Amhara Medical Association(AMA)
691 subscribers
211 photos
2 videos
19 files
145 links
Amhara medical Association is all about quality of medical care and physicians satisfaction in the nation.
Download Telegram
የሃዘን መግለጫ
በዶ/ር ሜሪ አበበ ድንገተኛ ህልፈት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል።

ዶ/ር ሜሪ የጎንደር ዩኒቨርስቲ  የ6ኛ አመት የህክምና ተማሪ(ኢንተርን ሀኪም) ስትሆን በትሁትነቷ የምትታወቅ ነበረች።ለመመረቅ 3 ወራት ሲቀራት ባልታወቀ ምክንያት ጥር 7, 2018 ዓ/ም አርፋለች።

ለቤተሰቦቿ እና ለጓደኞቿ  መፅናናትን ከልብ እንመኛለን።

ነፍሷን በአፀደ ገነት ያኑር።

የአማራ ህክምና ማህበር

ባ/ዳር, ኢትዮጵያ

Message of Condolence

We are deeply saddened by the untimely passing of Dr. Mery Abebe.
She was a humble intern(6th year) doctor  at University of Gondar.and about 3 months only remaining for Graduation!

Our heartfelt condolences go to her families, friends, and colleagues.
May she rest in peace

Amhara Medical Association
Bahir Dar,Ethiopia
ማቴዎስ 3፥16–17
ኢየሱስም በተጠመቀ ጊዜ ወዲያውኑ ከውኃው ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ወርዶ በእርሱ ላይ መጣ። እነሆም ከሰማይ ድምፅ፥ “ይህ የተወደደ ልጄ ነው፥ እኔ በእርሱ ደስ ብሎኛል” አለ።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች
እንኳን ለ2018 ዓ/ም የከተራ እንዲሁም የጥምቀት በዓል በሠላም በጤና አደረሳችሁ።


      አማራ ህክምና ማህበር
        ባህር ዳር
        ኢትዮጵያ

ጥር, 2018 ዓ/ም
👍3👎1
ጥምቀትን በባህርዳር የአማራ ህክምና ማህበር/Amhara medical association/ከአማራ ክልል ጤና ቢሮና ከባ/ዳር ከተማ ጤና መምሪያ ጋር በጋራ በመሆን የድንገተኛ ህክምና ቡድን አቋቁሞ በሁለቱም  ባህረ ጥምቀት አገልግሎት  እየሰጠ ይገኛል።በአለም ላይ ያላቹህ ክርስቲያኖች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ አመታዊ የጥምቀት በአል አደረሳቹህ። በአለም የቅርስ መዝገብነት ላይ የተመዘገበውን የጥምቀት በአል ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን ለማህበረሰቡ አገልግሎት በመስጠት የአማራ ህክምና ማህበር/Amhara Medical Association/በማሳለፉ እጅጉን ደስታ ይሰማዋል።በሁሉም  ቦታ በአሉ በሰላም እንዲጠናቀቅ ማህበሩ ምኞቱን ይገልፃል።ለወደፊትም በታላላቅ  የአደባባይ በዓላት ላይ ማህበሩ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመሆን በመስራት ለማህበረሰቡ የቅርብ ደራሽ ተቋም እንደሚሆን ፍፁም እምነት አለን።በየትኛውም ቦታ ያላቹህ የህክምና ባለሙያዎች የማህበሩ አባል በመሆን ማህበሩን የወደፊት የሀገር ተስፋ ማህበር እንዲሆን ታደርጉት  ዘንድ ጥሪውን ያስተላልፋል።ማህበሩ የእናንተው ውጤት ነው።ሁልጊዜም ማህበሩ ከእናንተው ጋር ነው።በድጋሜ እንኳን ለከተራና ለጥምቀት በአል አደረሳቹህ።

የአማራ ህክምና ማህበር/Amhara  Medical Association/
ባህርዳር
ኢትዮጵያ
👎2👍1
በሰላም ተጠናቋል
❤️❤️❤️
✍በባህርዳር በሁለቱም ባህረ ጥምቀት ሲካሄድ የነበረው የጥምቀት ስርአት በሰላም በመጠናቀቁ የአማራ ህክምና ማህበር/Amhara Medical Association /ደስታውን ይገልፃል።በሁለቱም ጥምቀተ ባህር የህክምና ቡድን ተቋቁሞ አገልግሎት በመሰጠቱና በስኬት በመጠናቀቁ እጅግ ደስ ብሎናል።ወደፊትም በተለያዩ ቦታዎች የሚካሄዱ የአደባባይ በአላት ላይ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ማህበሩ  በፅኑ ያምናል።የዘንድሮው አገልግሎት ትልቅ ትምህርት የወሰድንበት ነበር።ለወደፊቱ የተደራጀና ወጥ እንደሚሆን ባለሙሉ ተስፋ ነን።

✍ማህበሩ  የተቋቋመው 2008 ዓ.ም በአማራ የህክምና ባለሙያዎች የተቋቋመ ሲሆን አንጋፋ ሀኪሞች በፕሬዚዳንትነት መርተውታል።ዶ/ር ጋሹ ክንዱ፤፤ዶ/ር በቃሉ ውብሸት፤ዶ/ር መልካሙ አብጤ፤ዶ/ር አብራራው ታደሰ ማህበሩን  ይመሩ የነበሩና ማህበሩን ለዚህ ትውልድ ያስረከቡ አንጋፋ ሀኪሞች ናቸው።
✍ማህበሩ የበጎ አድራጎት ማህበር  ቋሚ የሆነ የበጀት ምንጭ የለውም/ ከአባላት ክፍያ በቀር/።ስለዚህ ውድ የህክምና ባለሙያዎች ማህበር እጅግ አስፈላጊ መሆኑን ተረድታቹህ ሁላቹህም አባል ትሆኑ ዘንድና ማህበሩን ታጠነክሩት ዘንድ ማህበሩ በክብር ይጠራቹሃል።ማህበሩ ላለፉት ጥቂት አመታት በተለያዩ ምክንያቶች ብዙም እንቅስቃሴ ሳያደርግ መቆየቱ ሁላችንም የምናውቀው እውነት ነው።ግን አሁን ወደ ሙሉ አቅሙ ለመመለስ እየታገለ ያለ ማህበር ነው።በዚህ ወቅት ከጎናችን ሆናቹህ ልታግዙን ይገባል።ባህር ውስጥ የገባችን ህፃን ለማውጣት ከውጭ ሆኖ መጮህ/ማልቀስ ምንም አይጠቅምም።ወደ ባህሩ ጠልቆ መግባት ያስፈልጋል።እናም ከውጭ ሆኖ መተቼት የትም አያደርስም።ስለዚህ ወደ ማህበሩ ግቡና ማህበሩን የወደፊት የሀገር ኩራት ማህበር አድርጉት።
መልካም የጥምቀት በአል ይሁንልን።
✍✍✍
የአማራ ህክምና ማህበር
/Amhara Medical Association
ባ/ዳር
ኢትዮጵያ
👎2
ለጤና ባለሙያዎች የተዘጋጀ/For All health professionals/
✍✍✍
የአማራ ህክምና ማህበር /AMA/ በ2008 ዓ.ም የተመሰረተ ማህበር ነው።ማህበሩ መስከረም 25/2018 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ማካሄዱ ይታወቃል።በዚች ጥቂት ወራት የቦርድ አመራርና ዳይሬክተሮች ሁልጊዜም በየሳምንቱ ስብሰባ እያደረጉ የሚከተሉትን ስራዎች አከናውኗል።
1.ማህበሩን ባዲስ መልኩ ለማደራጀት ተሞክሯል
2.የጤና ባለሙያውን ጥያቄ የሚመለከታቸው አካላትን እየጠየቀ ይገኛል።እልባት እስኪገኝ ድረስ እስከመጨረሻው መጠየቁንም ይቀጥላል።
3.ባ/ዳር በሚገኘው ሁለቱ ጥመቀተ ባህር ከጤና ቢሮ ጋር በመተባበር የህክምና ቡድን አቋቁሞ አገልግሎት ሰጥቷል።ወደፊትም ይሰጣል።
ከዚህ በመቀጠል ደግሞ ለጤና ባለሙያዎች ትልቅ እድል ከፍቷል።የማህበሩ አንዱ አላማ ተመራማሪና መዋቅራዊ እሳቤ /Researcher and Systemic Thinker/ ያላቸው የህክምና ባለሙያዎችን ማፍራት ነው።ይሄን ለማድረግ የማህበሩ ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ስለ ጥናትና ምርምር/Research training from Basic to advanced/አዘጋጅቷል።ማንኛውም ፍላጎት ያለው የጤና ባለሙያ መሳተፍ ይችላል።ቅድሚያ የተመዘገበ በቅድሚያ እድል ይሰጠዋል።በሚከተለው የመመዝገቢያ ቅፅ መመዝገብ ይቻላል።
https://forms.gle/UnewQLPjQZPpH1TU9
❤️❤️❤️
የአማራ ህክምና ማህበር
Amhara Medical Association
ባ/ዳር
አትዮጵያ
👍2
አስደሳች ዜና ለሁሉም ጤና ባለሙያዎች
        ከአማራ ህክምና ማህበር

የአማራ ህክምና ማህበር አዲስ ስራ አሰፈፃሚወች ፤ ዳይሬክተሮችና የዞን አመራሮች በአዲስ መልክ ከተመረጡ ጊዜ ጀምሮ  የተለያዩ ስራወችን እየሰራ ይገኛል።ማህበሩ ከተቋቋመባቸው አላማዎች ውስጥ አንዱ ከህክምናው በዘለለ በጥናትና ምርምር ማህበረሰባቸውን ማገልገል ለሚፈልጉ የጤና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት ነው። በመሆኑም በአማራ ህክምና ማህበር በጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት በኩል የተዘጋጀ የጥናት እና ምርምር ስልጠና የፊታችን አርብና ቅዳሜ(በ 29 & 30, 2018 ዓ/ም) ለሁሉም የጤና ባለሙያዎች ለመስጠት ዝግጅቱን ጨርሶ በጉጉት እየጠበቀ ይገኛል። ስልጠናው በመሠረታዊ የጥናትና ምርምር ክህሎቶች የሚያተኩር ሲሆን በኦንላይ እንደሚሰጥና ሰርቲፊኬትም እንደሚኖረው ገልፀዋል።በመሆኑም  መሣተፍ ለምትፈልጉ ማንኛውም የጤና ባለሙያዎች ከታች በምናስቀምጠው ሊንክ ገብታችሁ መመዝገብና በጥናትና ምርምር የካበተ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ስልጠናውን መውሰድ ትችላላችሁ።

👇👇👇

https://forms.gle/UnewQLPjQZPpH1TU9

     አማራ ህክምና ማህበር
     የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት
     ባህር ዳር
      ኢትዮጵያ
👍5👎1
የሀዘን መግለጫ///
በዶ/ር ጸጋሁን ስሜ በ26/05/2018 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ በድንገት ህይወታቸው በማለፉ ጥልቅ ሀዘን ተሰምቶናል!!!
ዶ/ር ጸጋሁን የህክምና ትምህርታቸውን በመቀሌ ዩኒቨርስቲ በ2011 ዓም ካጠናቀቁ በኋላ በጠቅላላ ሐኪምነት ህይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ የአማራ ጤና ቢሮ ባልደረባ በመሆን ህዝባቸውን በቀናነት ሲያገለግሉ የነበሩ ሀኪም ነበሩ።
እንዲሁም የአማራ ህክምና ማህበር አባል የነበሩ ሲሆን ትናንት 26/05/2018 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ በድንገት ህይወታቸው አልፏል።
በዶ/ር ጸጋሁን ስሜ ድንገተኛ ህልፈተ ህይዎት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን በድጋሚ እየገለጽን መንግስት የሀኪሙን አሟሟት ምክንያት በትክክል እንዲያጣራና ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ እንጠይቃለን።
ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና የስራ ባልደረቦቹ መጽናናትን እንመኛለን።
የአማራ ሕክምና ማህበር
ባህርዳር , ኢትዮጵያ///