Amhara Medical Association(AMA)
690 subscribers
211 photos
2 videos
19 files
145 links
Amhara medical Association is all about quality of medical care and physicians satisfaction in the nation.
Download Telegram
ማስታወሻ
የአማራ ህክምና ማህበር በየ ሆስፒታሎች ተወካይ እንዲኖረው ደብዳቤ መፃፉ ይታወሳል::
በርካታ ሆስፒታሎች ምላሽ እየሰጡን ቢሆንም አንዳንድ ቦታዎች ላይ መድረስ አልቻልንም ::ስለሆነም ደብዳቤው ሁሉንም የአማራ ሀኪም የሚመለከት ሲሆን ዓላማውም ጠንካራ የሀኪሞች ማህበር በመፍጠር የሀኪሙንና የተገልጋዩን መብት የሚያስከብርበት አቅም መፍጠር ነው::ስለሆነም እስከተጠቀሰበት ቀን ድረስ ተወካዮቻችሁን እንድታሳውቁን በድጋሚ እንጠይቃለን::በግል ሆስፒታሎችና በጤና ጣቢያ ለምትሰሩ ሀኪሞች በቅርብ ቀን አማራጭ የምናመጣ ይሆናል::
የአማራ ህክምና ማህበር
Alert on public health emergency
በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ኮሌራ መሠል ወረረሽኝ መከሰቱ ታውቋል::በዚሁ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ቁጥራቸው ለጊዜው በውል ያልታወቁ ሰዎች መሞታቸውንና በሺዎች ሚቆጠሩ ምልክቱን ያሳዩና ንክኪ ያላቸው ለይቶ ማቆያ ላይ መሆናቸው ተረጋግጧል::
በሌላ በኩል ንክኪ ያላቸው ሰዎች ከቦታው ወደ መሀል ሀገር እየመጡ ስለሆነ የበሽታውን ስርጭት አስከፊ እንዳይሆን የአማራ ህክምና ማህበር ስጋት አድሮበታል::
በመሆኑም ጤና ቢሮውና መንግስት በአስቸኳይ ርብርብ እንዲያደርግ እናሳስባለን::
1.በህመም ስቃይ ያሉ ታካሚዎችን ህይዎት ለማትረፍ በቂ የባለሙያና የግብዓት አቅርቦት በአስቸኳይ ወደ አካባቢው እንዲላክ እናሳስባለን::የህክምና ባለሙያዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሙሉ መከላከያ እቃዎች(PPE) እንዲሟላላቸው በጥብቅ እናሳስባለን::
2.የአካባቢው አስተዳደር የሰዎችን እንቅስቃሴ ላይ ገደቡን አጠናክሮ እንዲቀጥል ና ህብረተሰቡም ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን::ታካሚዎችና የአካባቢው ነዋሪች ሙሉ ህክምና በአቅራቢያቸው ስለሚያገኙ ወደ ጎንደር ከተማና ሌሎች አካባቢዎች የሚደረጉ ጉዞዎችን እንዲቀንሱና የህብረተሰቡን ጤና እንዲጠብቁ እንጠቁማለን::
3.ጎንደር ዩኒቨርስቲን ጨምሮ አቅራቢያ ያሉ ጤና መምሪያዎችም የህብረተሰብ ጤና አደጋ (public health emergency) መከሰቱ ታውቆ ጥንቃቄና ዝግጅት እንዲያደርጉ እያሳሰብን ማህበራችንም ለየትኛውም ግዳጅ ዝግጁ መሆኑን እንገልፃለን::
👍1
የውይይት ጥሪ
የአማራ ህክምና ማህበር ራሱን ለማጠናከርና የተቋቋመለትን ዓላማ ለማስፈፀም በሁሉም የክልሉ ሆስፒታሎች ተወካይ እያስመረጠ መቆየቱ ይታወቃል::
በዚህም ሁሉም ሀኪሞች ላደርጋችሁት ደማቅ ተሳትፎ እያመሰግን ለቀጣይ ስራዎች የጋራ አቋም ለመያዝ ለሁሉም የሆስፒታል ተወካዮች የውይይትና የስልጠና መድረክ አዘጋጅተናል::
1 .ለምዕራብ አማራ አካባቢ ሆስፒታሎች ማለትም ለሁሉም የጎንደር ዞኖች ወልቃይትን ጨምሮና ለሁሉም የጎጃም ዞኖች ቅዳሜ ሀምሌ 15/2015 ዓም በባህርዳር ሆምላንድ ሆቴል የሙሉ ቀን ስልጠና ውይይት ይኖረናል::
2.ለምስራቅ አማራ ማለትም ለሸዋ,ወሎና ዋግ ህምራ ደሴ ላይ ተመሳሳይ ዝግጅት ይኖረናል::ቀንና ቦታውን ከባህርዳሩ ውይይት በኃላ በቅርብ የምናሳውቅ ይሆናል::
በመጨረሻም በምዕራብ አማራ አካባቢ ያላችሁ ሁሉም ተወካዮች ለቅዳሜ ውይይት ነገ ባህርዳር ገብታችሁ እንድታድሩ እያሳሰብን ለዝርዝር ሁኔታ የማህበሩ ስራ አስፈፃሚዎችን ማነጋገር ትችላላችሁ::
ዛሬ የአማራ ህክምና ማህበር ከምዕራብ አማራ ሆስፒታል የማህበሩ ተወካዮች ጋር የተሳካ ወይይት አካሄደ::
ውይይቱ የአጥንት ህክምና ሰብ ስፔሻሊስትና የማህበሩ የቀድሞው ፕ/ት ዶር በቃሉ ባቀረቡት career development and leadership እና ወጣቱ ምሁር ዶር የሻንበል አግማስ leadership and health system ላይ ባቀረቡት በሳል ፅሁፍ የተጀመረ ሲሆን ማሳረጊውን በቅርንጫፎች ምርጫ ያደረገ ነበር::
በውይይቱ ማህበሩ ክንፉን አድሶ ለባለሙያውና ለህብረተሰቡ የሚያደርጋቸውን አበርክቶዎች የሚያጠናክርበት መንገድ ላይ አድምቶ ተወያይቷል::የህዝባችን የጤና አገልግሎት መሻሻል እንደሚገባውና የአማራን ህዝብ የሚመጥንና ዘመኑ ከደረሰበት የህክምና ቴክኖሎጅ ተጠቃሚ መሆን እንደሚገባው በአፅንኦት ተነስቷል::በተያያዘም የጤና ስርዓቱ የጀርባ አጥንት የሆነው የህክምና ባለሙያው ጤናውና የጤና ወጪው እንዲጠበቅለት,በሀገሩ ቤት ኖሮት ከስደት የሚቀርበት መንገድ መምጣት እንዳለበት ተነስቷል ::ሀኪሙ የላቡን መከፈል ቀርቶ ለመኖር እየተቸገረ እንደሆነና ለዚህም ትግል እንደሚያስፈልገው ስምምነት ላይ ደርሰናል::
በመሆኑም ሀኪሙ የአማራ ህክምና ማህበርን ማጠናከር እንደሚገባውና የማህበሩ መሪዎችም የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ እንዲሁም ከሌሎች የጤና ማህበራት ጋር በቅንጅት እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል::
በመጨረሻም በምዕራብ አማራ ስር 4 የማህበሩ ቅርንጫፎች ተቋቁመውና መሪዎችም ተመርጠው በድምቀት ተጠናቋል::
ምስራቅ አማራ ላይ መሠል ውይይት ኮምቦልቻ ላይ በ2 ሳምንት ውስጥ የምናካሂድ ይሆናል::
የአማራ ህክምና ማህበር
👍2
መረጃ ስለ አማራ ህክምና ማህበር
የአማራ ህክምና ማህበር የተመሠረተበትን ዓላማ ለመፈፀም የመዋቅርና የተግባር ማሻሻያዎች እያደረገ ይገኛል::በዚህም በዚህ ሳምንት የማህበሩን ቢሮ ባህርዳር ሀይፐርሲኒማ ህንፃ ውስጥ መክፈታችንን ስንገልፅ በደስታ ነው::ስለሆነም ጉዳይ ያላችሁ አባልና ደጋፊዎቻችን ቢሯችን ክፍት መሆኑን እየገለፅን የፀሀፊና መሰል ወጪዎችን ለመሸፈን ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን::
በተያያዘም የ CPD ፍቃድ ለማውጣት ጥረት እየተደረገ ሲሆን የማህበሩን ህግና ደንብ የሚያከብሩ ስፔሻሊስት ሀኪሞች ከፍ ያለ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ማሳወቅ እንወዳለን::
በሌላ በኩል የቅርንጫፍ ሀላፊዎች መዋቅራችሁን እንዲጠናከርና አባል ሀኪሞችም ከፍ ያለ ተሳትፎ እንድታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን::
👍9
ከአማራ ህክምና ማህበር የተሰጠ ማሳሰቢያ
መንግስት እያካሄደ ባለው ጦርነት በርካታ ንፁሀን እየተገደሉና እየቆሰሉ መሆኑን ከክልሉ የተለያዩ ሆስፒታሎች ሪፖርት እየደረሰን ነው::በተለይም ደ/ታቦር ሆ/ል ትናንት ማምሻውን 1የባጃጅ ሾፌርን ሞትን ጨምሮ ከ40 በላይ ንፁሀን ከባድና ቀላል አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን ጎንደር ዩኒቨርስቲ ሆ/ል 1 ሞት,5 ከባድ ቁስለኛ እና በርካታ ንፁሀን ቀላል ጉዳት አስተናግደው ህክምና አግኝተዋል:: ቡሬና አማኑኤል ሆስፒታልም መሠል ጥቃቶች መድረሳቸውን ከህክምና ባለሙያዎች መረጃ ደርሶናል::በመንገድ ምክንያት ወደ ሆስፓታል ያልመጡ ብዙ የተሰዉና የተጎዱ ሰዎች እንዳሉም ግልፅ ነው:: የአማራ ህክምና ማህበርን ጉዳዩ ክፉኛ አሳስቦታል::መንግስት ንፁሀንን መጨፍጨፍ የጦር ወንጀለኝነት መሆኑን ተረድቶ ለንፁህ ሰዎች ከለላ እንዲያደርግ በጥብቅ እናሳስባለን::
በተያያዘ ንፁሀንን ለማከም የሚያስፈልጉ ፈሳሽ(NS) እና ስቲች ማተሪያል ጉድለት ያጋጠማቸው ሆስፒታሎች ስላሉ የሚመለከተው አካል ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን::
አማራ ህክምና ማህበር
👍7
ለሚመለከተው ሁሉ
አሁን ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት በአማራ ክልል የመንገድ መዘጋት ፣የህክምና ግብዓት፣ የኦክስጅን እና ደም እጥረት እየተከሰተ ነው።
በዚህም ምክንያት በጦርነት ምክንያት ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉ ወገኖች ፣ እናቶች እና ህፃናት ጭምር መሰረታዊ የህክምና አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም ።
ስለዚህ የሚመለከታቸው አካላት ፣ አለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ተቋማት ህክምና በማንኛውም ሁኔታ ሊከለከል የማይገባው መሰረታዊ የሰው ልጆች መብት መሆኑ ታውቆ ሁሉም አካላት የህክምና አገልግሎት ተደራሽ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪ እናቀርባለን ።
ለሁሉም የህክምና እና ጤና ባለሙያዎች በሙሉ እስከአሁን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆናችሁ ለምትሰጡት አገልግሎት እያመሰገንን አሁንም በየአካባቢያቸሁ ከተቋቋሙት የድንገተኛ የህክምና ቡድኖች ጋር በመሆን ሙያዊ ግዴታችሁን መወጣታችሁን እንድትቀጥሉ ከአደራ ጋር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።
#urgent Humanitarian support in Amhara Region
# Acess to essential health service
#Protect civilians
#peace for all

የአማራ ህክምና ማህበር
👍3
Dear All Members of AMA

You are kindly requested to inform all Medical doctors in the Amhara region.
As you all know, there is no Internet access in the region, please inform your friends with short texts, and calls.
Thank you for all your kind support🙏
👍1