Amhara Medical Association(AMA)
691 subscribers
211 photos
2 videos
19 files
145 links
Amhara medical Association is all about quality of medical care and physicians satisfaction in the nation.
Download Telegram
ጥምቀትን በባህርዳር የአማራ ህክምና ማህበር/Amhara medical association/ከአማራ ክልል ጤና ቢሮና ከባ/ዳር ከተማ ጤና መምሪያ ጋር በጋራ በመሆን የድንገተኛ ህክምና ቡድን አቋቁሞ በሁለቱም  ባህረ ጥምቀት አገልግሎት  እየሰጠ ይገኛል።በአለም ላይ ያላቹህ ክርስቲያኖች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ አመታዊ የጥምቀት በአል አደረሳቹህ። በአለም የቅርስ መዝገብነት ላይ የተመዘገበውን የጥምቀት በአል ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ለማህበረሰቡ አገልግሎት በመስጠት የአማራ ህክምና ማህበር/Amhara Medical Association/በማሳለፉ እጅጉን ደስታ ይሰማዋል።በሁሉም  ቦታ በአሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ማህበሩ ምኞቱን ይገልፃል።ለወደፊትም በታላላቅ  የአደባባይ በዓላት ላይ ማህበሩ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመሆን በመስራት ለማህበረሰቡ የቅርብ ደራሽ ተቋም እንደሚሆን ፍፁም እምነት አለን።በየትኛውም ቦታ ያላቹህ የህክምና ባለሙያዎች የማህበሩ አባል በመሆን ማህበሩን የወደፊት የሀገር ተስፋ ማህበር እንዲሆን ታደርጉት  ዘንድ ጥሪውን ያስተላልፋል።ማህበሩ የእናንተው ውጤት ነው።ሁልጊዜም ማህበሩ ከእናንተው ጋር ነው።በድጋሜ እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በአል አደረሳቹህ።

የአማራ ህክምና ማህበር/Amhara  Medical Association/
ባህርዳር
ኢትዮጵያ
👎2👍1
በሰላም ተጠናቋል
❤️❤️❤️
✍በባህርዳር በሁለቱም ባህረ ጥምቀት ሲካሄድ የነበረው የጥምቀት ስርአት በሰላም በመጠናቀቁ የአማራ ህክምና ማህበር/Amhara Medical Association /ደስታውን ይገልፃል።በሁለቱም ጥምቀተ ባህር የህክምና ቡድን ተቋቁሞ አገልግሎት በመሰጠቱና በስኬት በመጠናቀቁ እጅግ ደስ ብሎናል።ወደፊትም በተለያዩ ቦታዎች የሚካሄዱ የአደባባይ በአላት ላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ማህበሩ  በፅኑ ያምናል።የዘንድሮው አገልግሎት ትልቅ ትምህርት የወሰድንበት ነበር።ለወደፊቱ የተደራጀና ወጥ እንደሚሆን ባለሙሉ ተስፋ ነን።

✍ማህበሩ  የተቋቋመው 2008 ዓ.ም በአማራ የህክምና ባለሙያዎች የተቋቋመ ሲሆን አንጋፋ ሀኪሞች በፕሬዚዳንትነት መርተውታል።ዶ/ር ጋሹ ክንዱ፤፤ዶ/ር በቃሉ ውብሸት፤ዶ/ር መልካሙ አብጤ፤ዶ/ር አብራራው ታደሰ ማህበሩን  ይመሩ የነበሩና ማህበሩን ለዚህ ትውልድ ያስረከቡ አንጋፋ ሀኪሞች ናቸው።
✍ማህበሩ የበጎ አድራጎት ማህበር  ቋሚ የሆነ የበጀት ምንጭ የለውም/ ከአባላት ክፍያ በቀር/።ስለዚህ ውድ የህክምና ባለሙያዎች ማህበር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተረድታቹህ ሁላቹህም አባል ትሆኑ ዘንድና ማህበሩን ታጠነክሩት ዘንድ ማህበሩ በክብር ይጠራቹሃል።ማህበሩ ላለፉት ጥቂት አመታት በተለያዩ ምክንያቶች ብዙም እንቅስቃሴ ሳያደርግ መቆየቱ ሁላችንም የምናውቀው እውነት ነው።ግን አሁን ወደ ሙሉ አቅሙ ለመመለስ እየታገለ ያለ ማህበር ነው።በዚህ ወቅት ከጎናችን ሆናቹህ ልታግዙን ይገባል።ባህር ውስጥ የገባችን ህፃን ለማውጣት ከውጭ ሆኖ መጮህ/ማልቀስ ምንም አይጠቅምም።ወደ ባህሩ ጠልቆ መግባት ያስፈልጋል።እናም ከውጭ ሆኖ መተቼት የትም አያደርስም።ስለዚህ ወደ ማህበሩ ግቡና ማህበሩን የወደፊት የሀገር ኩራት ማህበር አድርጉት።
መልካም የጥምቀት በአል ይሁንልን።
✍✍✍
የአማራ ህክምና ማህበር
/Amhara Medical Association
ባ/ዳር
ኢትዮጵያ
👎2
ለጤና ባለሙያዎች የተዘጋጀ/For All health professionals/
✍✍✍
የአማራ ህክምና ማህበር /AMA/ በ2008 ዓ.ም የተመሰረተ ማህበር ነው።ማህበሩ መስከረም 25/2018 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄዱ ይታወቃል።በዚች ጥቂት ወራት የቦርድ አመራርና ዳይሬክተሮች ሁልጊዜም በየሳምንቱ ስብሰባ እያደረጉ የሚከተሉትን ስራዎች አከናውኗል።
1.ማህበሩን ባዲስ መልኩ ለማደራጀት ተሞክሯል
2.የጤና ባለሙያውን ጥያቄ የሚመለከታቸው አካላትን እየጠየቀ ይገኛል።እልባት እስኪገኝ ድረስ እስከመጨረሻው መጠየቁንም ይቀጥላል።
3.ባ/ዳር በሚገኘው ሁለቱ ጥመቀተ ባህር ከጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የህክምና ቡድን አቋቁሞ አገልግሎት ሰጥቷል።ወደፊትም ይሰጣል።
ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ለጤና ባለሙያዎች ትልቅ እድል ከፍቷል።የማህበሩ አንዱ አላማ ተመራማሪና መዋቅራዊ እሳቤ /Researcher and Systemic Thinker/ ያላቸው የህክምና ባለሙያዎችን ማፍራት ነው።ይሄን ለማድረግ የማህበሩ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ስለ ጥናትና ምርምር/Research training from Basic to advanced/አዘጋጅቷል።ማንኛውም ፍላጎት ያለው የጤና ባለሙያ መሳተፍ ይችላል።ቅድሚያ የተመዘገበ በቅድሚያ እድል ይሰጠዋል።በሚከተለው የመመዝገቢያ ቅፅ መመዝገብ ይቻላል።
https://forms.gle/UnewQLPjQZPpH1TU9
❤️❤️❤️
የአማራ ህክምና ማህበር
Amhara Medical Association
ባ/ዳር
አትዮጵያ
👍2
አስደሳች ዜና ለሁሉም ጤና ባለሙያዎች
        ከአማራ ህክምና ማህበር

የአማራ ህክምና ማህበር አዲስ ስራ አሰፈፃሚወች ፤ ዳይሬክተሮችና የዞን አመራሮች በአዲስ መልክ ከተመረጡ ጊዜ ጀምሮ  የተለያዩ ስራወችን እየሰራ ይገኛል።ማህበሩ ከተቋቋመባቸው አላማዎች ውስጥ አንዱ ከህክምናው በዘለለ በጥናትና ምርምር ማህበረሰባቸውን ማገልገል ለሚፈልጉ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ነው። በመሆኑም በአማራ ህክምና ማህበር በጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት በኩል የተዘጋጀ የጥናት እና ምርምር ስልጠና የፊታችን አርብና ቅዳሜ(በ 29 & 30, 2018 ዓ/ም) ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች ለመስጠት ዝግጅቱን ጨርሶ በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል። ስልጠናው በመሠረታዊ የጥናትና ምርምር ክህሎቶች የሚያተኩር ሲሆን በኦንላይ እንደሚሰጥና ሰርቲፊኬትም እንደሚኖረው ገልፀዋል።በመሆኑም  መሣተፍ ለምትፈልጉ ማንኛውም የጤና ባለሙያዎች ከታች በምናስቀምጠው ሊንክ ገብታችሁ መመዝገብና በጥናትና ምርምር የካበተ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ስልጠናውን መውሰድ ትችላላችሁ።

👇👇👇

https://forms.gle/UnewQLPjQZPpH1TU9

     አማራ ህክምና ማህበር
     የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት
     ባህር ዳር
      ኢትዮጵያ
👍5👎1
የሀዘን መግለጫ///
በዶ/ር ጸጋሁን ስሜ በ26/05/2018 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ በድንገት ህይወታቸው በማለፉ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል!!!
ዶ/ር ጸጋሁን የህክምና ትምህርታቸውን በመቀሌ ዩኒቨርስቲ በ2011 ዓም ካጠናቀቁ በኋላ በጠቅላላ ሐኪምነት ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ የአማራ ጤና ቢሮ ባልደረባ በመሆን ህዝባቸውን በቀናነት ሲያገለግሉ የነበሩ ሀኪም ነበሩ።
እንዲሁም የአማራ ህክምና ማህበር አባል የነበሩ ሲሆን ትናንት 26/05/2018 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ በድንገት ህይወታቸው አልፏል።
በዶ/ር ጸጋሁን ስሜ ድንገተኛ ህልፈተ ህይዎት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን በድጋሚ እየገለጽን መንግስት የሀኪሙን አሟሟት ምክንያት በትክክል እንዲያጣራና ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ እንጠይቃለን።
ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና የስራ ባልደረቦቹ መጽናናትን እንመኛለን።
የአማራ ሕክምና ማህበር
ባህርዳር , ኢትዮጵያ///
ሰላም ውድ የአማራ ህክምና ማህበር አባላት።አርብና ቅዳሜ ሊካሄድ የነበረው የጥናትና ምርምር ስልጠና በዶ/ር ፀጋሁን ስሜ አሳዛኝ ህልፈተ ህይወት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።ማህበሩ በወንድማችን ህልፈተ ህይወት ጥልቅ ሀዘን ውስጥ በመሆኑ ለጊዜው ማራዘማችንን እንገልፃለን።የወንድማችንን ነፍስ በአፀደ ገነት ያኑርልን
👍11
የሐዘን መግለጫ

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 6ኛ ዓመት የሕክምና ዶክትሬት ተማሪ (ኢንተርን ሐኪም) የነበረው ዶ/ር በውቀቱ አንዳርጌ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

በኢንተርን ሐኪሙ ኅልፈተ-ሕይወት የተሰማንን ጥልቅ ኀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቹ፣ ለጓደኞቹ እና ለመላው ማህበረሰባችን መጽናናትን እንመኛለን።

     አማራ ህክምና ማህበር
     ባህር ዳር
      ኢትዮጵያ
ሰላም ወድ ቤተሰቦች::የአባልነት ክፍያ እየከፈልን ሃላፊነታችንን እንወጣ።የክፍያ መጠን 2000 ብር ነው።ስለዚህ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000171480683  Amhara medical Association ብላቹህ እያስገባቹህ ደረሰኝና ጉርድ ፎቶ ለአባላት ጉዳይ ዳይሬክቶሬት "ዶ/ር ጥላሁን ፀጋዬ" ቴሌግራም  መላክ ትችላላቹህ።መታወቂያ በቅርቡ ልናሰራ ነው።
ስልክ ቁጥር:0911929227
user name:@ttsegabit
አማራ ህክምና ማህበር ኩራታችን ሆኖ ለትውልድ እንዲቀጥል ሃላፊነታችንን እንወጣ
ከአማራ ህክምና ማህበር የተላለፈ ጥሪ
✍✍✍
የአማራ ህክምና ማህበር ከአማራ ሀኪሞች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች መጋቢት 6 /2018 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ውይይት ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል።ስለዚህ ማህበሩ ይመለከተኛል የምትሉና ለአማራ ህዝብ በጤናው ዘርፍ አሻራ ማሳረፍ የምትፈልጉ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያላቹህ አካላት ትቀላቀሉን ዘንድ የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
✍✍✍
ቅድሚያ ለጤና/Priority For Health
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህርዳር
ኢትዮጵያ
To join the meeting on Google Meet, click this link:
https://meet.google.com/noa-hcie-tsz

Or open Meet and enter this code: noa-hcie-tsz
Atalel Fentahun:
https://internationalforum.bmj.com/oslo/global-top-30-improvers-awards/

Please vote the young and intelligent researcherand Surgeon Dr Atale Fentahun
✍✍✍
ሁሉም ሰው ይምረጥ
Steps:
1. Click improvers Award
2. Click vote
4:Best cross-organization collaboration award
Click ETHIOSOS TEAM
Submit
✍✍✍
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህርዳር
ኢትዮጵያ
To Remember
ከአማራ ህክምና ማህበር የተላለፈ ጥሪ
✍✍✍
የአማራ ህክምና ማህበር ከአማራ ሀኪሞች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዛሬ እሁድ ማለትም መጋቢት 6 /2018 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ጀምሮ ውይይት ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል።ስለዚህ ማህበሩ ይመለከተኛል የምትሉና ለአማራ ህዝብ በጤናው ዘርፍ አሻራ ማሳረፍ የምትፈልጉ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም ያላቹህ አካላት ትቀላቀሉን ዘንድ የአክብሮት ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
✍✍✍
ቅድሚያ ለጤና/Priority For Health
የአማራ ህክምና ማህበር
ባህርዳር
ኢትዮጵያ
To join the meeting on Google Meet, click this link:
https://meet.google.com/noa-hcie-tsz

Or open Meet and enter this code: noa-hcie-tsz
👍1