ታላቅ የኩራት እና የእንኳን ደስ አለሽ መልዕክት
ውድ ተማሪ ህዳሴ ዘመኑ፣ በዩኒቨርስቲ መግቢያ
ፈተና ያስመዘገብሽውን እጅግ አስደናቂ እና ታላቅ ውጤት (ከ600/583!) ስንሰማ ማህበራችን ከልብ የመነጨ ታላቅ ደስታና ኩራት ተሰምቶናል። ይህ ውጤት ያሳየሽውን ልዩ የዕውቀት ፍላጎት(Curiosity )፣ ሳይንሳዊ ብልህነት እና ከፍተኛ ትጋት በግልጽ የሚያሳይ ነው።
የትምህርትን ዋጋ ከፍ አድርጎ እንደሚመለከት የህክምና ማህበር፣ የአንቺን የመሰሉ ስኬታማ ታዳጊዎችን መውጣት በታላቅ ተስፋ ይከታተላል። ላቅ ያለ ውጤት ለማምጣት ያሳየሽው ቁርጠኝነትና ተጋድሎ ለሀገራችን ታዳጊ ተማሪዎች አርአያ የሚሆን ብቻ ሳይሆን፣ ወደፊት ለሀገርሽ የምታበረክቺውን ታላቅ አስተዋጽኦ የምናይበት ብሩህ ተስፋችን ነው።
ይህ ያገኘሽው ስኬት ወደፊት ለምትገቢባቸው የከፍተኛ ትምህርት ምዕራፎች ሁሉ ጠንካራ መሠረት እንደሚሆንልሽ አንጠራጠርም። ምናልባትም ወደፊት ይህንን የላቀ አእምሮሽን እና ትጋትሽን የሰውን ልጅ ህይወት ለመታደግ እና ማህበረሰብሽን ለማገልገል ወደ ህክምናው ዓለም የመግባት ዝንባሌው ካለሽም ማህበራችን ታላቅ ደስታ ይሠማዋል።
በድጋሚ ላስመዘገብሽው አስደናቂ ውጤት እንኳን ደስ አለሽ እያልን፣ ለወደፊት የትምህርት እና የህይወት ጉዞሽ ሁሉ ስኬትን እና መልካሙን ሁሉ እንመኛለን።
በርቺ!!!
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህር ዳር
ኢትዮጵያ
ነሃሴ,2018 ዓ/ም

👍6
A Proud Message of Congratulations
©©©
Dear Student, Hidase Zemen,
On behalf of the Amhara Medical Association – Bahir Dar, Ethiopia, we extend our heartfelt congratulations on your extraordinary achievement in the National University Entrance Examination, scoring 583 out of 600.
Your remarkable result reflects exceptional curiosity, scientific brilliance, discipline, and unwavering dedication. It is a proud accomplishment not only for you and your family, but also for our community.
As an association that values education and excellence, we are inspired by outstanding young scholars like you. Your determination and hard work serve as a model for other students and give us great hope for the future of our country.
We are confident that this success will become a strong foundation for your higher education journey. Should you choose to pursue a career in medicine, we would be delighted to see your talent and commitment contribute to saving lives and serving society.
Congratulations once again on this outstanding achievement! We wish you continued success, wisdom, and excellence in all your future academic and life endeavors.
Keep shining!
With great respect,
Amhara Medical Association
Bahir Dar, Ethiopia
Nehase 2018 E.C. (August 2026)

👍4
የአማራ ህክምና ማህበር ከአማራ ክልል ስፔሻሊስት ሀኪሞች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ
©©©
የአማራ ህክምና ማህበር ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከአማራ ክልል ስፔሻሊስት ሀኪሞች ጋር በወቅታዊ እና አስቸኳይ የጤና ሴክተሩ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ፍሬያማ ውይይት አካሂዷል።በውይይቱም በርካታ ሀኪሞች የተሳተፉ ሲሆን ማህበሩ እስካሁን ያከናወናቸውን አበይት ተግባራት፣ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶች እና በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገባቸውን ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች ለተሳታፊ ሀኪሞች በስፋት አቅርቧል።
በውይይቱ ከተነሱት ዋና ዋና ነጥቦች መካከል፡
ሀ) የጤና ስርዓቱ ወቅታዊ ሁኔታ፡ ስለ አማራ ክልል እና በጠቅላላው ስለ ኢትዮጵያ ህዝብ የጤና ስርዓት ተስፋዎችና ተግዳሮቶች፣
ለ) የዱቲ (Duty) ክፍያ ስርዓት፡ በ2018 ዓ.ም ያልተከፈለውን የዱቲ ክፍያ በተመለከተ የሚወሰዱ የመፍትሔ እርምጃዎች እና የወደፊት የክፍያ ማሻሻያ መንገዶች(212 ሰአትን በተመለከተና ሌሎችን)፣
ሐ) የማህበሩ ጥንካሬ እና አንድነት፡ የአማራ ህክምና ማህበርን የበለጠ ማጠናከርና ማገዝ የሚቻልበት መንገድ እንዲሁም የሙያ ማህበራት ከክፍፍል ይልቅ በአንድነት የመቆማቸው ወሳኝ አስፈላጊነት በሰፊው ተዳስሰዋል።
በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የጤና ባለሙያዎቻችን ለጤናው ስርዓት መሻሻል እና ለሙያተኞች መብት መከበር ያላቸውን ቁርጠኝነት እና ፅኑ አቋም ገልጸዋል። እንዲሁም በቀጣይ በየጊዜው በመገናኘት ምክክር ለማድረግ እና ማህበሩ የሚያከናውናቸውን እያንዳንዳቸውን እንቅስቃሴዎች በመገናኛ ብዙሃን ለህዝብ ይፋ ለማድረግ ውሳኔ ላይ ተደርሷል።
የጥሪ መልእክት፡
©©©
ጠንካራ የጤና ስርዓት ለመገንባት እና የጤና ባለሙያው መብት እንዲከበር ጠንካራ እና አንድ የሆነ ማህበር መኖሩ የግድ ይላል። ስለሆነም ሁላችንም በአንድነት በመቆም የጤና ስርዓታችንን ዘመኑ ከደረሰበት የእድገት ደረጃ አብሮ እንዲጓዝ፤ የጤና ሙያም እጅግ የተከበረና ተፈላጊ ለማድረግ ያለብንን ታሪካዊ ሀላፊነት እንወጣ ዘንድ ማህበሩ ጥሪውን ያቀርባል።
ቅድሚያ ለጤና!
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህር ዳር፣ ኢትዮጵያ

Amhara medical association .pdf
24.5 MB
የአማራ ህክምና ማህበር ለተለያዩ ተቋማት/ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ለክልሉ ጤና ቢሮ፣ለሲቭል ሰርቪስና የሰው ሀብት ኮሚሽን፤ለክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፤ለኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም(ባህርዳር ቅርንጫፍ)፣ለክልሉ ፍትሕ ቢሮ፣ለአማራ ሚዲያ ኮርፐሬሽን/ስለ ጤና ባለሙያዎች የ2018 ዓ.ም ያልተከፈለ ዱቲና ስለ አዲሱ የሰው ሀይል ስምሪት ይፋው ደብዳቤ ፅፏል።ተቋማቱ የማህበሩን ጥያቄ በሚገባ በማጤን መልስ እንደሚሰጡና እንደሚያሰጡ እንጠይቃለን።
ቅድሚያ ለጤና
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህርዳር ኢትዮጵያ
ቅድሚያ ለጤና
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህርዳር ኢትዮጵያ
👍13
አዲስ ዓመት — የፈውስ፣ የጽናትና የሕይወት ተስፋ!
©©©
ውድ የሕይወት ዘበኞች — የሕክምና ባለሙያዎቻችን፤የተወደዳችሁ የአማራና የመላው ኢትዮጵያ ሕዝቦች፤
ዓመታት ይነጉዳሉ፤ ዘመናት ይፈራረቃሉ፤ ነገር ግን በጨለማ ውስጥ ተስፋ ሆኖ መብራት፣ በሚንቀጠቀጡ እጆች መካከል ሕይወትን መታደግ፣ በሕመም ከባድ ሲቃ ውስጥ የፈውስ እፎይታ መሆን የእናንተ የዕለት ተዕለት ቅዱስ ተልዕኮ ነው። ሌላው በሞቀ ቤቱ ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር ሲያሳልፍ፣ በቅዝቃዜው ሌሊትና በሆስፒታል ኮሪደሮች ውስጥ የሰው ሕይወት እንዳይጠፋ የምታደሩት አድር፣ የምትከፍሉት የማይነገር መስዋዕትነት በሰው ዘንድ ብቻ ሳይሆን በፈጣሪም ፊት ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ተግባር ነው።
የታመመውን ሞቅ ባለ ፍቅር የምትቀበሉ፣ የቆሰለውን በጥበብና በትዕግሥት የምትጠግኑ፣ የሕመምተኞችን እንባ የምታብሱና ተስፋ ለቆረጡት አዲስ ሕይወት የምታበስሩ የሕክምና ባለሙያዎቻችን — እናንተ የዚህ ሕዝብ እውነተኛ አለኝታዎችና የጸና ግድግዳዎች ናችሁ!
ወደ አዲሱ 2019 ዓ.ም ስንሸጋገር የአማራ ሕክምና ማህበር ልባዊ ምኞቱን እያቀረበ፣ የሚከተለውን የፀና አቋም ያስተላልፋል።
ሀ) ለሕክምና ባለሙያዎቻችን፦ ድካማችሁ የሚመጥነውን ከፍ ያለ ክብርና ዋስትና እንድታገኙ፣ በሙያችሁ ሳታፍሩና ሳትሰጉ በፍቅር የምታገለግሉበት ምቹና ደህንነቱ የተጠበቀ የሥራ አካባቢ እንዲፈጠር የምናደርገውን ትግል አጠናክረን እንቀጥላለን።
ለ) ለሕሙማኖቻችንና ለህብረተሰባችን፦ እያንዳንዱ ታካሚ በሰውነቱ ብቻ ተከብሮ፣ ሙሉ እንክብካቤና ፈውስ የሚያገኝበት፣ የሰው ሕይወት ከማንኛውም ነገር በላይ ውድ ሆኖ የሚጠበቅበት ዓመት እንዲሆን በጽናት እንቆማለን።
ይህ አዲስ ዓመት እንባ የሚታበስበት፣ የቆሰለው ሕሊናና አካል የሚፈወስበት፣ ስቃይና ሕመም የሚቀልበት፣ ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለሕዝባችን ደግሞ ፍቅር፣ ሰላም፣ እፎይታና አንድነት የሚሰፍንበት ይሁንልን!
አዲሱ 2019 ዓ.ም — የፈውስና የሰላም ዘመን ይሁንልን!
ቅድሚያ ለጤና
የአማራ ሕክምና ማህበር
ባህር ዳር ፣ኢትዮጵያ

👍8👎2
እንኳን ለመስቀል በዓል አደረሳችሁ!
©©©
በመጀመሪያ በሙሉ ጤንነትና በሰላም ለብርሃነ መስቀሉ በዓል አደረሳችሁ!
ደመራ ሲደመር፣ መስቀል ሲሰቀል ጨለማ አልፎ ብርሃን እንደሚተካ ሁሉ፤ የበዓሉ በረከት ለሀገራችን ሰላምን፣ ለህዝባችን ፍቅርንና አንድነትን፣ ለህሙማን ደግሞ ሙሉ ፈውስን ይዞ እንዲመጣ እንመኛለን።
ህይወትን ለማዳንና ህመምን ለመቀነስ በፍቅር፣ በቁርጠኝነትና በትዕግስት የምታገለግሉ የህክምና ሙያተኞች፣ የጤና ባለሙያዎች እንዲሁም መላው የሀገራችን ህዝብ በዓሉ የደስታ፣ የጤናና የሰላም እንዲሆንላችሁ የማህበራችን የዘወትር ምኞት ነው።
በዓሉ የጤና፣ የሰላም፣ የፍቅርና የመደጋገፍ ይሁንልን!
ቅድሚያ ለጤና
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህርዳር፣ ኢትዮጵያ

👍2