ABRET PRO
4.41K subscribers
1.77K photos
63 videos
43 files
525 links
የአብሬት እንዲሁም የቃዲሪይ ሲልሲላ መንዙማዎችን ፣ ከአካቢሮች የሰማናቸውን ቀሰሶች ፣ እንዲሁም ከመሻኢኾቻችን ኪታቦች አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮችን የምንማማርበት አጠቃላይ የሀድራ ስራዎችን የምንዘክርበት ቻናል ነው
@Abretpro
Download Telegram
🔰💢 ሰለሏ አላ ሙሀመድ ሳሂቡል ኢስራ ወል ሚእራጅ💢🔰
🔰💢ሰለሏ አላ ሙሀመድ ማእዲኑ ኑሪ ወሲራጅ 💢🔰

❇️ @abretpro
❇️🔰 ኸሚስ🔰💚

#አብሬት_መንዙማ
#ዛኪር_አብዱልራህማን

صلى الله على محمد باب المنن والكرم
صلى الله على محمد مفتاح كنوز النعم (العلم)


ሰለሏ አላ ሙሀመድ ባቡል ሚነኒ ወልከረም:
ሰለሏ አላ ሙሀመድ ሚፍታሁ ኩኑዚ ኒعም / عለም /

♻️Share & join
♦️👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾

❇️ @abretpro

https://youtu.be/uwsGC_8a7sA
🔰💢መገርገበያ💢🔰

አብሬት መንዙማ
በሸህ መኪ

አሏሁመ ሰሌ አላ ሙሀመዴ (2)
በርቁ ፈይዱል አይኔ ኒዛሚል ውጁዲ

اللهم صل على محمّد ٢
برق فيض العين نظام الوجود

@abretpro

https://youtu.be/3-Fj0BTL0Aw
😢1
የኢልም ባህር ስለሆኑት ሸይኽ ሰይድ ሚቅባሰል ኑር የቂራት ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ ለኸሚስ ስጦታ

@abretpro
♦️👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
የኢልም ባህር ስለሆኑት ሸይኽ ሰይድ ሚቅባሰል ኑር የቂራት ታሪክ ከብዙ በጥቂቱ @abretpro

🔰 #አህመድ_ጉርባ ከአብሬትይ (አበል ራሙዝ) ቁጥር አንድ ተጠሪ ከሆኑ ሙሪዶቻቸው አንዱ ናቸው:: አንዴ "#የአብሬት_ሸህ #ሰይድ_ባኡ_ሳሊስ አስጠሩኝ ተጣድፌ ወዳሉበት አቀናሁ። ያሉበት እንደደረስኩ አንድ ቆጮ የማይበላ ልጅ ሊወለድላቸው እንደሆነ እና እኔ ጤፍ መዝራት እንድጀምር አዘዙኝ ትእዛዛቸውን ተቀብይ ያሉትን ፈፀምኩ። ጤፉን አጨድኩና ወደ ጎተራ አስገብቼ ወደ አብሬት ወረድኩ። ለአብሬት ሸይኽ ያሉኝን አድርጊያለሁ ልጁ የታለ ብዬ አልኳቸው። እርሳቸውም 'አህመድ እኔ ዋሽቼህ አውቃለሁን?' ብለው ጠየቁኝ እኔም 'በፍፁም!' አልኳቸው። 'ያልኩህ ልጅ እናቱ ልትገባ 3 አመት ይቀራታል..' አሉኝ። ብለው አህመድ ጉርባ ተናግረዋል::

🔰 ሱብሀነሏህ! ጉድ አትሉም? ጤፍ እንዲዘራ የነገሩት ወቅት ይወለዳል ብለው ያሉዋቸው ልጃቸው እናት እንኳን ገና አልገቡም ነበር በዛን ወቅት #እመት_ዘህራ #ጅማ ነበሩ ፣ እመት ዘህራ እጅግ አሏህን ፈሪ ሙእሚን እና በጣም የቀሩ አሊም ነበሩ ፣ #አብሬትይ ይህንን በተናገሩ በሶስተኛው አመት እሜት ዘሀራን አገቧቸው ፣ እመት ዘህራም ወደ አብሬት መጡ። አብሬትይ የተናገሩላቸው ልጅም በ1933 ጣሊያን ሲወጣ ተወለዱ ፣ እሳቸውም #ሰይድ_ሚቅባሰል_ኑር ናቸው::

🔰 5አመት ሲሆናቸው ቁርአንን በ #ዛኪር_አብዱልራህማን አንድ አመት ከስድስት ወር ፈጅቶባቸው ጨረሱ። አባታቸው ኪታብ እንዲጀምሩ ወደ አንድ ሸህ እልካለሁ ብለው ሲሉ ከእናቶቻቸው ቤተሰቦች እነ ኢማም አቂል ሌሎችም 'ገና የ6 አመት ከግማሽ ልጅ ነው። የሰው አፍ ወስጥ ይገባል አይሆንም። ' የሚል ቅሬታ አሰሙ #ኢማም_አቂል ቁርአን ደግሞ ቢቃራ ይሻላል ብለው ሲሉ አባባ ሰይዲን አስጠርተው ቁርአን ከፍተው ሰጡዋቸውን ቅራ ብለው አሏቸው እሳቸውም አሳምረው ቀሩ ከዚ የተሻለ የሚቀራ ደረሳ የት አለ? በማለት ኢማም አቂልን ጠየቋቸው ኢማም አቂልም በደምብ አይቀራም ብዬስ አይደለም በዚህ ቁመቱ በዚህ እድሜው ከደረሶች ተቀላቅሎ ኪታብ ቢጀምር የሰው አይን ምን ያደርግብኝ ይሆን ብዬ ሰግቼ ነው ብለው አሉ ያኔ አባባ እንደዛ ነው እንዴ በቃ ትንሽ ከፍ እስኪል እኔ አቀራዋለው ብለው አሉ ፣ ሹጃእ እና ባፈድል የተሰኙትን ኪታቦችን በአባታቸው በሰይድ ባኡ ሳሊስ ጨርሰው ሚንሀጅን ግማሽ ያህል ከቀሩ በሁዋላ ወደ ስልጥ ወሰዷቸው በዳምር ሸህ ቂራታቸውን ቀጠሉ። ከዛ ያለ ማቆም ጉራጌ እና ስልጤ ውስጥ ከአንድ ቦታ ሌላ ቦታ እየተጏጏዙ በወቅቱ በነበሩ ታላላቅ ሸሆች ቂራታቸውን ቀጠሉ::
🔰ለአብዮት ያህል *በስልጥ #ኧዳምር_ሼህ ፦ ኡምዳ ፣ ሚንሀጅ እና ፊቂህ
* በ #ሸህ_ሁሴን_ዳሎቻ፦ ሚንሀጅ ፣ ነህው እና ሙልሀ ወ.ዘ.ተ ፣ አክሊል በ #ዋቻ_ሸህ #ሙሀመድ_ኸጣጥ ፦ከሽፈል ኒማብ ፣ ፈዋኪር ፣ ኢብኑ አቂል ፣ ሙጂብ እና ሱሩዳ ወ.ዘ.ተ ፣ በመቀጠል ወደ #መገር_ሸህ ፤ ቸሀ #አዶሼ_ሼህ በመቀጠል በ #ጮካ_ሸህ ጋር በያን፦ ኢስቲሀራ ፣ በመረር #የዋራ_ሸህ በያን፦ የቁርአን ተፍሲር እና የሀዲስ ኪታቦችን ተዟዙረው ከቀሯቸው ኪታቦች የሚጠቀሱት እናም ጥቂቶቹ ናቸው።

@abretpro

🔰ከዛሬ 25 አመታት በፊት የመደሁት መድህ በአሽር ጌታ ሸህ ጀመል የተከተበ መንዙማቸውን እስከነ ኪታቡ በራሳቸው ድምፅ ተጋበዙልን

♦️👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
1👍1
#ኢናሊላህ_ወኢና_ኢለይሂ_ራጅዑን

የገታ ሐሪማ ኸሊፋ የሆኑት ሸይኽ ሙሒዲን ገታ አልፈዋል
አላህዬ ይዘንላቸው ያሉትን አላህ ያቆይልን የአሊም ሞት የአለም ሞት ነው ጀነተል ፊርደውስ ይወፍቃቸው
👍1
🔰🔆መገርገበያ🔆🔰

♦️አብሬት መንዙማ ከነ #ፅሁፉ
♦️በዛኪር አብዱልራህማን

💢አሏሁመ ሰሌ አላ ሙሀመዴ
አሚኒ ወህዪከ ኢለል ኸልቂ ጡራ

💢اللهم صل على محمد
امين وحيك الى الخلق طرا

https://youtu.be/wlUiGcfBMa4
ኢላሂ አኼራ የሄዱትን በደረጃ ላይ ደረጃ ጨምርላቸው ፣ በሀያት ያሉትን ሙባረክ የሆነ ረጅም ሀያት ሰጥተህ አቆይልን ፣ ባዶ አታድርገን
🔰ሸህሩ ረመዷን ተቃርቧልና ለማስታወሻ ያክል የአብሬት ሸይኽ ረመዳንን ምን ያህል በኢባዳ ያሳልፉ እንደነበር ከብዙ በጥቂቱ

👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
🔰ሸህሩ ረመዷን ተቃርቧልና ለማስታወሻ ያክል የአብሬት ሸይኽ ረመዳንን ምን ያህል በኢባዳ ያሳልፉ እንደነበር ከብዙ በጥቂቱ

♦️የአብሬት ሸይኽ በረመዳን ለምንም አይነት ጉዳይ ከኢባዳቸው ከዚክራቸው ከሀድራቸው አይወጡም ነበር ለሰላት ሲቀር።
♦️በረመዳን ከኢባዳ የሚያሻግላቸው ሰው የራሳቸው ልጆችም ቢሆኑ አጠገባቸው እንዲመጣ አይፈልጉም ነበር ፣ በአንድ ወቅት ከሰይዲ እንድሰማሁት በረመዳን እኛ ልጆቻቸው እንኳን አጠገባቸው ስንመጣ ከኢባዳ ያዘናጉኛል በማለት ቶሎ ከአጠገባቸው እስክንሄድ ይጨንቃቸው ነበር ፣ በየቀኑ 24,000 ተህሊል ሌሎችም ቁጥር ስፍር የሌላቸው አዝካሮችን ፣ ቲላዋተል ቁርአን በጥቅሉ ምንም የሚቀራቸው ኢባዳ አልነበረም ፣ ሙሉ ረመዳንን እና ሸዋል 10 ቀናት የሲልሲላ ዱኣ እስኪያልቅ ድረስ በተለያዩ ኢባዳ እና አዝካር በተወጁህ ሀላዋቸው ውስጥ ነበር የሚያሳልፉት። ከኢባዳ ውጪ ትርፍ የሆኑ ቃላቶችን መናገር እንዲሁም ትንሽ እንኳን ፈገግ ማለት ለእርሳቸው ፆም የማጥፋት ያክል ነበር የሚሆንባቸው።
♦️አንድ ግዜ በረመዳን አንዲት ሴት ልጃቸው ወደ አኼራ ሄዱ ፣ ከዛ ከረመዳን ኢባዳቸው አቋርጠው ስለልጃቸው ሞት ሊነገሩዋቸው ሰዎች ፈሩ ፣ ትልልቅ የተባሉ ሰዎች ተመራርጠው እንዲያረዷቸው ይላካሉ ፣ የተላኩ ሰዎችም ሄደው ልጃቸው መታመማቸውን ሲነግሯቸው ስላመማቸው ብቻ እንዳልመጡ ይገባቸውና "ሞተች ወይ? " ብለው ጠየቁ ፣ ሰዎችም አዎን አሏቸው ፣ ታላላቅ ልጆቻቸውን ሰይድ አንሳር እና ሰይድ ሚቅባስን ጥሩልኝ አሉ ፣ ተጠርተው መጡ ለልጆቻቸው ምንም ነገር ቢመጣ የረመዳን ኢባዳቸውን ትተው እንደማይወጡ ነግረዋቸው ሄዳቹ እንግዳ ሸኙ ብለው ላኩዋቸውና እሳቸውም ወደ ኢባዳቸው ተመለሱ ፣ ሙሉ ረመዳን, ሸዋል 6 ቀን ፆመው የሲልሲላ ዱኣ ከተደረገ በሁዋላ በጠቅላላ ሙሉ ረመዳን እና ሸዋል 10 ቀናትን ሀድራቸው ውስጥ አሳልፈው ነበር የልጃቸውን ቀብር ለማየት የሄዱት።
ልብ በሉ አውሊያዎች ከማንም በላይ ዙሪያቸውን ይወዳሉ በረመዳን ከምን ግዜውም በላይ ሁሉንም ነገር ትተው ፊታቸውን ወደ ጌታቸው ስለሚያዙሩ ነው እንጂ የልጃቸው ሞት ስላላሳዘናቸው አይደለም

አሏህ እሳቸው ያስያዙንን መንገድ ምንከተል ያድርገን
አሚን አሚን አሚን

♻️Share & join
♦️@abretpro
🤩1
🔰የሸህ ሰይድ ሚቅባሰል ኑር መንዙማዎች
👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
የሸህ ሰይድ ሚቅባሰል ኑር መንዙማዎች

🔰የመጀመሪያ መንዙማቸው
'አሰላም አሌይኩም አሰላም አሌይኩም
ያሙናዬ ጠውዱል አውሊያዬ'
የተሰኘ አባታቸውን (አበል ራሙዝ) የመደሁመት የግጥም መድብል እንደሆነ የቀድሞ የፉል ውሃ መስኪድ አሰጋጅ እና መስራች ሸህ አስራር አስተላልፈዋል።
የመጀመሪያ መንዙማቸውን ገና በአፍላ እድሜያቸው እንደፃፉም ጭምር።
የጠፉ እንዲሁም በየሀድራው የተበታተኑ፣ መንዙማዎቻቸው ቀላል የማይባሉ ቢሆኑም አሁን ከተበታተኑት እና በደርግ በጓጉር እና ሰፈር በሚገኙት ሀድራቸው ከተቃጠሉት ባሻገር አሁን 3 የመንዙማ ኪታቦች ሲገኙ እነዚህም የተወሱል ነብዩ ሙሀመድን ሰ.ወ.ወ የሚያወድሱ እንዲሁም አባታቸውን የሚመድሁ ይገኙበታል።
🔰አሁን በመረጃ ማጠር ምክንያት ይሄን ይሄንን ማለት ባልችልም የተለያዩ የዱአ ኪታቦች እንዲሁም በቅርብ ወደ አብሬት ሙሪዶች እጅ የሚገባውን የአባታቸውን የሸህ ሰይድ ባኡ ሳሊስ የህይወት ታሪክ የሚያብራራው መናቂባቸው ይገኙበታል።
🔰ስለ መንዙማዎቻቸው ተነስቶ የማይዘለሉት የቡሩዳ መኸመስ ታሪክን ካቲብ ጀማል እንዲህ ሲሉ ከትበው አስቀምጠውታል።
'የዋቻ ሸህ ሙሀመድ ኸጣጥ ጋር እየቀሩ በነበሩበት አንድ ወክት ሸህ ሙሀመድ ኸጣጥ 'የሀበሻ መሻይሆች በምንም የሚታሙ አይደሉም። መንዙማዎቻቸውም አጂቦች ናቸው። ነገር ግን አንዳቸውም የቃፍያ (የግጥም መስፈርት እና ስርአት ) የሚያሟላ መንዙማ አልፃፉም።' ሲሉ ሰይድ ሚቅባስ 'የአባ ሾንኬንስ አይታቹታል ወይ የነሱ በቃፍያ የሚገባ መንዙማ የላቸውምን?' በለው ሲጠይቋቸው 'አው የነሱንም አይቻቸዋለሁ። አንዳቸውም አይገቡም።'ብለው መለሱላቸው። ይህም ግዜ ሰይዲ የሀበሻ መሻኢኾች ዋሪዳው እንደወረደላቸው ስለሚፅፉት እንጂ የግጥም ህግጋቱን ጠብቀው መፃፍ ስላቃታቸው አይደለም በማለት '15ቀን ስጡኝ' ብለው ወጡ። በ15 ቀኑ የቡሩዳ ሙኸመስ እና የሀምዝያ ሙቃበላን በመክተብ ወስደው አሳዩዋቸው። እሳቸውም 'አንተ የሆነ ነገር እንደምታመጣ አውቅ ነበር። ይህ የከተብከው መንዙማ የቃፍያ የግጥም ህጎችን የሚያሞላ ነው።' አሉ ሸህ ሙሀመድ ኸጣጥ..." ብለው ከሃበሻ የመጀመሪያውን የቃፍያ የግጥም ህጎችን የጠበቀ እንዲሁም በቃፍያ ህጎች መመዘን የሚችለውን መንዙማ መክተባቸውን አስቀምጠዋል። የተወሰኑ ገልፆቹን ከታች አስቀምጣለው

🔰ዛኪር አብዱልራህማን :-
"አንዴ ከአብሬት ሸህ ሰይድ ባኡ ሳሊስ ጋር የሰይድ ሸህ ቡሽራ (ሰይድ ባኡ ሳኑ) ደረሳ በነበሩት ሸህ አደም ሀድራ በተቀምጥንበት። የአብሬት ሸሆች የአባቴ ሸህ ቡሽራ (የቁባ አባ) መንዙማ በሸህ አደም ኪታብ ውስጥ አለ ብለው በመፈለግ
#ያረቢ_ሰሊ_አላ_ሙሀመድ
#ወከዛ_ሰላም_ማአቢ_አህመድ የሚለው የአባታቸውን መንዙማ አገኙት።
ዜማ ጠፍቶ ስንፈልግ ሸህ ሚቅባስ አሁን የሚባልበት ዜማ ደርሰው በዚህ ሞክሩት አሉ። ስንሞክረው ከግጥሙ ጋር ፍፁም ተስማማ።
የአብሬት ሸሆችም ይህን ሲያዩ 'ልክ ነህ ሚቅባስ አባቴም በዚሁ ዜማ ብለውት ይሆናል።' ብለው አሉ።

@abretpro
👍1
የሻእባን ወር የተለያዩ ክስተቶች የተከናወኑበት የሚከናወኑበትም ወር በመሆኑ የተላቀ ወር ነው። የሻእባንን ወር ልዩ ከሚያደርጉት መካከል የሚከተሉት ለአብነት ይጠቀሳሉ፡-
1. ወርሀ ሻእባን የሶላት ቂብላ ከበይተል መቅዲስ ወደ ካእባ የተዛወረበት ነው።
2. ከማንኛውም ወር በበለጠ የባሮች ስራ ወደ አላህ የሚቀርብበት ወር ነው። ኡሳማ ኢብኑ ዘይድ(ረዲየሏሁ አንሁማ) የአላህን መልእክተኛ(ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለው ጠየቋቸው "አንቱ የአላህን መልእክተኛ(ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ከወራቶች መካከል እንደ ሻእባን ወር በጣም የምትጾሙት ወር አይቸ አላውቅም ለምንድነው?"
የአላህን መልእክተኛ(ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) መለሱ፡- "ይህ ወር በረጀብና በረመዷን መካከል ያለ ሲሆን ሰዎች የሚዘናጉበት ወር ነው፡ በዚህ ወር የባሮች ስራ ወደ አለማቱ ጌታ ይቀረባል፡ የኔም ስራ ጾመኛ ሁኘ ወደ አላህ እንዲቀረብ እዎዳለሁ"። (ነሳኢይ ዘግበውታል)
3. የቀን ስራ በቀን፡ የለሊት ስራ ደግሞ በለሊት በየ እለቱ ወደ አላህ የሚቀረቡበት ወር ነው።
4. የሰማይ በር ተከፍቶ የባሮች ስራ በፍጥነት ወደ ላይ የሚወጡበት ወር ነው።
5. ከየ እለቱ በተጨማሪ በየሳምንቱ የባሮች ስራ ወደ ላይ የሚወጣበት ወር ነው።
ኒስፈ ሻእባን
""''''''''''"""""""
በዚህ በሸእባን ወር በጣም የተላቀችና የተከበረች ለሊት ትገኛለች። እሷም የሻእባን አጋማሽ(ኒስፈ ሻእባን) ለሊት ነች። በዚህች ለሊት አላህ ባሮቹን ሙሉ በሆነ እዝነቱና ረህመቱ ይሸፍናቸዋል። ይቅርታን ለጠየቀ ይቅር ይለዋል፡ ለጠየቀም ይሰጠዋል፡ የተቸገረን ከችግሩ ያላቀዋል፡ ለባሮቹ ስራቸውንና ሲሳያቸውን ይጽፍላቸዋል።
የሻእባን አጋማሽ ለሊትን አስመልክቶ ብዙ የሀዲስ ዘገባዎች ሰፍረው ይገኛሉ፡ ከነዚህ ዘገባዎች ውስጥ ሶሂህ፡ ሀሰንና ዶኢፍ የሆነ አለ። በኡለሞች የሀዲስ ሚዛን ሶሂህ እና ሀሰን ከተባሉት የተወሰኑትን ብቻ ልጥቀስ።
የአላህን መልእክተኛ(ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) የሚከተለውን ብለዋል፡-
1. "አላህ በሻእባን አጋማሽ ለሊት ለባሮቹ ረህመቱን ይገልጣል፡ ሙሽሪክና ሙናፊቅ የሆኑት ሲቀሩ ለሁሉም ምህረት ይደረጋል" (ጦበራኒይና ኢብኑ ሂባን)
2. "ጂብሪል(አለይሂ ሰላም) መጣና 'ይህች የሻእባን አጋማሽ ለሊት ናት፡ በአላህ ይሁንብኝ በዚህች ለሊት በከሊብ ጎሳ በጎ ጸጉር ቁጥር ልክ ከእሳት የሚድኑ ሰዎች አሉ፡ አላህ ወደ ሙሽሪኮች፡ ሙናፊቆች፡ ዝምድና ቆራጭ ወደሆኑት፡ ልብሳቸውን ጎታች ወደሆኑት(ልብሳቸውን ማያሳጥሩ ወንዶች)፡ ወላጆቹን ወደሚበድል፡ አስካሪ መጠጥ ወደሚጠምቅ. . . . አይመለከትም" (በይሀቂይ)
3."የሻእባን አጋማሽ ለሊት ሲሆን ተጣሪ ይጣራል 'ማርታ የሚፈልግ ምህረት የማደርግለት፡ የሚጠይቀኝ የምሰጠው' ይላል። በዚህች ለሊት አንድ ባሪያ ጠይቆ የሚከለከለው ነገር የለም በብልቷ ዝሙትን የፈጸመች እና ሙሽሪክ የሆነ ሲቀር" (በይሀቂይ)
አላህ በዚህ ወር፡ በዚች የተከበረች ለሊት ከሚምራቸው ባሮቹ ያድርገን። ረመዷንንም በሰላም ያድርሰን።
ምንጭ፡- 'ማዛ ፊ ሻእባን' ከተሰኘው ከሀረመይኑ(ከሁለቱ ሀረሞች) ሙሀዲስ ሙሀመድ ቢን አለዊይ(ረሂመሁሏህ) ኪታብ የተቀነጫጨበ።
👍
🔰እንደሚታወቀው #አልከስይ አወሉ የቁባ አባ የሩህ ወዳጅ ነበሩ #የቁባ_አባም በጣም ይወዷቸው ነበር ፣ በአንድ ወቅት የሆነ ቀን አብሬት ሀድራ የሂድማ ቡና ጠፋ ማንም አፍልቶ ይዞ የመጣ ሰው አልነበረም ፣ ሰው ስለቡና ካወራ ከተወሰነ ግዜ በሁዋላ አልከስይ ትኩስ ቡና ከትኩስ የተቀቀለ ድንች ጋር ይዘው ከተፍ አሉ። ቡናውን ይዘው የመጡት ከአልከሶ (ስልጤ) ሲሆን አብሬት ሲደርሱ ግን ቡናውም ድንቹም ትኩስ ነበሩ።
🔰በሌላ ወቅት እንዲሁ አልከስይ ደረሳዎቻቸውን አስከትለው አብሬት ገቡ የቁባ አባ በጣም ተደስተው ዱአ አደረጉላቸው አልከስይም ልክ አባ ሁረይራ ከሩሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጋቢያቸውን ዘርግተው ሀዲስ እንደተቀበሉት አልከስይም ጋቢያቸውን ዘርግተው አሚን አሚን ብለው የቁባ አባ ዱአ ተቀበሉ ዱአቸውን ሲጨርሱ ዘርግተውት የነበረውን ጋቢያቸውን ሽፍንፍን አድርገው ቋጥረው ይዘው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

እንኳን ለአልከሶ መውሊድ አደረሳቹ

♻️Share & join
♦️👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾

@abretpro
1