የ ዑስማን ኢብን አፋን - ጠሮ መስጅድ ወጣት ጀምዓዎች በአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብም ሆነ በሌላ እምነት ተከታዩ ማህበረሰብ በጥሩ ስብእናቸው የተመሰከረላቸው ፣እጅግ ጥሩ በሆነ ስነምግባራቸው የሚታወቁ የሰፈሩ ታዳጊ ብሩህ ወጣቶች ናቸው::
ሚጥሚጣና ዲንጋይ በፌስታል ይዘው መስጂድ ገብተው የሰው አይን ላይ ሲበትኑ ፣ በዲንጋይ የመስጂድ መስታወት ሲሰብሩ፣ ቁርአን ሲወረውሩ ፣ የመስጂዱን ጀምዓ ሽማግሌ ሙአዚን ሳይቀር ሲፈነkቱ የምናስታውሳቸው፣ አድራሻቸው የት እንደሆነ እንኳን በቅጡ የማይታወቁ ረባሽ ስብስቦች ተመሳስሎ በተከፈተ ፌክ አካውንት የመስጂዱን ኻዲሞች ስም ለማጥፋt ቢሞክሩ የሚሰማቸው የለም:: ማን ምን እንደሆነ ሁሉም ጠንቅቆ ያውቃል::
ፎቶ:- ከዚህ ቀደም በነዚሁ ስብስቦች ጥቃt ከደረሰባቸው የመስጂዱ ሙዓዚን ሐጅ ከድር እና የመስጂዱ ጀምዓዎች በጥቂቱ::

❤21💔6😢2👏1
ኸሚስ 💚🔥 | ወአዲም ሰላቲ
የአብሬትዩ ሳኒ መድህ በዛኪር አብዱልራሕማን እስከነ ፅሁፉ
ወአዲም ሰላቲ ወሠላም
ዐላ ሙሐመዲን ፊልኪራም
وادم صلاتى وسلام
على محمد فى الكرام
✍️የዚህን መንዙማው የዛኪር አብዱልራሕማን ሙሉ ወይም ረዘም ያለ ቅጂ ያለው ይተባበረን🙏
https://youtu.be/j5i8B6qQAbQ?si=SAEjutoy3oOzgdAq

YouTube
Abret Menzuma | ወአዲም ሰላቲ
ወአዲም ሰላቲ ወሠላም
ዐላ ሙሐመዲን ፊልኪራም
وادم صلاتى وسلام
على محمد فى الكرام
የአብሬትዩ ሳኒ መድህ በዛኪር አብዱልራሕማን እስከነ ፅሁፉ
ዐላ ሙሐመዲን ፊልኪራም
وادم صلاتى وسلام
على محمد فى الكرام
የአብሬትዩ ሳኒ መድህ በዛኪር አብዱልራሕማን እስከነ ፅሁፉ
❤23
አብሬትዩ ሳኒ ቀደሠላሁ ሢረሁ ነብያችንንﷺ ከመደሁበት አንድ እጅግ ውብ መድህ ማለቂያ ላይ ሸይኻቸውን ሠይዲ ባኡ ሳኒን(አብሬትዩል አወል) ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ መድኸው በዱዓ ይዘጉታል::
ባኡ ሳኒን እናውሳ እንደው በጥቂቱ
ለታመመ ሁላ ናቸው መድሀኒቱ
ልብሳቸው ያበራል ከብርሃንም በላይ
ጠረናቸው ያውዳል ከምርጥ ሽቶ በላይ
እርሰዎን መካድ ነው ረሡልን እንደመካድ
እርሰዎን መውደድም ረሱልን እንደመውደድ
ለመቃብራቸው ክብር ዓይኖች ዝቅ ብለዋል (ተናንሷል)
በእርሱ በርቷል ጨረቃም ዙሐል (ሳተርን)
በተግባራቸው ላይ አፅናን ጌታችን
መጥፎ ድርጊትን ከኛ አርቅልን
ቀነ ቀጠሯችን ሲደርስም ግጠመን
በተውሒድ መሄድን ልክ እንደ ዘይነል ውጁድ
በኡሚዩ ነቢይ በወዳጅህ መጀን
ለመልካም ስራዎች ወፍቀን ግጠመን
ሞታችንን አድርገው የእረፍት
እንደ ታች ወራጆች አታስደንግጠን
አብሮ ሲመጣ ሁሉም ከመሪው ጋር
እኛንም አቅርበን ከአድራሹ ሸይኸ ጋር
መዝገባችንን ስጠን በቀኛችን
በግራ እጃችን አታስረክበን
ወንጀላችንን ማር፣ ነውራችንን ሰትር
ጀነትም አስገባን፣ ከረሱላችን ጋር
{ ከመንዙማ ስንኞች በቀጥታ የተተረጎመ }
እነዚህ ስንኞች ከየትኛው የአብሬትይ መድህ የተወሰዱ ናቸው? ገምቱ:: መልሳችሁን ኮመንት ላይ🙏

❤30😍3🥰2
💚🔥መገርገቢያ
ያዘይነል ከማል || እስከነ ፅሁፉ
ያዘይነል ከማል ያዘይነል ከማል
ሶሊ ዐለይሂ ቢገይሪ ዘዋል
يَا زَينُ الكَمَال يَا زَينُ الكَمَال
صَلِّ عَلَيهِ بِغَيرِ زَوال
https://youtu.be/CYS6kq5Oo4U?si=j7ShxZdD5IlRdA9b
ያዘይነል ከማል || እስከነ ፅሁፉ
ያዘይነል ከማል ያዘይነል ከማል
ሶሊ ዐለይሂ ቢገይሪ ዘዋል
يَا زَينُ الكَمَال يَا زَينُ الكَمَال
صَلِّ عَلَيهِ بِغَيرِ زَوال
https://youtu.be/CYS6kq5Oo4U?si=j7ShxZdD5IlRdA9b
YouTube
Abret Menzuma | ያዘይነል ከማል
የአብሬትዩ ሳኒ መድህ እስከነ ፅሁፉ
ያዘይነል ከማል ያዘይነል ከማል
ሶሊ ዐለይሂ ቢገይሪ ዘዋል
يَا زَينَ الكَمَال يَا زَينَ الكَمَال
صَلِّ عَلَيهِ بِغَيرِ زَوال
ያዘይነል ከማል ያዘይነል ከማል
ሶሊ ዐለይሂ ቢገይሪ ዘዋል
يَا زَينَ الكَمَال يَا زَينَ الكَمَال
صَلِّ عَلَيهِ بِغَيرِ زَوال
❤21👏2
በስድስት አመት የ YouTube ቆይታችን ለመጀመሪያ ግዜ የ 2$ super thanks ስጦታ ከአንዲት መኪያ ሺፋ ከምትባል ተከታታያችን ደረሰን:: እህታችን ይህን ለማድረግ ተጨማሪ ጊዜ እና ርቀት ተጉዛ ከቻናላችን ጋር engage አድርጋለች:: ይህም ከትዩባችን ባገኘችው ነገር መደሰቷን ያሳያል:: ለኛም ጉልበትና ብርታት ሆኖናል:: እናመሰግናለን 🙏
Note:- ወደዚህ ያመጣነው በስድስት አመት የዩቱብ ቆይታችን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን ያደረገቺውን እህታችን ለማመስገን ታስቦ እንጂ gift ላኩ ለማለት አለመሆኑን እና ምንም አይነት ስጦታ የማንፈልግ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን::
Note:- ወደዚህ ያመጣነው በስድስት አመት የዩቱብ ቆይታችን ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን ያደረገቺውን እህታችን ለማመስገን ታስቦ እንጂ gift ላኩ ለማለት አለመሆኑን እና ምንም አይነት ስጦታ የማንፈልግ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን::
❤50🥰6🔥4
🔥💚ኸሚስ | አምሳያው የታጣው
✦✦✦
የሠይድ ጫሌ መድህ በ ሸይኽ ሠኢድ ወረባቦ
አላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዴ ²
ሙሐመድ ባለጣው አምሳያው የታጣው
https://youtu.be/lsuvRSKiVs8?si=k7TvQY1d7l7HrlaB
✦✦✦
የሠይድ ጫሌ መድህ በ ሸይኽ ሠኢድ ወረባቦ
አላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዴ ²
ሙሐመድ ባለጣው አምሳያው የታጣው
https://youtu.be/lsuvRSKiVs8?si=k7TvQY1d7l7HrlaB
YouTube
ሸይኽ ሠኢድ ወረባቦ | አምሳያው የታጣው
የሠይድ ጫሌ መድህ በ ሸይኽ ሠኢድ ወረባቦ
አላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዴ ²
ሙሐመድ ባለጣው አምሳያው የታጣው
አላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዴ ²
ሙሐመድ ባለጣው አምሳያው የታጣው
❤16
መገርገብያ 💚🔥 | ያኢማመል ሐረሚ
ውብ የአብሬትዩ ሳኒ ቀደሠላሁ ሢረሁ መድህ በማዲህ ሸይኽ መኪ እስከነ ፅሁፉ
ሰላት ዐለይኩም ነቢ
ሠላም ዐለይኩም ነቢ ያኢማመል ሐረሚ
صلاة عليكم نبى
سلام عليكم نبى يا امام الحرم
https://youtu.be/XZpYhjTIbfE?si=Aa3LtUL5usPPRcun
ውብ የአብሬትዩ ሳኒ ቀደሠላሁ ሢረሁ መድህ በማዲህ ሸይኽ መኪ እስከነ ፅሁፉ
ሰላት ዐለይኩም ነቢ
ሠላም ዐለይኩም ነቢ ያኢማመል ሐረሚ
صلاة عليكم نبى
سلام عليكم نبى يا امام الحرم
https://youtu.be/XZpYhjTIbfE?si=Aa3LtUL5usPPRcun
YouTube
Abret Menzuma | ያኢማመል ሐረሚ
ውብ የአብሬትዩ ሳኒ ቀደሠላሁ ሢረሁ መድህ በማዲህ ሸይኽ መኪ እስከነ ፅሁፉ
ሰላት ዐለይኩም ነቢ
ሠላም ዐለይኩም ነቢ ያኢማመል ሐረሚ
صلاة عليكم نبى
سلام عليكم نبى يا امام الحرم
ሰላት ዐለይኩም ነቢ
ሠላም ዐለይኩም ነቢ ያኢማመል ሐረሚ
صلاة عليكم نبى
سلام عليكم نبى يا امام الحرم
❤18🤩2
🔥💚ኸሚስ | ወሠሊም ወባሪክ
✦✦✦
ሸይኽ ዐሊ ሪቄ
አላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዴ ²
ወሠሊም ወባሪክ ወዐላ አሊሂ
https://youtu.be/fSak2JMFLdo?si=Fl_icWZajwpagERL
✦✦✦
ሸይኽ ዐሊ ሪቄ
አላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዴ ²
ወሠሊም ወባሪክ ወዐላ አሊሂ
https://youtu.be/fSak2JMFLdo?si=Fl_icWZajwpagERL
YouTube
ሸይኽ አሊ ሪቄ | ወሠሊም ወባሪክ
ሸይኽ ዐሊ ሪቄ
አላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዴ ²
ወሠሊም ወባሪክ ወዐላ አሊሂ
አላሁመ ሶሊ ዐላ ሙሐመዴ ²
ወሠሊም ወባሪክ ወዐላ አሊሂ
❤17
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሠላም ያረሱለላህ
🔥💚አዲስ ነሺዳ በሙንሺድ Fuad Melka
✦✦✦
እንደ አባራሙዞ
ነው የናፍቆት ጉዞ
እንደ ሠይድ ሚቅባስ
ቀን ሌት በእምባ መራስ
እንደሠይድ አርባው
በፍቅሮ ሚያነባው
እንደ ጫሌው ጌታ
ክንድ ይሚያበረታ
ሁሉ ለየቅል ነው
ሠላም ያረሱለላህ ሙሓባ ውዴታው
🔥💚አዲስ ነሺዳ በሙንሺድ Fuad Melka
✦✦✦
እንደ አባራሙዞ
ነው የናፍቆት ጉዞ
እንደ ሠይድ ሚቅባስ
ቀን ሌት በእምባ መራስ
እንደሠይድ አርባው
በፍቅሮ ሚያነባው
እንደ ጫሌው ጌታ
ክንድ ይሚያበረታ
ሁሉ ለየቅል ነው
ሠላም ያረሱለላህ ሙሓባ ውዴታው
❤46
አንድ ሙስሊም ማወቅ ያለበት
የተውሂድ ትምህርት 50 ናቸው
==================== ✍️@haseniye
እያንዳንዱ አካለ-መጠኑ የደረሰና አእምሮው ጤናማ የሆነ ሰው ሊያውቃቸው የሚገቡ 50 የዐቂዳ መሠረቶች (አቃኢድ አል-ኸምሲን) አሉ።
እነዚህም በአላህ መብት 41፣ በነቢያት መብት ደግሞ 9 ናቸው።
1) ስለአላህ ማወቅት ያለብን 41 መሠረታዊ ትምህርቶች (20 ዋጂብ, 20 ሙስተሂል እና 1 ጃኢዝ ናቸው)
//ሀ\\ ዋጂብ (በአላህ ላይ ሊኖሩ የሚገቡ 20 ፍጹማዊ መገለጫዎች
እነዚህ መገለጫዎች አላህ በእነሱ መገለጹ ግድ የሆነና አእምሮ የነሱን አለመኖር ፈጽሞ የማይቀበላቸው ናቸው። ማለትም አእምሯችን በፍጹም አልቀበልም የማይላቸውና አላህም የግድ ሊገለጽባቸው የሚገቡ 20 ሲሆኑ እነሱም በአራት ይመደባሉ::
👉🏼ምድብ አንድ:- ነፍሲያ (የማንነት/የመኖር ባህሪ) አንድ ነው:: እርሱም:-
1️⃣ ውጁድ (وجود) ይባላል:: ትርጉሙም መኖር ማለት ነው:: (አላህ ያለ ነው፣ መኖሩም የራሱ ባህሪ ነው)።
----------
👉🏼ምድብ ሁለት ሰልቢያ (ጉድለትንና ፍጡራንን የመሰሉ ባህሪያትን የሚገፉ ወይም የማይቀበሉ) 5 ናቸው::
2️⃣ ቂደም (قدم): ቀዳሚነት (መጀመሪያ የሌለው መሆን)።
3️⃣ በቃእ (بقاء): ዘላለማዊነት (መጨረሻ የሌለው መሆን)።
4️⃣ ሙኻለፈቱሁ ሊል-ሐዋዲሥ (مخالفته للحوادث): ፍጡራንን ፈጽሞ አለመምሰል (በማንነቱም፣ በባህሪውም ሆነ በሥራው)።
5️⃣ ቂያሙሁ ቢነፍሲህ (قيامه بنفسه): ራሱን ቻይነት (መገኛ ቦታ/አካል ወይም አስገኚ ጌታ የማይፈልግ መሆን)።
6️⃣ ወሕዳኒያ (وحدانية): አንድነት (በማንነቱ፣ በባህሪያቱና በድርጊቶቹ አጋርና ቢጤ የሌለው መሆን)።
-------
👉🏼 ምድብ ሦስት:- መዓኒ (የማንነት መገለጫ የሆኑ የረቂቅ ኃይል መገለጫዎች) 7 ናቸው::
7️⃣ ቁድራ (قدرة): ችሎታ/ኃይል (ሁሉን አድራጊነት)።
8️⃣ ኢራዳ (إرادة): ፍላጎት/ውሳኔ (ሁሉን በራሱ ምርጫና ጥበብ መሻት)።
9️⃣ ዒልም (علم): ዕውቀት (ሁሉን ነገር የነበረውን፣ ያለውንና የሚሆነውን አስቀድሞ አዋቂ መሆን)።
🔟 ሐያት (حياة): ሕያውነት (ፍጹም የሆነ ሕይወት ያለው)።
1️⃣1️⃣ ሰምዕ (سمع): መስማት (ድምፅና ጆሮ ሳይሻ ሰሚ መሆን)።
1️⃣2️⃣ በሶር (بصر): ማየት (ብርሃን ዓይን ሳይሻ ተመልካች መሆን)።
1️⃣3️⃣ ከላም (كلام): ንግግር (ፊደል፣ ቋንቋና ድምፅ ሳይሻ ተናጋሪ መሆን)።
----------
👉🏼 ምድብ አራት:- መዕነዊያ (እላይ የተጠቀሱ የመዓኒ ባህሪያት መኖራቸውን የሚያረጋግጡ) 7 መገለጫዎች
1️⃣4️⃣ ከውኑሁ ቃዲረን (كونه قادرا): ቻይ/ኃያል መሆኑ።
1️⃣5️⃣ ከውኑሁ ሙሪደን (كونه مريدا): ፈቃጅ መሆኑ።
1️⃣6️⃣ ከውኑሁ ዓሊመን (كونه عالما): አዋቂ መሆኑ።
1️⃣7️⃣ ከውኑሁ ሐየን (كونه حيا): ሕያው መሆኑ።
1️⃣8️⃣ ከውኑሁ ሰሚኧን (كونه سميعا): ሰሚ መሆኑ።
1️⃣9️⃣ ከውኑሁ በሲረን (كونه بصيرا): ተመልካች መሆኑ።
2️⃣0️⃣ ከውኑሁ ሙተከሊመን (كونه متكلما): ተናጋሪ መሆኑ።
********
\\ለ// ሙስተሒል (በአላህ ላይ ሊኖሩ የማይችሉ/የማይገቡ) 20 ባህሪያት:- እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት የ20ዎቹ ዋጂብ ባህሪያት ቀጥተኛ ተቃራኒዎች (ጉድለቶች) ሲሆኑ፣ በአላህ ላይ መኖራቸው በአእምሮም በሸሪዓም ፈጽሞ የማይታሰብ ነው።
1. ዐደም (عدم): አለመኖር።
2. ሑዱሥ (حدوث): አዲስ መሆን (አስገኚ መፈለግ)
3. ፈናእ (فناء): መጥፋት/መውደም።
4. ሙማሠለቱሁ ሊል-ሐዋዲሥ (مماثلته للحوادث): ፍጡራንን መምሰል።
5. ኢሕቲያጁሁ ኢላ መሐሊን አው ሙኸሲስ (احتياجه إلى محل أو مخصص): ቦታን ወይም አስገኚን መፈለግ።
6. ተዓዱድ (تعدد): ከአንድ በላይ መሆን (መቆጠር, መብዛት)።
7. ዐጅዝ (عجز): ድክመት/አለመቻል።
8. ከራሃ (كراهة): ተገዳጅነት (የሆነ ነገር ያለፍላጎቱ መከሰት)።
9. ጀህል (جهل): አለማወቅ/ስንፍና።
10. መውት (موت): መሞት።
11. ሶመም (صمم): መስማት አለመቻል።
12. ዐማ (عمى): ማየት አለመቻል።
13. በከም (بكم): መናገር አለመቻል።
14. ከውኑሁ ዐጂዘን (كونه عاجزا): ደካማ መሆንን
15. ከውኑሁ ካሪሀን (كونه كارها): ተገዳጅ መሆንን
16. ከውኑሁ ጃሂለን (كونه جاهلا): የማያውቅ መሆንን
17. ከውኑሁ መይተን (كونه ميتا): ሙት መሆንን
18. ከውኑሁ አሶም (كونه أصم): ደንቆሮ መሆንን
19. ከውኑሁ አዕማ (كونه أعمى): ዕውር መሆንን
20. ከውኑሁ አብከም (كونه أبكم): ዲዳ መሆንን
👆🏾እነዚህ ሸሪዓተል ኢስላምም ይሁን አዕምሮ ሊቀበላቸው የማይችሉና ጉድለቶች ናቸው:: አምላክ እነዚህ ባሕሪያት በፍጹም የማይነኩት ነው::
_
(((ሐ))) ጃኢዝ (በአላህ ላይ ሊሆንም ላይሆንም የሚችል) 1 መገለጫ አለ::
1️⃣ ፊዕሉ ኩሊ ሙምኪኒን አው ተርኩሁ (فعل كل ممكن أو تركه): ማድረግም አለማድረግም የሚቻል, አላህ ቢያደርገውም ባያደርገውም መሆን የሚችል ይባላል::
ማንኛውንም ሊኖር የሚችልን (ፍጡር) ነገር መፍጠር ወይም አለመፍጠር፤ ማድረግ ወይም አለማድረግ የአላህ ፍጹም ምርጫ ነው። (ለምሳሌ፦ ሰውን ማበልጸግ ወይም ማደህየት፣ ሰማይን መፍጠር ወይም አለመፍጠር በአላህ ላይ ግዴታ የለበትም፣ ሙስታሒልም አይደለም፤ የራሱ ፍላጎትና ውሳኔ ብቻ ነው)።
ስለ አላህ እነዚህ 41 አተረጓጎም ማወቅ ለሙስሊም እጅግ አስፈላጊና ተቀዳሚ ትምህርት ነው:: ይህ የሰፊው ሕዝብ የተውሂድ ትምህርት ይባላል:: በትምህርት የመጠቀም ይሁን የጀመረ ሰው ማወቅ ያለበት ዕውቀት ነው:: ቀጣዩ የነቢያት መገለጫዎች ናቸው::
በነቢያት መብት ላይ የሚገቡ ባህሪያት (9 ዝርዝሮች)
አሉ::
ሀ. ዋጂብ:-
በነቢያት ላይ ሊኖሩ የሚገቡ ፍጹም ባህሪያት 4 ናቸው:: ነቢያትና መልክተኞች የአላህን ቃል ለሕዝብ የሚያደርሱ በመሆናቸው፣ እነዚህ ባህሪያት ሊኖሯቸው ግድ ነው።
1) ሲድቅ (صدق): እውነተኛነት (በንግግራቸውም ሆነ በተግባራቸው ፍጹም እውነትን መናገር)
2) አማና (أمانة): ታማኝነት (ከውስጥም ከውጭም ከኃጢአትና ከነውር የጠሩ መሆን)።
3) ተብሊግ (تبليغ): መልዕክትን ማድረስ (የታዘዙትን መለኮታዊ ትዕዛዝ ሳይደብቁና ሳይቀንሱ ማድረስ)።
4. ፈጧና (فطانة): ንቁነት/ብልህነት (ከፍተኛ አእምሯዊ ብቃትና ተከራካሪዎችን የመርታት ችሎታ)።
ለ. ሙስተሒል
በነቢያት ላይ ሊኖሩ የማይችሉ/የማይገቡ 4 ባህሪያት
ከላይ የተጠቀሱት የ4ቱ ዋጂብ ባህሪያት ቀጥተኛ ተቃራኒዎች ሲሆኑ፣ በነቢያት ላይ መከሰታቸው የማይቻል ነው፦
1. ኪዝብ (كذب): ውሸት ወይም መዋሸትን
2. ኺያና (خيانه): ክህደት (ኃጢአት ላይ መውደቅ ወይም ታማኝነትን ማጉደል።)
3. ኪትማን (كتمان): መልዕክትን መደበቅ።
4. በላዳ (بلادة): ዝንጉነት/የአእምሮ መደንዘዝ።
ሐ. ጃኢዝ
በነቢያት ላይ ሊሆን የሚችል ሰዋዊ ባህሪ ሲሆን ይህም በአንድ ምድብ ይጠቃለላል::
አል-አዕራድ አል-በሸሪያ (الأعراض البشرية): የነቢይነትና የመልክተኝነት ደረጃቸውን የማይቀንሱ ሰዋዊ ባህሪያት በእነርሱ ላይ መከሰቱ የሚቻል ነው። (ለምሳሌ፦ መታመም፣ መራብ፣ መጠማት፣ መብላት፣ መጠጣት፣ ማግባት፣ መገበያየት፣ መተኛትና መሞት)።

❤18🥰1👌1
ማጠቃለያ፦
አላህን ስንተረጉም-> 20 ዋጂብ + 20 ሙስተሒል + 1 ጃኢዝ = 41 (በአላህ መብት)
ነቢያትን ስንተረጉም:-> 4 ዋጂብ + 4 ሙስተሒል + 1 ጃኢዝ = 9 (በነቢያት መብት)
በጠቅላላው = 50 የዐቂዳ መሠረቶች (አቃኢድ አል-ኸምሲን) ማወቅ ይጠበቅብናል:: እነዚህ ያልተማረ ሰው ሊደነጋገረው ይችላል::
አላህን ስንተረጉም-> 20 ዋጂብ + 20 ሙስተሒል + 1 ጃኢዝ = 41 (በአላህ መብት)
ነቢያትን ስንተረጉም:-> 4 ዋጂብ + 4 ሙስተሒል + 1 ጃኢዝ = 9 (በነቢያት መብት)
በጠቅላላው = 50 የዐቂዳ መሠረቶች (አቃኢድ አል-ኸምሲን) ማወቅ ይጠበቅብናል:: እነዚህ ያልተማረ ሰው ሊደነጋገረው ይችላል::
❤12🥰3
💚🔥መገርገቢያ || በሕረ ጁዲላህ
ሸይኽ ሠይድ ሚቅባሰል ኑር አብሬትይ አባታቸውን(ሸይኻቸውን) የመደሁበት እጅግ ውብ መድህ እስከነ ፅሁፉ
የአብሬትዩ ሳኒ በጣም ቅርብ በነበሩት ታላቁ ሙሪድ ካቲብ ኑር ሁሴን ልጅ በሸይኽ ኢምራን ሸይኽ ኑር ሁሰይን እና ማዲህ ፉዓድ መልካ እስከነ ፅሁፉ
سلام عليكم بحر جود الله ٢
غياث الأحباب باب فضل الله
ሠላም ዓለይኩም በሕረ ጁዲላህ ²
ጊያሡል አህባብ ባቡ ፈድሊላበ
https://youtu.be/9X7f2W8tbQE?si=rRhaWvgBS8L5jMYF

Abret Menzuma | በሕረ ጁዲላህ
በሕረ ጁዲላህ
ሸይኽ ሠይድ ሚቅባሰል ኑር አብሬትይ አባታቸውን(ሸይኻቸውን) የመደሁበት እጅግ ውብ መድህ እስከነ ፅሁፉ
የአብሬትዩ ሳኒ በጣም ቅርብ በነበሩት ታላቁ ሙሪድ ካቲብ ኑር ሁሴን ልጅ በሸይኽ ኢምራን ሸይኽ ኑር ሁሰይን እና ማዲህ ፉዓድ መልካ እስከነ ፅሁፉ
سلام عليكم بحر جود الله ٢
غياث الأحباب باب فضل الله
ሠላም ዓለይኩም በሕረ ጁዲላህ ²
ጊያሡል አህባብ…

🔥5❤3