ቀን 30/07/18 ዓ.ም
ከአማራ ህክምና ማህበር የተረጠ መግለጫ
የህክምና ባለሙያዎች በአስቸኳይ ይለቀቁ
✍✍✍
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሀኪሞችና በሌሎች የህክምና ባለሙያዎች ላይ እየተከሰተ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግር አደገኛ ደረጃ ላይ ደረርሷል።በዚህም የህክምና ባለሙያዎች ለሞት፤ለግድያ፤ለእስራት፤ለአፈና እንዲሁም ለስደት ተዳርገዋል።ይሄ ደግሞ በሀገራችን ብሎም በክልላችን የህክምና ባለሙያዎች እጥረት ባለበት ሁኔታ "በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ"እንደሚባለው የሀኪሞች እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲከሰት ምክንያት እየሆነ ይገኛል።በዚህም መሰረት ህዝባችን ሀኪም ለማግኘት ርቀት ቦታ እንዲሄድና አላግባብ የሆነ ወጪ እንዲያወጣ እየተገደደ ይገኛል።
✍ በዚህ ሳምንት ብቻ በህክምና ባለሙያዎቻችን ላይ እጅግ አስከፊና ኢሰብአዊ የሆነ ድርጊት እየተፈፀመ ይገኛሉ።
1.ዶክተር አብርሃም አማረ የአማራ ህክምና ማህበርን/Amhara Medical Association/በስራ አስፈፃሚነትና በምክትል ፕሬዚደንትነት ለብዙ አመታት ያገለገለ፤ በእንጅባራ ሆስፒታል የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት እንዲሁም የእንጂባራ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ታስሯል።
2.ዶክተር አስማረ ጌታነህ በደባርቅ ሆስፒታል የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ሐኪም ሲሆን ለደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል አዲስ የተመደበ ለሆስፒታሉ ብቸኛ ስፔሻሊስት ሐኪም ገና ፊቱን እንኳን ያላየነው በዓልን ከቤተሰቤ ጋር አልውልም ለወላድ እናቶችና ለህፃናት መድረስ አለብኝ ብሎ ሲመጣ ታግቷል።
3. ታደሰ እውነቱ በደባርቅ ሆስፒታል የፋርማሲ ባለሙያ ሲሆን መድኃኒት አቅርቦት የሚሰራ ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል መድኃኒት ጭኖ ሲመጣ ታግቷል።
4. መሳፍንት ሰረበ የደባርቅ ሆስፒታል ሹፌር ሲሆን ወላዶችን ሪፈር ሲባሉ ወደ ጎንደር የሚያመላልስ ጥዋት ሪፈር ወስዶ ከስዓት መድኃኒት እና ባለሙያዎችን ሲያመጣ ታግቷል።
✍ስለዚህ መንግስት የሀኪሞችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለበት ሙሉ ሃላፊነትና ግዴታ ስላለበት እነዚህን ባለሙያዎቸ ከነሙሉ ጤንነታቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ቤታቸውና ወደ ስራ ቦታቸው እንዲመልሳቸው ስንል እንገልፃለን።
✍ባለሙያዎችን ያገታቹህ አካላት ሆይ የታገቱት ሀኪሞች እናትህን፣ አባትህን፣ ሚስትህን፣ ልጅህን፣ ወንድምህን፣ እህትህን የሚያክሙ ወገኖችህ መሆናቸውን አውቃቹህ በፍጥነት ትለቋቸው ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
✍✍✍
ቅድሚያ ለጤና
የአማራ ህክምና ማህበር
ባ/ዳር
ኢትዮጵያ

👍5
ከአማራ ህክምና ማህበር
ቀን 1/08/18 ዒ.ም
✍✍✍
✍የደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያዎች ከእገታ በመለቀቃቸው እጅግ በጣም ደስ ብሎናል።
እንኳን ደስ አለን/አላቹህ።
✍የታገታቹህ ወንድሞቻችን እንኳን በሰላም ወደ ቤታቹህ፤ ወደ ምትወዱትና በቅንነት ወደ ምታገለግሉት ማህበረሰብ በሰላም ተቀላቀላቹህ።
✍ሀኪሞችን ያገታቹህ ወገኖቻችን ወንድሞቻቹህን ምንም ጉዳት ሳታደርሱ በመልቀቃቹህ ደስታችን ወደር የለውም።
✍ለወደፊቱም የጤና ባለሙያ በማንኛውም ሰአትና ጊዜ በነፃነት መንቀሳቀስ እንዳለበት አውቃቹህ ከማገት ይልቅ ልዩ ጥበቃ እንድታደርጉላቸው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
✍የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በተለይም የደባርቅና የዳባት ማህበረሰብ ልጆች እንዲለቀቁ ያደረጋቹህት ጥረት ታሪክ የማይረሳው ጉዳይ ነው።በርቱልን።ወደፊትም ለጤና ባለሙያው ልዩ እንክብካቤ ታደርጉላቸው ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
✍የዲጂታሉ ዓለም ማህበረሰብ ያደረጋቹህት ርብርብ እጅግ አስደማሚ ነበር።በጣም እናመሰግናለን።ለወደፊቱም በማንኛውም ጉዳይ ከጤና ባለሙያዎች ጎን ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
✍በመጨረሻም መንግስት የታሰሩ ባለሙያዎችን እንዲፈታልንና ለጤና ባለሙያዎች ልዩ ጥበቃ እንዲያደርግልን እንዲሁም የተጠየቁት ጥያቄዎች በሙሉ ምላሽ እንዲያገኙ በድጋሜ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

👍6
የአማራ ህክምና ማህበር የዶ/ር አበበን ቤተሰቦች አፅናኑ
✍✍✍
🟣የአማራ ህክምና ማህበር በቅርቡ ህይወቱ ያለፈውን የዶ/ር አበበ መኮነን ቤተሰቦችን በ03/08/18 ዓ.ም አፅናንተዋል።የማህበሩ ፕሬዚደንት እንደተናገሩት ዶ/ር አበበን እስከምናውቀው ድረስ ምንም የጤና እክል ያልነበረበት ውድ ጓደኛችንና ወንድማችን ነበር ብለዋል።
🟣ነገር ግን ፈጣሪን ለምንና እንዴት ይሄን አደረክ ማለት ስለማንችል ከእኛ የሚጠበቀው መፅናናትና የእምነቱ ስርአት የሚያዝዘውን ማድረግ፤ያሰባቸውን እቅዶች ከዳር ማድረስና የእርሱን ጀግንነት ለልጆቻቹህ እየነገራቹህ በልጆቻቹህ ልብ ውስጥ እንዲኖር ማድረግና የእርሱን አሻራ እንዲከተሉ ማድረግ ነው። የዚያን ጊዜ ዶ/ር አበበ ህያው እንደሆነ ምስክር ትሆናላቹህ ብለዋል።
🟣ዶ/ር አበበ በጣም ቅን፤ትሁት፤ግልፅ፤ተግባቢ የነበረ ሲሆን በጣም የሚያሳዝነው ከበርሃ እስከ ደጋ እየተንከራተተ ምንም እረፍት ሳያገኝ ማረፉ ነው።ያም ሆነ ይህ ዶ/ር አበበን መመለስ አንችልም።ነገር ግን በእናንተና በልጆቻቹህ ስራ ህያው ሆኖ እንደምናዬው ተስፋ አለን ብለዋል።
🟣በመጨረሻም የወንድማችንን ነፍስ በአፀደ ገነት እንዲያኖርልን በፀሎት ፈፅመዋል።
ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹ በድጋሜ መጽናናትን ይስጥልን።

👍4
ከአማራ ህክምና ማህበር
ቀን 03/08/18 ዓ.ም
ዶ/ር አብርሃም አማረ እንኳን ተፈታህ
✍✍✍
🟣ለረጅም አመታት የአማራ ህክምና ማህበር ስራ አስፈፃሚና ምክትል ፕሬዚደንት እንዲሁም በእንጅባራ ሆስፒታል የአጥንት ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስትና የእንጅባራ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን እንኳን በሰላም ወደ ወገኖችህና በቅንነት ወደ ምታገለግለው ህዝብ ተቀላቀልክ።የምታገለግለው ህዝብ ላንተ ያሳየው ፍቅር እጅግ አስደማሚና የሚደንቅ ነበር።አንተም ማህበረሰብህን የበለጠ እንደምታገለግላቸው ጥልቅ የሆነ መልእክት ነበር ያስተላለፉት።
🟣የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በተለይም የእንጅባራ ማህበረሰብ ዶ/ር አብርሃም እንዲፈታ ያደረጋቹህት ጥረት ታሪክ የማይረሳው ጉዳይ ነው።በርቱልን።ወደፊትም ለጤና ባለሙያው ልዩ እንክብካቤ ታደርጉላቸው ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
🟣የዲጂታሉ ዓለም ማህበረሰብ ያደረጋቹህት ርብርብ እጅግ አስደማሚ ነበር።በጣም እናመሰግናለን።ለወደፊቱም በማንኛውም ጉዳይ ከጤና ባለሙያዎች ጎን ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

👍7
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ! በዓሉ የሰላም: የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
"ቅድሚያ ለጤና"
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህር ዳር: ኢትዮጵያ
"ቅድሚያ ለጤና"
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህር ዳር: ኢትዮጵያ
የድረሱልኝ ጥሪ
✍✍✍
ዶ/ር አስናቀው የሁላችንንም እጅ ይፈልጋል!
የሰው ልጅ ህመም ሰምቶ የማይተኛው፣ ሌሎችን ለማዳን የህክምና መሳሪያ ይዞ የሚባክነው ወንድማችን ዶ/ር አስናቀው ደሳለኝ ዛሬ ራሱ በህመም አልጋ ላይ ሆኖ የሁላችንንም እገዛ እየተማጸነ ይገኛል።
✍ከዚህ ቀደም በወገኖቹ ድጋፍ ወደ ህንድ ሀገር ለህብረሰረሰር እጢ ቀዶ ጥገና ሄዶ የነበረ ቢሆንም፣ እዚያ እንደደረሰ ግን ያልታሰበ ሌላ መርዶ ተሰማ። በምርመራ ወቅት ከጀርባው እጢ በተጨማሪ ጭንቅላቱ ላይ ሌላ እጢ ተገኘበት። ዶ/ር አስናቀው በታላቅ ጥንካሬ ሁለቱንም ከባድ ቀዶ ጥገናዎች አድርጓል።
✍ፈተናው ግን ገና አላበቃም! ከቀዶ ጥገናው በኋላ በተደረገ ምረመራ (Control MRI)፣ አሁንም ትንንሽ እጢዎች በሰውነቱ ውስጥ እየታዩ ነው። ሀኪሞች እነዚህን እጢዎች ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት አስቸኳይ የጨረር ህክምና (Radiation) እንደሚያስፈልገው ወስነዋል።
ይህ አዲስ የህክምና ሂደት ደግሞ ካቀደውና ከነበረው አቅም በላይ ሆኖበታል። ለዚህ ህክምና ተጨማሪ 1.8 ሚሊዮን ብር አስቸኳይ ክፍያ ይጠበቅበታል። በገንዘብ እጥረት ምክንያት ህክምናው ተቋርጦበት በሰው ሀገር ተስፋ በቆረጠ ሁኔታ ላይ ይገኛል።
ኢትዮጵያውያን ወገኖች፣ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የክልልና የዞን ጤና ቢሮዎች! ይህ ወጣት ባለሙያ ገና ብዙ ህይወት ሊታደግ፣ ብዙ ወገኖቹን ሊያገለግል የሚችል የሀገር ተስፋ ነው። ዛሬ ግን የእርሱ ህይወት በእጃችሁ ናት። ዶ/ር አስናቀው ወደ ሀገሩና ወደ ስራው ተመልሶ ወገኖቹን ማዳን እንዲችል፣ እባካችሁ አቅማችሁ የፈቀደውን በማድረግ ህይወቱን እንታደግ።
መርዳት ለምትፈልጉ
CBE:1000066288106/አስናቀው ደሳለኝ
zell:301-640-8908/Banchamlak Betew
Gofund:https://gofund.me/5ed59baf4
ቅድሚያ ለጤና
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህርዳር