥም፡፡
ግን ወደሆስፒታል ለመሄድ ጥሩ ምክንያት ናቸው፡፡
አስም ያለባቸው የቅርብ ዘመዶች – እናትና አባት
ወይም እህት እና ወንድም – ያለው ሰው ከሌላው
ሰው በተለየ በአስም ለመያዝ ትልቅ እድል አለው፡፡
በሽታው በቤተሰብ የሚሄድ ባይሆንም አስም ያለበት
ቤተሰብ ያለው ሰው ሰፋ ያለ ተጋላጭነት ይኖረዋል፡፡
አስምን የሚያባብሱ (የሚያስነሱ) ነገሮች ምንድን ናቸው?
አስምን የሚያስነሱ አሊያም የሚያባብሱ ብዙ ነገሮች
አሉ፡፡ ጉንፋን እና የሳይነስ መቁሰል (sinusitis)
አስምን ያባብሳሉ፡፡ከበድ ያለ እንቅስቃሤ በምታደርግበት ጊዜ
አየር ቶሎ ቶሎ ትተነፍሳለህ፡፡ ይሄ ደግሞ የአየር
ቱቦዎችህ እንዲጠቡ የሚያደርጉ ኬሚካሎች
ከተለያዩ ህዋሳት እንዲመረቱ ያደርጋል፡፡ ድሮም
ጠባብ በነበረው የአይየር ቱቦ ላይ ተጨማሪ
መጥበብ በአተነፋፈስህ ላይ ከበፊቱ በበለጠ
አስቸጋሪ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ቅዝቃዜም የራሱ የሆነ
ድርሻ አለው፡፡ ከባድ ስፖርት ከመስራት ጋር
ተመሳሳይ የሆነ ለውጥ ያስከትላል፡፡
ሲጋራ ማጨስ በጣም መጥፎ ችግሮችን
የሚያስከትል ተግባር ነው፡፡ የሳንባ ጠንቅ የሆነው
ይህ ልማድ ይህንን በሽታ ለማባባስ ትልቅ አስተዋፅኦ
ያደርጋል፡፡ አንዳድ ህመምተኞች ላይ ሽቶ፣ ሳቅ፣
የአየር ለውጥ ፣ ሙቀት እና ጭንቀት ህመሙን
ያባብስባቸዋል፡፡ውፍረትም(ጤናማ ያልሆነ) ከአስም ጋር በተያያዘ
እራሱን የቻለ መጥፎ ጎን አለው፡፡ አንደ አነድ መደሀኒቶችም
አስምን ሊቀሰቅሱ ይችላሉ፡፡ የክረምት
ወራትም ቅዝቃዜ ስለሚኖር አስምህን ሊያስነሳብህ
ይችላል፡፡በተጨማሪም ብዙ ጀርሞች በእነዚህ
ወቅቶች ስለሚራቡ ብዙ የላይኛው መተንፈሻ አካላት
በሽታዎች ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ጉንፋንና ጉንፋን መሰል
በሽታዎች አስምን ያባብሳሉ፡፡ በተጨማሪም ዋነኛው
አለርጂክ አምጪው ፈንገስ በክረምት በየቦታው
ስለሚገኝ አስምህን ያባብሳሎ፡፡
የአስም ህመምተኛ ሰው እራሱን እንዴት ሊንከባከብ
ይችላል?
በሽታው እንዳለብህ ከታወቀ በኋላ የሚሰጡህን
መድሃኒቶች በባለመውያ ትእዛዝ መሰረት በአግባቡ
መጠቀም ፡ በተጨማሪ ቪታሚን ሲ እና ቪታሚን ኤን
የያዙ ምግቦችን ለምሳሌ ፍራፍሬ እና አትክልትን –
ቲማቲም፣ ፣ ጥቅል ጎመን (ቪታሚን ሲ በሙቀት
ቶሎ ስለሚጠፋ በደንብ ባይበስሉ ይመከራል)
በተጨማሪ ሎሚ እና ብርቱካን – እንዲሁም የአሳ
ዘይትን መመገብ፡፡ ከዚህ ባለፈ በቂ እረፍት ማግኘትና
አስሙን ከሚያባብሱ ነገሮች በ አመጋገብ እንደ ጋስ የሚፈጥር ፣ ተጨመሪ ነገር ከፋብሪካዎች በሚወጡ ምግብ ላይ (preservative and adative color ) መቅነስ ተገቢ ነው፡፡
#Share #share ጓደኟችው እንዴቀላቀ @silegnafashion
@silegnafashion
መልካም የጤና እና የዕርፍት ግዜ፡፡
"የጤናዉ ዘርፍ ተደፈረ! ሙያዉ ተናቀ፡" በማያውቁት ደራሲያንንን፡ ተዋናያንንንን......
-------በጣም ከፋኝኝኝ.....'-----
ምንም ቢባል ምን ግን ጤና የተከበረ ሙያ ነዉ፡፡

ተሰደብን፡ ተወረደብን፡፡ የጤና ባለሙያዉና የጤና ሙያ ከአፈር በታች ቀበሩት፡፡ የጤና ባለሙያዉን ተዘባበቱበት-'ሚስቴን ዳርኳት' የአማረኛ ፊልም አዋረደን፡፡ ሰራችንን ዋጋ አሳጣዉ፡፡ ሙያዉን ረጋገጠዉዉ!
ፊልሙን ያዩ ለጤና ባለሙያዉ አዘኑለት፡ እንባ መጠጡለት--ተዋናያኑ የጤና ሙያዉን ዘለፉትትትትትትትትት---!

ነገሩ እንዲህ ነዉ፡፡ የፊልሙ መሪ ተዋናይ አለማየሁ ታደሰ ነዉ፡፡ ጓደኛዉ ደግሞ አለምሰገድ ....! መሪ ተዋናዩ ደማቅ ጋብቻ ለመፈፀም ለሰርግ እየተሰናዳ ሳለ አልፎ አልፎ ይነስረዋል፡፡ ለጋብቻ ሽማግሌ ለመላክ እየተሰናዳ ባለበት ወቅት ወደ ሆስፒታል ያመራል፡፡ በጤና ተቋሙ ምርመራ ተደርጎለት በገፀባህርይ ስሙ ናሆም(አለማየሁ)ን ነርሷና ሐኪሙ ወደ አንድ ክፍሉ ጠርተዉት
<<እንዲህ ላለ ተስፈኛ ወጣት ይኽን መንገር ቢከብድም መናገር...>> ሐኪሙ ተናገረ፡፡
<<ካንሰር ነዉ የምትለኝ?>> አለ ተዋናዩ በተስፋ መቁረጥ
<<አዎ፡፡ ይኽን ማሳወቅ ሙያዊ ግዴታችን ነዉ፡፡ በመሆኑም በህይወት የምትቆየዉ አንድ ወር ነዉ፡፡>> አለችዊ ነርሷ ከአጠገቡ ቆማ በኩራት...
<<አንድ ወር ማለት ስንት አመት ማለት ነዉ? ሰርጌ እኮ በወር ዉስጥ ነዉ..>> አለ ተዋናዪ ግራ ግብት ብሎት...
*
ይኽ መጥፎ ዜና ማርዳት(Breaking Bad News) እጅጉን ሙያዉን ባዋረደና የሙያዉን ምግባር ባልተለበሰ መልኩ ተከዉኗል፡፡ ተዋናዩ በሁለት አጋጣሚ ቀለል ያለ ነስር አጋጥሞት ለቼክ አፕ ከመሄዱ ዉጪ በተረፈ 'ጤነኛ ነዉ'፡ ካንሰር የተባለበት ምርመራ፡ ምክንየት አልተነገረም፡ የምን ካንሰር እንደሆነም አልተገለፀም፡፡
****
ተስፋ የቆረጠዉና በአንድ ወር እንደሚሞት የተነገረዉን ተዋናይ አለማየሁ ጓደኛዉ አለምሰገድ <<አትመናቸዉ፡ የኛን ሐገር ሐኪሞች አትመናቸዉ..>> ይለዋል፡ ይቀጥልና
<<የእኛ ሀገር ሐኪሞች እኮ እንቅርት ብለዉ ትርፍ አንጀት የሚቆርጡ ናቸዉ፡፡ ግራ እግርህን ታመህ ቀኝ እግርህን የሚቆርጡ ናቸዉ፡፡... ደግሞም ቀዶ ህክምና አርገዉ ቢላና መቀስ ታካሚዉ ሆድ ውስጥ እረስተዉ የሚወጡ ናቸዉ!!>> እያለዉ 'የጤና ባለሙያዎችን' እንዳያምን ይነግረዋል፡፡ ሆኖም ግን ዋና ተዋናዩ 'ካንሰር' እንዳለበትና በአንድ ወር እንደሚሞት አመኗል፡፡
*
ከዚህ ትዕይንት በሁዋላ ዋና ተዋናዪ የሰርግ ተስፍዉ ሟሸሸ፡፡ ሞት አንዣበበት፡ ሞት ቀረበዉ፡ ...ተቆርጦ በነበረዉ ሰርግ ዕለት መገኘት እንደማይችል የተረዳዉ ተዋናዩ ሙሽራ ሚስቱን ለሌላ ሰዉ ለማደር፡ የሰርግ ቀኗ እንዳይበላሽ መሯሯጥ ጀመረ-'ሚስቴን ዳርኳት''፡፡ ለሚስቱ ባል ማፈላላግ ጀመረ፡፡ አብሮት እንደማይቀበር የተረዳዉን ሀብቱንም መበተን፡ ለሰዉ ማከፋፈል ጀመረ፡፡---ያለምክንያት እያፈቀራት ተጣላት፡ አስከፋት፡፡ሌላ ባልም (የድሮ ፍቅረኛዋን) አገኘላት-ገንዘብም ሠጠዉ፡፡ ከሙሽራዋ ጋርም ተስማሙ!
*
ወደ መጨረሻም የሙሽራዋ ቤተሰቦች ሽማግሌዎችን በተቆረጠዉ የሽምግልና ቀን ስጠባበቁ ቢዉሉም የተገኘላት ባል 'ገንዘብ ካልጨመርክ ሽማግሌ አልክም....>> ብጥብጥ ተነሳ፡፡ የመሽራዉ ተዋናይ ሐናን ቤተሰቦች ተዋረዱ፡ ሙሽራዋ ቀን ጨለመባት፡፡
*
በዚህ መኻል እየተጨነቀ ላለዉ 'ካንሰር' በሽተኛ ለተባለዉ ናሆም(አለማየሁ ታደሰ) ከሆስፒታል ተደወለለት፡፡ ሆስፒታል እንደደረሰም ነርሷ 'ናሆሞ ...>> እያለች ስትጣራ መሪ ተዋናዪ ወደ ሐኪሙ ገባ፡፡
<<በጣም ይቅርታ፡፡ ባለፈዉ ከወር በፊት የካንሰር በሽተኛ ነህ ያልንህ በስህተት ነዉ፡፡ በስም መመሳሰል ነዉ...!>> አሐ ሐኪሙ
<<አዎ በስህተት ነዉ፡፡ የአንተና የሌላ ሰዉ ሰም እስከ አባታችሁ መመሳሰል ነዉ ችግሩን የፈጠረዉ..፡፡ ያኛዉ ናሆም በካንሰሩ ሞቷል፡፡ >> አለች ነርሷ ኮራ ብላ
ተዋናዩ ማመን አቃተዉ፡...ደስ አለዉዉ!!
<<የካንሰር በሽተኛ አይደለሁም ማለት ነዉ?>> ይለዋል ሐኪሙን፡፡ ሐኪሙም
<<አዎ አንተ ጤነኛ ነህህ፡፡ ሰርግህ እንዴት ሆነ...>> ሲለዉ ተዋናዩ ብድግ ብሉ ሌላ ሰዉ ልታገባ የሽማግሌ ቀኑ በዚያች ቅፅበት መሆኑን ሲታወሰዉ ሩጫ ጀመረ፡፡
**

'በህክምና ስህተት 'ካንሰር' ተብሎ የነበረዉ ተዋናዩ ወደ ሙሽራዋ(ሐናን) ከጓደኛዉ ጋ በመኪና ተጣደፊ፡፡ ከአመሻሽ ቤት ደርሰዉ አባቷን አግኝተዉ ይቅርታ ጠይቀዉ ሽምግልና መሆኑን ተናግረዉ ወደ ሙሽራዉ ክፋል ሲገቡ፡ ሽማግሌዎች ቀርተዉ ቤተሰቦቿን ያሳፈረችዉ መሪዋ ሴት ተዋናይ፡ ፍቅሯንም ያጣችዉ ተዋናይ ራሷን ለማጥፈት(Suicide) ብዚ መድኃኒት ዉጣ አኮረፋት እየደፈቀች አገኟት፡፡ ወደ ሆስፒታልም ይዘዉት ሄዱ፡፡ ሐኪሞች 'ማትረፋ አለመቻሏን፡ መሞቷን አረዱ፡፡...ኡኡታ ተፈጠረ፡፡
****
መሪ ተዋናዪ 'አትመኗቸዉ፡ በስህተት ነዉ፡፡ በስህተት ነዉ፡ ሐኪሞች ተሳስተዉ ነዉ...፡ በህይወት አለች፡፡ >> እያለ እየጮኸ ሳለ ጓደኛዉን <<የእዉነት ሞታለች አለዉ..?>>
ጓደኛዉም <<አዎ፡ እነዚህ ሐኪሞች፡ የጤና ባለሙያዎች ሲመረቁ እጃቸዉን አንስተዉ ቃል የሚገቡት ሰዉ ለመግደል ነዉ፡፡>> አለዉ፡፡ <<እንዴት አመንካቸዉ? አትመናቸዉ ትለኝ አልነበረም? እንቅርት ለመቁረጥ ትርፍ አንጀት የሚቆርጡ ትለኝ አልነበር--አሁን ሞታለች ሲሉህ እንዴት አመንካቸዉ?>> ይለዋል፡፡ መሪ ተዋናዪ 'አልሞተችም፡ ትመጣለች፡ የሙሽራ ልብስ ለብሳ መጣች፡ መጣች፡ ..እይዋት መጣች>> ብሎ ማመን ጀመረ-የአዕምሮ በሽተኛ ሆነ፡፡_Hallucinations!
'ሚስቴን ዳርኳት' ፊልሙ ሲያልቅም የማጀቢያ ሙዚቃዉ <<በስህተት፡ በስህተት፡ በህክምና ስህተት...የቱ ነዉስ እዉነት>> እያለ ይደመጣል፡፡
*
በአጠቃላይ ፊልሙ የጤና ባለሙያዉን የሰደበ፡ ምንም የማይሰሩ ግዑዛን እንደሆነ የሚተርክ ነዉ፡፡ የጤና ባለሙያዎች ሲመረቁ ቃል ኪዳን የሚገቡት 'ሰዉን ለመግደል?' ነዉ ሲል ይደመድማል፡፡ 'ሚስቴን ዳርኩት' የሀገራችንን ህክምና 'ሙታን' ያለ፡ የጤና ባለሙያዎችን 'ገዳይ' ብሎ የፈረጀ ነዉ ብንል ማጋነን አይሆንም ፡፡
በመሆኑም
1. የጤና ጥበቃና የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር፡ የኢትየጵያ የጤና ባለሙያ ማህበራት...ፊልሙ በአስቸኳይ ሳይዉል፡ ሳያድር በሲኒማ መታየቱ እንዲቆም ያድርጉ፡፡ አሁነነነነነኑኑኑኑ!
2. የፊልሙ ደራሲ፡ ዳይሬክተር፡ ተዋናይ....በሙሉ በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡቡቡቡቡ፡፡
3. የኢትዮጵያ አርቲስቶች ይኽን አይነት አስነዋሪ ስራ ከመስራት ይቆጠቡ፡፡
4. አርቲስት አለማየሁ ታደሰ፡ አለምሰገድ ተስፋዬ...በፊልሙ ያሳያችሁን በጤና ባለሙያዉ ላይ የፈፀማችሁት ነዉር መሆኑን እወቁትትትት
5. ጤና ጥበቃ እና የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አስቸኳይ መልስ የጤና ባለሙያዉ ከእናንተ እንደሚጠብቅ አዉቃችሁ ለሙያዉ ተቆርቋሪነታችሁን አሳዩንንን!!
6. የጤና ባለሙያዎችም ይኽን አይነትትትት ተግባር በቸልተኝነት ላለማለፍ 'በቃችሁ!' እንበላቸዉ፡፡
++++
++++
(ፊልሙ በተለያያ ሲኒማ ቤቶች እየታዬ ነዉ፡፡ ሰዎች እየደወሉ እንዳያዉ በነገሩኝ መሠረት ዛሬ አይቼዋለሁ---አንገቴን ደፍቻለሁ፡፡)

# ክብር ለጤና ባለሙያዎች!!
cc Amir Aman
Gemechis Mamo
Getachew tollera
Abraham Ariaya
Tihitena Negussie
we would like to extended our deep heartfelt congratulations he did it successfully in computer science 👍👍👍 @sami
#የአእምሮ #ጤንነት
#ለአንጎል #ጎጂ #የሆኑ #ልማዶች


👉#ቁርስ #አለመመገብ
ቁርስ የማይመገቡ ከሆነ በሰውነትዎ ውስጥ የሚገኘውን የደም ስኳር መጠን ስለሚቀንስ ለአንጎል የሚደርሰውን የምግብ መጠን በማስተጓጎል ለጉዳት ይዳርገናል።
👉#በህመም #ወቅት #በቂ #እረፍት #አለማድረግ
ሰውነታችን በህመም ሲጠቃ በቂ እረፍት ማድረግ እና ከህመሙ ማገገም በአንጎል ላይ ተጨማሪ ጫና እንዳይኖር ይረዳል።
👉#ሲጋራ #ማጤስ
ሲጋራ ማጤስ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። የልብ ህመም፣ የሳምባ ካንሰር እና ስትሮክን ከማስከተል ባለፈ በአንጎል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።
👉#ከፍተኛ #የስኳር #መጠን ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጣፋጭነት ያላቸው ምግቦችና መጠጦች ማዘውተር ለአንጎል ጉዳት መንስኤ ናቸው።
👉#የአየር #ብክለት
አንጎል ከየትኛውም የሰውነት ክፍሎቻችን በበለጠ ኦክስጂን ያስፈልገዋል። የምንተነፍሰው አየር የተበከለ ከሆነና ለአንጎል የሚደርሰው የኦክስጅን መጠን ከቀነሰ ጉዳት ያስከትላል።
👉#የእንቅልፍ #እጦት
እንቅልፍ አንጎልን እረፍት እንዲያገኝ የምናደርግበት ሂደት ስለሆነ በቂ እንቅልፍ አለመውሰድ ለጉዳት ይዳርጋል።
ለረጅም ጊዜ እንቅልፍ ማጣት የአንጎል ህዋሳት ሞትን ያፋጥናል፡፡
👉#የአልኮል #መጠጥ #ማብዛት
በቀን የምንወስደው የአልኮል መጠጥ ከፍተኛ ከሆነ የአንጎል ህዋሶቻችንን ቀስ በቀስ ሊገድል ስለሚችል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።
👉#የምግብ አይነቶችን መምረጥ
ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምግቦችን መመገብ ለአንጎል ጤናማነት ወሳኝ ነው።
ጤና ይስጥልኝ
እራስሽን አሞሽ ሄደሽ ከፍሎ ነዉ እሚያምሽ ሲሉሽ አይ በነጻ ነዉ ያልሽዉ ልጅ የሚስቴን ዳርኳት ዳይሬክተር ነሽ እንዴ?😂😂😂 #የህዝብ
#አልኮል #መጠጣት #ለምን #ያወፍራል?

መጠኑ ይለያይ እንጂ የአልኮል ይዘት ያላቸውን መጠጦች መውሰድ በየትኛውም ማህበረሰብ የተለመደ ነው። አልኮል በመጠኑ ሲወሰድ የተለያዩ የማህበራዊና የጤና ጥቅሞች ቢኖሩትም ከልክ ሲያልፍ ግን መዘዙ ብዙ ነው። የአዕምሮ መመሳቀል፣ የስኳር እና ጉበት በሽታ፣ ሱስኝነት እና መሰል ጉዳቶች አልኮልን ከማዘውተር የተነሳ የሚከሰቱ የጤና እክሎች ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ አልኮል የሚያዘወትሩ ሰዎች ለከፍተኛ ውፍረት እንደሚጋለጡ ነው የሚነገረው። ከአልኮል የምናገኘው ካርቦሃይድሬት፣ ፕሮቲን እና ስብ ምንም አይነት የምግብ ይዘት የሌለው መሆኑም ሰውነታችንን ለበርካታ ችግሮች ተጋላጭ እንዲሆን ያደርጋል። ከዚህ በታችም አልኮል ለሰውነት ክብደት መጨመር ያለውን አስተዋጽኦ እንመለከታለን።
#አልኮል፡-
👉ሰውነታችን በርካታ ኤስትሮጂን እንዲያመርት ያደርጋል
ኤስትሮጂን በሰውነታችን ውስጥ የስብ መከማቸትን ከማሳደጉም ባሻገር የጡንቻ ጥንካሬ እንዲቀንስ ያደርጋል።
👉የምግብ ፍላጎትን ያሳድጋል
አልኮል የምግብ ፍላጎታችን እንዲጨምር በማድረግ ከልክ በላይ እንድንመገብ ያበረታታል።
አንዳንድ ሬስቶራንቶችም ከምግብ በፊት የአልኮል መጠጦችን ማቅረባቸው ደንበኞቻቸው የሚወስዱት የምግብ ፍጆታ እንዲጨምር በማሰብ መሆኑን ልብ ማለት ይገባል።
👉የስብ መቃጠልን ያዘገያል
ጉበታችን የምንጠጣውን አልኮል ወደ ኮምጣጤነት በመቀየር ሲጠመድ የሰውነታችንን ስብ በማቅለጥ ሃይል ከማግኘት ይልቅ ከኮምጣጤ ሃይል ለማግኘት ይገደዳል።
ኮምጣጤ የስብ መቅለጥንና የሃይል ምንጭነትን ሲተካም ውፍረት ይከሰታል።
አንድ ጥናት አልኮል አብዝተን የምንወስድ ከሆነ ሰውነታችን እስከ አራት ቀናት ያህል ስብን ማቅለጥ እንደማይችል አመላክቷል።
👉የድካም ስሜት ይፈጥራል
አብዝቶ መጠጣት ለውሃ ጥም በመዳረግ እና በማዳከም ክብደትን በተሻለ ፍጥነት ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ይጎዳል።
በአልኮል ምክንያት የሚከሰት የውሃ ጥም ለቆዳ መሸብሸብ እና ድርቀትም ያጋልጣል።
👉የስኳር መጠኑ ከፍተኛ ነው
አልኮል የተፈጥሯዊ ምግቦች ጭማቂ እንደመሆኑ ከፍተኛ የስኳር ይዘት አለው፤ ይህም በቀላሉ ለውፍረት ያጋልጣል።
👉ክብደትን ለመቀነስ የሚረዱ ማዕድናት (ሚኒራሎችን) ያሳጣል
አልኮል እንደ ማግኔዢየም፣ ፖታሲየም፣ ካልሲየም እና ዚንክ ያሉ የስብ መቅለጥን የሚያፋጥኑ ማዕድናትን እንደሚያሳጣ ይነገራል።
👉የመነቃቃትን ስሜትን ያዳክማል
አልኮል አዕምሯችን ተግባሩን በአግባቡ እንዳይወጣ በማድረግ ለጭንቀትና ድብርት ከመዳረጉም በዘለለ ክብደት ለመቀነስ የሚደረግ እንቅስቃሴን በንቃት ገቢራዊ እንዳናደርገው ያደርጋል።
በአጠቃላይ አልኮል ምንም እንኳን በተለምዶ ክብደትን ይቀንሳል እንጂ ይጨምራል ተብሎ ባይታሰብም ከላይ የተመለከትናቸውና ሌሎች በርካታ ምክንያቶች አልኮል የውፍረት ምንጭ መሆኑን መረዳት ይኖርብናል።
@zabule
ምንጭ፡- www.nowloss.com
Forwarded from Pharmacy for all (@Abba Gemechis)
ሰበር ዜና የአባይ ግድብ ዋና ስራአስኪያጅ የነበሩት ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ውስጥ መስቀል አደባባይ አካባቢ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ ተገኝቷል!

👉 @pharmforall
👉 @pharmforall
😭😭😭
How ascaris made obstruction .....
nunu:
class of 2018 of Africa medical college graduation commitee has started the preparation of its graduation year book as well as embarked upon various events to give back to the community. If you are interested to be a sponsor please contact via @derse @Edandi or @zabule
.2018 Graduation commitee
How To Heal A Strep Throat Naturally.

https://curejoy.io/2wngss

(Click the link to download the video to your phone)
@Amcs
#ስለጨጓራ #ሕመም


👉መንስኤዎች
የጨጓራ ሕመም የሚከሰተው በጨጓራችን ግድግዳ ላይ ቁስለት በሚያስከትሉ ምክንያቶች ነው፡፡ ከመንስኤዎቹ መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ፡-
👉ለጨጓራ ተስማሚ ያልሆኑ መድሃኒቶችን በመውሰድ
👉የባክቴሪያ ኢንፌክሽን
👉ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ መውሰድ
👉ቅመም የበዛባቸው ምግቦች መመገብ
👉ጭንቀት
👉ሲጋራ ማጤስ
👉መርዛማ ኬሚካሎች ወደ ሆድ ማስገባት
#የጨጓራ #ሕመም #ምልክቶች #ምንድን #ናቸው?
የጨጓራ ሕመም ምልክቶች ከሰውስው የሚለያዩ ቢሆንም በአብዛኛው ግን እነዚህን ያካትታሉ፡፡
👉የማቅለሽለሽ ስሜት
👉የሆድ መንፋት ስሜት
👉ማስመለስ
👉የምግብ አለመፈጨት
👉የማቃጠል ስሜት በተለይ 👉ከምግብ በኋላ
👉የምግብ ፍላጎት መቀነስ
👉የሠገራ ቀለም መለወጥ ወይም መጥቆር ናቸው
ከባድ የሆነ የጨጓራ ሕመም ያላቸው ሰዎች የጨጓራ ቁስለት እና መድማት ሊከሰትባቸው ስለሚችል በተጨማሪ እነዚህ ምልክቶች ሊታይባቸው ይችላሉ፡፡
👉የማላብ ስሜት
👉የልብ ምት መጨመር
👉የትንፋሽ ማጠር
👉ከፍተኛ የሆነ የማቃጠል ስሜት
👉ደም ማስመለስ
👉ደም የቀላቀለና ከወትሮው 👉የተለየ መጥፎ ሽታ ያለው ሠገራ መኖር ናቸው፡፡
እነዚህ ዓይነት ምልክቶች ያሉበት ሰው ወደ ሕክምና ማዕከል በመሄድ ተገቢ የሆነውን ምርመራና ሕክምና ማግኘት ይኖርበታል፡፡
የሕክምናው ሁኔታ የጨጓራ ሕመሙ እንደተከሰተበት ምክንያት ሊለያይ ቢችልም ያሉትን ምልክቶች በማስወገድ ለሕመምተኛው ፋታ መስጠትና ሕምሙን ያስከተላውን ሁኔታ በምርመራዎች አረጋግጦ መፍትሔ መስጠት ተገቢ ነው፡፡
የጨጓራ ሕመምን ሊያስነሱብን የሚችሉ ማናቸውንም ነገሮች በማስወገድ ሕምሙ እንዳይቀሰቀስብን ማድረግ ይቻላል፡፡

መረጃው ከተመቻችሁ Share በማድረግ ለሌሎችም ያጋሩ