Abune gorgorios school nursery_ukg
3.67K subscribers
186 photos
29 videos
126 files
12 links
Download Telegram
ጤና ይስጥልኝ ይህ ለ22 ቅርንጫፍ ት-ቤት ዕጣ የወጣላቸው ተማሪዎች ዝርዝር ነው እስከ ነገ 12/12/2013 ዓ.ም 6፡00 ድረስ ብቻ አዋሬ አጸደ ሕፃናት ት/ቤት ተገኝታችሁ የምዝገባ ፎርም ሞልታችሁ ክፍያ እንድትፈጽሙ እያሳሰብን በተገለጸው ሰዓት ካላስመዘገባችሁ በቦታው ተጠባባቂ ተማሪዎችን የምንጠራ ይሆናል።
እጣ የወጣው ለጀማሪ ተማሪዋች ሲሆን ለኬጂ 2 እና ለኬጂ 3 ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ቀን ሰሞኑን እናሳውቃለን።
ጤና ይስጥልን ለኬጂ 2 እና ለኬጂ 3 ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ነገ 14/12/2013 ዓ.ም 3:00 በአዋሬ አጸደ ህጻናት ፈተና የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን።
ዕጣ ተጠባባቂ የነበራችሁ እስከ ነገ 6፡00 መጥታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን
የተከበራችሁ ወላጆች እንዴት አላችሁ? ጀማሪ ላይ ልጆቻችሁን አስመዝግባችሁ ዕጣ ያልወጣላችሁ ወላጆች ተጠባብቂዎችን ጠርተን ጥቂት ቦታዎች ስለቀሩ በአመዘጋገብ ቅደም ተከተላችሁ መሰረት ስለምናስተናግዳችሁ ሰኞ 17/12/2013 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ አስፈላጊውን ዶክመንት አሟልታችሁ እንድታስመዘግቡ እናሳስባለን።
Forwarded from Esdros S.C
የአክስዮን ማኅበሩ የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ ጀመረ
************************
ነሐሴ፤18 ቀን 2013 ዓ.ም
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በአዲስ ከተማ ወረዳ 7 ውስጥ ከሚገኙ እጅግ በጣም ያረጁ የቀበሌ ቤቶች መካከል በመምረጥ የሙሉ እድሳት ሥራ አስጀምሯል፡፡
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ በኃይሉ ሰለሞን የቤት እድሳቱን ባስጀመሩበት ወቅት ስራው ረጅም ጊዜ እንዳይወስድ ግንባታውን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ እንደሚያስረክቡ ቃል ገብተዋል፡፡ የቤት እድሳት የሚደረግላቸው ነዋሪ ወ/ሮ አበራሽ ተሰማ በቤቱ ረጅም ዓመታት ሲኖሩ አንድም ጊዜ ታድሶ ስለማያውቅ ወደ መፍረሱ የተቃረበ መሆኑን ገልፀው አሁን ግን የአክስዮን ማኅበሩ ስላደረገላቸው ድገፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የአክስዮን ማኅበሩ የበጎ ፍቃድ ሥራዎችን ጊዜና ወቅት ሳይመርጡ በቀጣይ አጠናክረው በማስቀጠል የኅብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እንደሚሠራ የኤስድሮስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ በኃይሉ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡

የአክሲዮን ማህበራችንን ድህረ ገፅ https://esdros.com/e/ እና በፌስቡክ ገፃችን https://www.facebook.com/Esdros-Construction-Trade-and-Industry-SC-282021025628947 በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡
ጤና ይስጥልኝ ውድ ወላጆች እንደምን ሰነበታችሁ? ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎቻችን ወደ ት/ቤት ይዘዋቸው የሚመጡ የትምህርት መሳሪያዎች ናቸው፡፡ ብዛታቸው እንደየ ክፍል ደረጃቸው የሚለያይ ሲሆን ሁሉም ጥራታቸውን የጠበቁና የመገልገያ ጊዜያቸው ያላለፈ መሆኑን አረጋግጣችሁ እንድትገዙ አደራ እንላለን፡፡
ውድ ወላጆች የ1ኛ ክፍል መረጃዎችን ከላይ በተቀመጠው የቴሌግራም ቻነል ስለምታገኙ ቻናሉን እንድትቀላቀሉ በአክብሮት እንጠይቃለን
Forwarded from Esdros ICT
ውድ ተማሪዎቻችን ፣ ወላጆች እንዲሁም መላው ቤተሰብ እንኳን ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያልን ከታች በተቀመጠው የተጠቃሚ መመሪያ /user manual/ መሠረት https://elearning.esdros.com ይህንን ሊንክ በመጠቀም ወይም ከታች ያስቀመጥነውን የሞባይል መተግበሪያ በመጫን የተለያዩ አጋዥ መጽሐፍትን እንዲሁም አጋዥ ቪዲዮችን ማግኘት ይችላሉ::