ABRET PRO
4.41K subscribers
1.77K photos
63 videos
43 files
525 links
የአብሬት እንዲሁም የቃዲሪይ ሲልሲላ መንዙማዎችን ፣ ከአካቢሮች የሰማናቸውን ቀሰሶች ፣ እንዲሁም ከመሻኢኾቻችን ኪታቦች አንዳንድ ጠቃሚ ነገሮችን የምንማማርበት አጠቃላይ የሀድራ ስራዎችን የምንዘክርበት ቻናል ነው
@Abretpro
Download Telegram
💚
اللهم صل على سيدنا محمد
الفاتح لما أغلق
والخاتم لما سبق
ناصر الحق بالحق
والهادي إلى صراطك المستقيم
وعلى آله حق قدره
ومقداره العظيم
💚
💚የእስነይን ስጦታ

ማሾዎቹ በመደድ ሀድራውን ነቀነቁት
እጅግ የሚማርክ የማሾ/ደዌ መሽረብ ሙቃበላ መንዙማ

https://youtu.be/pV0dgiT7XeI
Forwarded from Abretprobot
‏اللهم إني أعوذ بك من الهم والحزن،
وأعوذ بك من العجز والكسل،
وأعوذ بك من الجبن والبخل،
وأعوذ بك من غلبة الدين وقهر الرجال

امين 🙏
💚
💚💚❤️❤️መገርገበያ
አሰላሙ አለይኩም ሳኪኑል አብሬቲ
አሰላሙ አለይኩም ሳኪኑል አብሬቲ
ያ አበል ራሙዜ ሲራጁል ሀድረቲ

አልሀምዱሊላሂ ረቢል በሪየቲ
ሊአን ወጀደና ቢሀዘል ኒእመቲ
ለቀድ ኸሰሰና ቢኑሪል አብሬቲ
አእኒ አበል ራሙዝ ሲራጁል ሀድረቲ
መአዊል አሂበቲ የውመን ወለይለቲ

ሰላሙ አለይኩሙ ሰይዲ ሳዳቲ
ያ አበል ራሙዜ ፈይዱል አሂበቲ
ተፈድሉ ቢላህ ቁጥቡል ሙሀበቲ
አንቂዙና ቢላህ ቢአይኒ ራህመቲ
ፉቲሁ ባቢኩም ባበል ሙሀበቲ

ወሰላቱሏሂ ወመአ ሰላሚ
አላ ሙሀመዲን ሰፍወተል አናሚ
ወአላ አሊሂ ወሷህቢል ኪራሚ
አልሙጠሂሪነ ሚን ጀሚኢል አልዘሚ
አስቂና ያ ረቢ ካእሰል ሙሀበቲ

አሰላሙ አለይኩም ሳሂቡል ነብወቲ
ያአበል ራሙዜ ገውሰል ኡሙመቲ
ሲሩሁም ወሰለ ሸርቀን ወገርበቲ
ያ አበል ራሙዜ ወጅሃል በሻሸቲ
ፊ ኩሊል አውቃቲ የውመን ወለይሊቲ

ያ ሸምሰል አብሬቲ ሰላሙ አለይኩም
ያ አበል ወሊያ ሰላሙ አለይኩም
ያአበል ፋኢዛ ሰላሙ አለይኩም
ያ አበል ፋቲሃ ሩሂ ፊዳኡኩም
ኢንካነ ዩፋዱ አህለል መወደቲ

ኑሩሏሂ ሀድራ ያአበል ዋሲላ
ፈአንቱም ደዋ ሊዘዊል ኡቀላ
አዲምሁም አዲምሁም ያረበና መውላ
ቢጃሂ ሙሀመድ ሲሩሏሂል አላ
አምጢር መደደሁም ፊ ኩሊል አውቃቲ

ኡህዱሩ ሳዳቲ ፊ ሀዘ ሰአቲ
መአ አህባቢኩም ጀሚኡል አውቃቲ
አስቂና ሳዳቲ ካእሰል መወደቲ
ኡንዙሩና ቢላህ ቢአይኒ ራህመቲ
አጊሱና ቢላህ ፊ የውመል ሺደቲ

የጡፉ ኢለይኩም አርዋሁል ሙሂቢን
ተማየለ ኸልቂ ኢለይኩም አጅመኢን
ያ ወሊየላሂ ያሳዲቀል አሚን
ያአባ ሰፊያት ዚነተል ሷሊሂን
ሰይዱል ኡረፋ ሸይኹል ጠሪቀቲ

ያ አዩሃል ሸይኹ ቁጥቡል አክበሩ
ያ አዩሃል በህሩ ሸምሱ ወቀመሩ
ያ አዩሃል ኑሩ ሶፋኡ ዱረሩ
ያ ክብሪተል አህመር ጢቡ ሙአጠሩ
ኢህፈዝና ሰይዲ ሚን ኩሊል ፊትነቲ

ጡባ ሊአሺቂን ፊ ሀዚል ዘማኒ
ጡባ ሊዋሲሊን ሐድረተል ረሕማኒ
ጡባ ሊሳይቂን ቢቁጥቢል ዘማኒ
ያአበል ራሙዚ ከውሰሩ ጂናኒ
መንበዑ ኑሪላህ አሩሱ ሐድረቲ

ሰላሙ አለይኩሞ ሱለሙል ሀድረቲ
ያ አበል ፈትሂያት ራህመቱል ዑመቲ
ያ አበል ሷፊያት አሩሱል ሀድረቲ
ቁጥቡ ዘማኒና ፊ ሀዘል አውቃቲ
አልሀምዱሊላሂ ሊሀዘል ኒእመቲ
""
""
https://t.me/ABRETPRO
ቴሌግራም ይቀላቀሉን👆🏾
👍
🌼አባናይ መገርገበያ💚

እጅግ ውብ የሆነ የአብሬትይ መድህ ውብ በሆነው በዛኪር አብዱልራህማን አቀራር እስከነ አረብኛ ፅሁፉ

صلى الله على محمد
صلى الله على محمد
وعلى ال محمد

ሰለሏ አላ ሙሀመድ
ሰለሏ አላ ሙሀመድ
ወአላ አሊ ሙሀመድ

https://youtu.be/MZwUMhEyKtc
👌
Forwarded from Abretprobot
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ،
وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ،
وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ،
إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ،
وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ،
كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ،
وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ،
إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ

#صلوا_على_الحبيب_محمد
👌
👍
#ከወርቃማ_የጉራጌ_ሙስሊም_ታሪኮች_ማህደር #ክፍል_4

📍 መጨረሻ ላይ ተደርጎ በነበረው ጦርነት አንድ ቁስለኛ ወድቆ በሞት እና ሽረት መሀል ሆኖ ጀናዛዎች ላይ ሁረል አይኖች ሲወርዱ በአይኑ እንዳየ ተናግሯል ብለን ነበር ያቆምነው ይህ ከሆነ በሁዋላ #ኢማም_ሀሰን_ኢንጃሞ ጦራቸ ሽንፈት ስለገጠመው የሀይል እርዳታ ለመጠየቅ ወደ ጅማው ንጉስ #አባ_ጂፋር ሄዱ ፣ ነገር ግን ሳይሳካላቸው ቀረ ፣ #አባ_ጂፋር ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ከማስተዋል አንፃር ይመስለኛል የሀይል እርዳታ ሳያደርጉላቸው ቀረ ፣ በ1880ዎቹ የጉራጌ ተወላጅ ከነበሩት እናታቸው እና ዋልጋ ሞቼ በእነሞር የሀድያ መሪ ከነበሩት ከአባታቸው የተወለዱት ለእስልምና በጀግንነት ብዙ የሰሩት #ጀግናው_ሀሰን_ኢንጃሞ ብዙም አልቆዩም ከጅማ ሲመለሱ በወባ በሽታ ተይዘው በህመም ምክንያት ወደ ቀጣዩ አለም በሞት ተሻገሩ ፣ #ሀምዛ_ኑርየ #ዑመር ፋርዳ እና ከሽንፈት በሁዋላ ያፈገፈጉ ሰራዊቶች በየገጠሩ ተበተኑ በሁዋላም ከመንግስት ጋር እርቅ ወረደ ::
📍አፄ ሚኒልክ የጦር ሹም አድርገው ወደ ሞህር የላኩት ሹም ( ራስ ጎበና ዳጨ ) ፣ በሀሰን ኢንጃሞ ወቅት እስልምናን የተቀበሉ ሰዎችን በሙሉ በሀይል ያከፍር ጀመር ፣ ሞህር ላይ ድግስ ደግሶ እነዚያ እስልምና የተቀበሉ የየክልሉ ባላባቶችን በሙሉ አስጠርቶ ማህተብ እንዲያስሩና የክርስቲያን ስጋ እንዲበሉ ማስገደድ ጀመረ ፣ አብዛኛዎቻቸውንም በሀይል አከፈረ ፣ ያኔ የጌቶ መሪ የነበሩት ጀግናው #አጋዝ_አምዴነህ የክርስቲያን ስጋ እንዲበሉ እና ማህተም እንዲያስሩ በተጠየቁ ግዜ በጭራሽ አይሆንም እኔ እስልምናዬን የተቀበልኩት በሀሰን ኢንጃሞ አይደለም ፣ ከዛም በፊት ሙስሊም ነኝ አሁን ሀሰን ኢንጃሞ ተሸነፉ ብዬ እስልምናዬን አልለቅም ብለው ይላሉ ፣ ሹሙም ( ራስ ጎበና ዳጨ ) በአጋዝ አምዴነህ እምቢታ ተቆጥቶ በጅራፍ እንዲገረፉ አዘዘ ፣ አርባ ጅራፍ እንደተገረፉም ከሹሙ ጋር የነበረ አንድ ሰው እሳቸው እንዳይገረፉ እየተከላከለ ለሹሙ እንዲህ ሲል ተማፀነ " እባክዎ ይህን የመሰለ ግርማ ይህንን የመሰለ ሰውንት አናጥፋው " (አጋዝ አምዴነህ ግዙፍ እና ሲታዩ የሚማርኩ ሰው ነበሩ) ሹሙም እሺ ብሎ ግርፋቱ እንዲቆም አዘዘ ፣ እሳቸውም እስልምናቸውን ሳይለቁ ቆዩ ፣ በጣም ቁጭት ይዟቸው ባለስልጣኑን ለመክሰስ እስከነ ቁስላቸው አዲስ አበባ ተሳፈሩ ፣ አፄ ሚኒሊክ ጋር ቀርበው ከሰሱ ፣ አፄ ሚኒሊክም አሁን ሹሙ ያለለው እዛው ሞህር ነውና እስኪመለስ አንድ ቦታ ጠብቅና ሲመጣ መጥተህ ክስህን ታቀርባለህ ብለው ይሏቸዋል ፣ ሹሙ ግን ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ አልመጣም ፣ ጦርነቱን ካሸነፈ በሁዋላ ለተወሰኑ ቀናት ብቻ ነው የኖረው ፣ በድንገተኛ ሞት ወደ ቀጣዩ አለም ተሻገረ ፣ በሞቱ የተደናገጡት ሰራዊቶቹ የሀሰን ኢንጃሞን መሞት አልሰሙም ነበርና የሹማችንን ሞት ሀስን ኢንጃሞ የሰማ እንደሆነ መጥቶ ሊያጠቃን ነው የሚል ፍርሀት አደረባቸው ፣ ጀናዝውን ልክ በህይወት እንዳላ ሰው አስመስለው ፈርስ ላይ አስደግፈው አስቀምጠው አጅበው ወደ አዲስ አበባ ወሰዱት ::
📍ከመንግስት ጋር እርቅ ከወረደ ፣ በሁዋላ #ሀምዛኑሪየ የመናገሻ ከተማ አስተዳደር ሆነው ተሾሙ ፣ ከብዙ ቆይታ በሁዋላም በህመም ምክንያት ከዚች አለም በሞት ተለዩ ፣ ማረፊያቸው እዛው ኧዣ ላይ ነው #ዑመር_ፋርዳም ብዙ ቆይተው በህመም ምክንያት ወደ አኼራ ሄዱ ቸሀ ላይም ተቀበሩ ::
📍የሆነው ሆነና ጉራጌ ውስጥ የነበሩ ሙስሊሞች በሰላም መኖር ጀመሩ ከዛ በሁዋላ ነው ጉራጌ ላይ ጀሀድ ቀርቶ በሂክማ ፣ በተዋዱእ ፣ ጥርት ባለ አቂዳ ፣ በነብዩ صلى الله عليه وسلم ሙሀባ ፣ ነብስያን በማፅዳት ና በጥሩ ስነምግባር እያነፀ ሀገራችን ላይ ዲነል ኢላምን በስፋት ያስፋፋውን የሀድራ ስራ #ሀ ተብሎ #በቁባ_አባ ረ.ዐ የተጀመረው
ያለፉት ክፍሎች ላይ አፄ ሚኒሊክ ሹም አድርገው የላኩትን ባለስልጣን ስሙን አልገለፅኩም ነበር ስሙ ( ራስ ጎበና ዳጨ ) ይባላል

https://t.me/ABRETPRO

ቴሌግራም ይቀላቀሉን👆🏾
👍
👌
💚💚የኸሚስ ስጦታ

የአብሬትይ መድህ
በዛኪር አብዱልራህማን

እስከነ ኪታቡ

አሏሁመ ሰሌ አላ ሙሀመዴ
ዚል መአሪጂ ወሰሊም ተስሊማ

اللهم صل على محمد
ذي المعارج وسلم تسليما

https://youtu.be/E5uQM0ow7ow