ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን/ሳችሁ! በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆንልን/ዎ እንመኛለን። ዒድ ሙባረክ!!!
ቅድሚያ ለጤና!!!
አማራ ህክምና ማህበር
ባህር ዳር
ኢትዮጵያ
መጋቢት,2018 ዓ/ም
ቅድሚያ ለጤና!!!
አማራ ህክምና ማህበር
ባህር ዳር
ኢትዮጵያ
መጋቢት,2018 ዓ/ም
👍3
ቀን:18/07/2018 ዓም
ከአማራ ህክምና ማህበር የተሰጠ መግለጫ
✍✍✍
የአማራ ህክምና ማህበር ከ20ዐ8 ዓም ጀምሮ ለህክምና ባለሙያዎችና ለማህበረሰቡ ይበጃሉ ያላቸውን ዘርፈ ብዙ ስራዎች ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር አመርቂ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ የሙያ ማህበር ነው። በተለይም ደግሞ አሁን ባለው ወቅታዊና አንገብጋቢ የጤና ሙያተኞች ጥያቄዎች መልስ ባለማግኘታቸው ምክንያት በጤና ሙያተኛው መብትና ግዴታዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
✍የጤና ባለሙያዎች ከወራት በፊት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከወቅቱ የኑሮ ውድነትና ከሙያው ባህሪ ጋር ተያያዥ የሆኑ የጥቅማጥቅምና የመብት ጥያቄዎችን ሲያነሱ መቆየታቸው ይታወቃል። ይህን ተከትሎም መንግስት
ወቅታዊ ሁኔታውን ታሳቢ በማድረግ ለሁሉም የመንግስት ሰራተኞች ሀገር አቀፍ የደሞዝ ጭማሪ በማድረግ የኑሮ ውድነቱን በተወሰነ መልኩ ለማስተካከል የተሞከረበት ሁኔታ መኖሩን እናስታውሳለን።
✍ይሁን እንጅ መንግስት ያወጣውን የደሞዝና ተያያዥ የጤና ሙያተኞች የጥቅማጥቅም መመሪያዎች ተፈጻሚ ባለመሆናቸው ምክንያት ከወራት በፊት በጤና ሙያተኞች የተጠየቁት ጥያቄዎች ምንም ዓይነት ምላሽ ባለማግኘታቸው ሙያተኞች ተረጋግተው ስራቸውን እንዳይሰሩ ከፍተኛ እንቅፋት እየፈጠረ ይገኛል። የአማራ ህክምና ማህበርም ወጥ የሆነ የደሞዝና የትርፍ ሰዓት ክፍያ እና ሌሎችንም ጥያቄዎች በመያዝ ከሚመለከታቸው ከፍተኛ የክልሉ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ውይይቶችን ስናደርግ መቆየታችን ለማስታወስ እንወዳለን።
✍ነገር ግን "የበጀት እጥረትና ከአቅማችን በላይ ነው" የሚል ምላሽ ከመስጠት ውጭ ኃላፊነቱን ወስዶ ምላሽ የሚሰጥ አካል ባለመኖሩ በህክምና ሙያተኞች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየፈጠረ ይገኛል። ስለሆነም በጤና ሙያተኞች ከዚህ በፊት የተጠየቁ ጥያቄዎች በሙሉ ደረጃ በደረጃ ምላሽ እንዲሰጥባቸው እያሳሰብን የፌደራል መንግስቱ ያወጣውን መመሪያ ወደ መሬት በማውረድ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት አንገብጋቢ ጥያቄዎች ግን የሚመለከተው የመንግስት አካል በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ እንጠይቃለን።
1. የትርፍ ሰዓት ክፍያና የተጨማሪ ስራ ክፍያን በተመለከተ፦ የጤና ሙያተኛው በከፍተኛ ጫና ውስጥ ሁኖ
ከ7 ወር በላይ የሰራውን የትርፍ ሰዓት ክፍያ በአስቸኳይ አንዲከፈል፡
2. የተጋላጭነት ክፍያን በተመለከተ፦ የጤና ሙያተኛው በስራው ባህሪ ምክንያት ለተላላፊ በሽታዎች
ተጋላጭነቱ ከፍተኛ በመሆኑ የሚከፈለው የተጋላጭነት ክፍያ አንዲከፈል፡
3. ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎትን በተመለከተ፦ በስራው አስገዳጅነትና አሁን ባለው አለም ዓቀፋዊና አገር
ዓቀፋዊ ችግሮች ምክንያት በጤና ሙያተኞች ላይ ከፍተኛ ጫና አያሳደረ ስለሆነ መንግስት ነጻ
የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያመቻች እና
4. የመኖሪያ ቤትን በተመለከተ ደግሞ መንግስት ለህክምና ባለሙያዎች ነጻ የቤት መስሪያ መሬት ወይም
የረጅም ጊዜ ብድር አገልግሎተ እንዲያመቻች በአንክሮ አንጠይቃለን።
“ቅድሚያ ለጤና”
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህር ዳር፥ ኢትዮጵያ

👍9
Dn Dr Tadesse Fenta:
ለኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር
አዲስ አበባ
ጉዳዩ:- የህክምና ባለሙያዎች ጥያቄ እንዲመለስ ስለመጠየቅ
✍የአማራ ህክምና ማህበር /AMA/ የበጎ አድራጎት ድርጅትና ማህበራትን ለመመዝገብና ለማስተዳደር በወጣው አዋጅ ቁጥር 194/5004 መሰረት በ2008 ዓ.ም የተቋቋመ መሆኑና ከተቋቋመ ጀምሮም የተስራዎችን እየሰራ ያለ ማህበር ነው።ማህበሩ ከሚሰራቸው ወርፈ ብዙ ስራዎች መካከል የህክምና ባለሙያዎችን መብት ማስጠበቅና መጠየቅ ነው።የህክምና ባለሙያዎች በተደጋጋሚ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች እስካሁን መሬት ላይ የወረደ መልስ ባለማግኘታቸው በተለያዩ መንገዶች ስሜታቸውንና ቅሬታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።ይሄ ደግሞ ቋሚና ዘላቂ
መፍትሔ ካልተበጀለት ጤና ተቋማት ውጤታማ ስራ ለመስራት እየተቸገሩ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ለማህበራችን ሲገልፁ ቆይተዋል።ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና ባለሙያዎችን ጥያቄ በቅንነት ተገንዝቦ ባጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ ስንል በፅኑ እንጠይቃለን።የባለሙያዎችንም ጥያቄ በ 04 ገፅ አባሪ አድርገን ልከናል።
ቅድሚያ ለጤና
የአማራ ህክምና ማህበር
ከህክምና ባለሙያዎች መብት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥያቄዎች
✍✍✍
1. የትርፍ ሰዓት ክፍያን በተመለከተ:- በሀገር አቀፍ ደርጃ ወጥ የሆነ የትርፍ ሰዓት ክፍያ አከፋፈል አዋጅ የተፈቀደና የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከታህሳስ 07/2018 ዓም ጀምሮ የአከፋፈል መመሪያ ያወረደ ቢሆንም ክልሎች ብሎም አሰሪ ተቋማት ግን የተለያየ አይነት የትርፍ ሰዓት ክፍያ አሰራር ሂደትን ሲከተሉ እናያለን።
ይህም ጉዳይ በህክምና ሙያተኞች ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታን እየፈጠረ ይገኛል። ይባስ ብሎ በአሁኑ ወቅት ደግሞ የትርፍ ሰዓት ክፍያ በአዲሱ የደሞዝ ስኬል መሰረት በሰአቱ እየተከፈለ አለመሆኑና የትርፍ ሰዓት አቆጣጠር የምሳ ሰዓትን ማለትም /ከ6:30-7:30/ በትርፍ ሰዓት እንደሚሸፈን እየታወቀ ከትርፍ ሰዓት ስራ ላይ ስለማይደመር በባለሙያው ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ቅሬታን እያስከተለ ይገኛል። ስለሆነም ክፍያው በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ታህሳስ 07/2018 ዓ.ም በወጣው መመሪያ መሰረት በወቅቱና በአግባቡ እንዲከፈል እንጠይቃለን።
✍ከላይ የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ በዱቲ አከፋፈል ስርአት አንድ ሰው ከ212 ሰአት በላይ መስራት የለበትም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም በኮሚሽን በኩል አስፈቅዶ ነው የሚለው አንቀፅ ፈፅሞ የተሳሳተ እንዲሁም ግልፀኝነት የገደለው በመሆኑ ከአዋጁ እንዲነሳ ይደረግ።ለስራ ፈፅሞ እንቅፋት የሆነ ውሳኔ ስለሆነ።
2. የደሞዝ ክፍያን በተመለከተ፡- የህክምና ባለሙያዎች የደሞዝና የደረጃ እድገት መጠን ከሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ሲወዳደር እጅግ በጣም የወረደ በመሆኑ የትምህርት ዝግጅትንና የሙያውን ክብር በሚመጥን መልኩ የደመወዝ ማስተካከያ እንዲደረግላቸው እንጠይቃለን።
3. የተጋላጭነት ክፍያን በተመለከተ፦ የህክምና ባለሙያዎች ለተለያዩ ተላላፊና ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች እጅጉን ተጋላጭ ናቸው። ለዚህም እንድማሳያ በቅርቡ በዓለም አቀፍ ብሎም በሀገራችን የተከሰተው ወረርሽኝ /Covid- 19 and Marburg virus/ እና ጦርነት ዋና ምስክር ናቸው። ስለዚህ ይህን ታሳቢ ተደርጎ ወቅቱን ያማከለ የተጋላጭነት አበል ክፍያ እንዲታሰብ እንጠይቃለን።በተጨማሪም ከፍተኛ ተጋላጭ ቦታ ላይ እየሰሩ ጭራሽ የማይከፈላቸው የህክምና ባለሙያዎች አሉ/ለምሳሌ ቀዶ ህክምና ውስጥ የሚሰሩ ነርሶች/።ይሄ ትክክል ስላልሆነ ጥናት ተደርጎበት መስተካከል አለበት።
4.ለድንገተኛ ህክምና ታካሚዎቻችን ሲባል የህክምና ባለሙያዎቻችን ከጤና ተቋሞቻችን በቅርብ ርቀት ሆነው ማገልገል ስለሚገባቸው በየሆስፒታሎች ወቅቱን ባገናዘበ (በብዛትም በጥራትም) መልኩ ቤቶች እንዲገነቡና የቤት ኪራይ አበልም ነባራዊ ሁኔታውን ባገናዘበ መልኩ ተስተካክሎ እንዲከፈል (አሁን የሚከፈለው የቤት ኪራይ አበል ክፍያ ማለትም 1000 ብር ለሳምንት የታክሲ ክፍያንም መሸፍን ስለማይችል በሚገባ ማጤን እንዲቻል)።አብዛሃኛው የህክምና ባለሙያ የቤት አበል አይከፈለውም።ስለዚህ ይሄን ከግምት ውስጥ በማስገባት ክፍያው እንዲስተካከልና እንዲፈፀም።
5. Top Up /Clinical allowance/ ተብሎ የሚከፈለው ክፍያ እጅጉን ከመጠን በታች በመሆኑ ወቅቱን ታሳቢ ተደርጎ እንዲስተካከል እንጠይቃለን።የማይከፈላቸው የህክምና ባለሙያዎችንም እንዲያካትት።
6. የህክምና ባለሙያዎች ወደ ጤና ተቋም ለመሄድ የትራንስፖርት ወረፋ/ሰልፍ እየጠበቁ ወደ ጤና ተቋም በሰዓቱ ለመድረስ እየተቸገሩ ስለሆነ ሰርቪስ እንዲመቻች።ይህ ካልሆነ ግን የትራንስፖርትና የነዳጅ አበል ክፍያ ታሳቢ ተደርጎ እንዲከፈል።እንዲሁም ከቀረጥ ነፃ የመኪና ግዥ ስርዓት እንዲዘረጋና እንዲመቻችላቸው።
7. በበረሃና በጮቄ ለሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎች የበረሃ አበል ክፍያና የጮቄ አበል ክፍያ እንዲታሰብላቸው።
8. ከላይ ከቁጥር 1 ጀምሮ የተዘረዘሩት በሙሉ ከግብር ነፃ እንዲሆኑ/ከደሞዝ በቀር/ እንዲደረግላቸው።
9. የቤት መሥሪያ ቦታን በተመለከተ:- የህክምና ባለሙያዎች ለትምህርትና ለስራ ከቦታ ቦታ በየጊዜው እንደሚንቀሳቀሱ ይታወቃል። ስለሆነም ይህን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የቤት መስሪያ ቦታ በዜሮ አመት እንዲሰጥና ለቦታው የሚያስፈልገው የካሳ ክፍያም በመንግስት እንዲሸፈንላቸውና ወጥ የሆነ አሰራር ለክልሎች እንዲወርድ።
10. የብድር አገልግሎትን በተመለከተ፡- ከተለያዩ ባንኮች ጋር ውል በመያዝ የረጅም ጊዜ የብድር አገልግሎት እንዲመቻችላቸውና የሙያ ፈቃዳቸውንም እንደ ሶስተኛ ወገን ተቆጥሮ ለብድር ማስያዣነት እንዲያገለግል አሰራር እንዲዘረጋ።
11.የጤና ባለሙያዎች ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ከ12 በላይ መሠረታዊ ጥያቄዎችን እንደ ሀገር በየደረጃው ለሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ማቅረባቸው ይታወቀል።እነዚህን ጥያቄዎች መንግስት ያመነባቸውና ትክክል መሆናቸውን በተለያዩ መድረኮች ሲገልፅ ቆይቷል። ነገር ግን እንደ ሀገርም እንደ ክልል የተነሱ ጥያቄዎችን በቸልተኝነት እየታለፉ ነው። ስለዚህ ጥያቄዎችን በቅንነት ተመልክታቹህ ወጥ የሆነ መልስ እንድትሰጡ።
12. የተጀመረው የጤና መድህን አገልግሎት ሁሉንም ዓይነት ህክምናዎች ያካተተ እንዲሆን፡ ከሆስፒታል ውጭ ለሚሰሩ የምርመራ ውጤቶችና የመድሃኒት ግዢ ሂሳብ እንዲወራረድና ከሀገር ውጭ ለሚሰጡ የህክምና ወጭ ሙሉ በሙሉ በመንግስት እንዲሸፈን እንዲደረግላቸው።
13. የህክምና ስህተቶች ሲፈጠሩ ሆነ ሳይፈጠሩ በሙያዊ ትንታኔ ሳይሆን ምክንያቱና ምንጩ ባልታወቀ ሁኔታ ሚዲያዎች በሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት ማህበረሰቡ በጤና ተቋማትና በሙያተኞች ላይ እምነት እንዲያጣ በር ይከፍታል። ለዚህ ደግሞ መንግስት ለሚዲያዎች ልጓም ሊያበጅላቸውና አሰራር ሊዘረጋላቸው ይገባል።
14. የሙያ ማህበራት ለማህበረሰቡ የሚያደርጉትን አስተዋፅኦ ግምት ውስጥ በማስገባት መንግስት ለእነዚህ ማህበራት በቂ ድጋፍና ከትትል በማድረግ ለማህበረሰቡ የበኩላቸውን እንዲወጡ እንዲደረግ።

15.በመጀመሪያ ደረጃም ሆነ በጠቅላላ ሆስፒታል ደረጃ በትርፍ ሰዓት ስራ ላይ የሚመደበው ስፔሻሊስት ሃኪም አንድ በመሆኑ የተነሳ ስራውን አቀላጥፎ ለመስራት ስለሚያስቸግር የስፔሻሊስት ሃኪሞች የትርፍ ሰዓት ስራ ላይ ተጨማሪ ስፔሻሊስት ሃኪም የሚጨመርበት ሁኔታ እንዲመቻች።
16.የሬዚደንት ሀኪሞች እያከሙ ስለሚማሩ የትምህርት ቤት የቆይታ ጊዜያቸው እንደ አግልግሎት እንዲቆጠርና አሰራር እንዲዘረጋ ።
እናመሰግናለን

👍4
አሳዛኝ ክስተት
✍✍✍
በቡሬ ከተማ አስራደ ሆስፒታል የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት የነበረውና ማህበረሰቡን በቅንነት ሲያገለግል የነበረው አንጋፋው ዶክተር አበበ መኮነን በድንገት ከዚህ አለም በሞት ተለይቶናል።
✍ወንድማችን የመጀመሪያ ድግሪውን በዶክትሬት ድግራ ከአንጋፋው ጅማ ዩኒቨርስቲ በ2010 ዓ.ም የተመረቀ ሲሆን የቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ትምህርቱን ደግሞ በ2016 ዓ.ም ከአንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርስቲ ተመርቋል።ዶ/ር አበበ መኮነን በጣም ቅን፤ሩህሩህ፤ተጫዋች እንቁ ሀኪም መሆኑን ብዙዎች ይመሰክሩለታል።ለወገኖቹ በህክምናው ዘርፍ ዘርፈ ብዙ አገልግሎትን ያበረከተ አንጋፋ ሀኪም ነበር።
✍ለወገኖቹ ሻማ የሆነው ወንድማችን እሱ ራሱ ግን ህክምና ሳያገኝ/ሳይደረግለት በድንገት ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል።
✍ማሳሰቢያ:የሀኪሞች ሞት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ አስፊ ደረጃ ላይ ደርሷል።የክልል ጤና ቢሮዎች፤ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፤ዩኒቨርስቲዎች ይሄ ነገር በፍጥነት ጥናት ሊደረግበት ና መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል።
የወንድማችንን ነፍስ ይማርልን።ለቤተሰቦቹና ለወዳጆቹ መፅናናትን እንመኛለን።
✍✍✍
ቅድሚያ ለጤና
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህርዳር

👍1