African Digital & Innovation Technology Academy-ADITA
77 subscribers
9 photos
17 videos
10 links
Empowering Africa's digital future through cutting-edge AI education , training, and innovation.
Download Telegram
Channel name was changed to «African Digital & Innovation Technology Academy-ADITA»
አሁን ላይ አብዛኛው ሰው ዘመኑ የኤ.አይ ወይም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ነው ሲል እንሰማለን ነገር ግን ኤ.አይን እንደ ዘመኑ ተቀዳሚ ቴክኖሎጂ በምን መልኩ ተጠቅመን ስራችንንና ኑሮአችንን ማቅለል እንደሚቻል የሚያውቁት ጥቂቶች ብቻ ናችው።

ስለ ዲጂታሉ ዓለም እና ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ በቂ እውቀት እንዲኖሮዎትና ኤ.አይን በምን መልኩ ልጠቀመው የሚለውን ጥያቄዎትን ለመመለስ አፍሪካን ዲጂታል ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ አካዳሚ በዘርፉ በቂ እውቀትና ልምድ ያላቸውን አሰልጣኞችን አዘጋጅቶ እየጠበቃችሁ ነው።

በተጨማሪም አካዳሚያችን ከኢትዮጵያ ውጪ በኬንያና በኡጋንዳ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ስልጠናዎችን ለመስጠት ሙሉ ዝግጅቱን ጨርሷል።

ይህ ኮርስ ስለ ኤ.አይ ማወቅ እፈልጋለሁ ለሚል ለማነኛውም ሰው የሚሰጥ ሲሆን በተለያየ የሙያ ዘርፍ የተሰማራችሁ ባለሙያዎች፤ነጋዴዎች፤መምህራን እንዲሁም ተማሪዎች መማር ትችላላችሁ።

ኮርሱን ጎሮ በሚገኘው አይቲ ፓርክ ወይም ላምበረት በሚገኘው የፌደራል ቴክኒክ እና ሞያ ኮሌጅ እንዲሁም በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በአካል በመምጣት መከታተል የምትችሉ ሲሆን በአካል መምጣት ለማትችሉ ከየትኛውም ሃገር ሆናችሁ ኮርሶቻችንን በኦንላየን (በይነመረብ) መከታተል እንደምትችሉ ለማሳውቅ እንወዳለን።
3