ጤና ይስጥልን ውድ ወላጆች እንዴት አላችሁ ነገ ጠዋት 4:00 ተማሪዎቻችን በማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የሚያቀርቡት ዝግጅት ስላለ እንድትከታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን።
ጤና ይስጥልን ውድ ወላጆች ከፈተና መርሀ ግብሩ ጋር ባሳወቅወቅነው መሰረት የሰኞ፣ረቡዕ እና ዓርብ ፈረቃ ተማሪዎች ፈተና ወረቀት ለመውስድ ት/ቤት የሚመጡት ረቡዕ በ14/11/2013 ዓ.ም ሲሆን የማክሰኞ፣የሐሙስ እና የቅዳሜ ፈረቃ ተማሪዎች ደግሞ ፈተና ወረቀት ለመውስድ ት/ቤት የሚመጡት ሐሙስ በ15/11/2013 ዓ.ም ይሆናል ።
ጤና ይስጥልኝ ውድ ወላጆች መደበኛው ምዝገባ የተራዘመው ከነርሰሪ ጀምሮ ላሉት ሁሉም ክፍሎች ሲሆን ኤልኬጂ እና ዩኬጂ ላይ አዲስ ለ22 ቱ አዲስ ቅርንጫፍ ማስመዝገብ ለምትፈልጉ ነባር ወላጆች፣ የድርጅቱ ሰራተኞች፣ ባለአክሲዮኖች እና አዲስ ወላጆች ከ28/11/2014 እስከ 01/12/2013 ዓ.ም ቅድመ ምዝገባ ስለሚካሄድ የተማሪውን ውጤት መግልጫ ካርድ ት/ቤት ይዛችሁ በመምጣት ጠዋት ከ3:00 እስከ 6፡30 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 9፡00 ማስመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን
ውድ ወላጆች ለ22 ቱ አዲስ ቅርንጫፍ ት/ቤት ምዝገባ የሚካሄደው አዋሬ አጸደ ሕፃናት መሆኑን እንገልፃለን።
ጤና ይስጥልን ለጀማሪ ተማሪዎች የመደበኛ ምዝገባ ፎርም የሞላችሁ ሰኞ ከ3፡00 እስከ 9፡00 ከቅ/ገብርኤል ሆስፒታል ገባ ብሎ ከአዲሱ የቅድስት አርሴማ እና የቅ/ገብርኤል ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው አዲሱ ቅርንጫፍ ት/ቤታችን በመገኘት የመክፈያ ወረቀት ወስዳችሁ ክፍያውን እንድትፈጽሙ በአክብሮት እንገልጻለን።
ዕጣ የምትጠባበቁ ወላጆች ማክሰኞ በ11/12/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ዕጣ ስለምና ወጣ አዋሬ አጸደ ሕፃናት ት/ቤት ተገኝታችሁ ዕጣ እንድታወጡ እናሳስባለን።
4_5825843126631139786.xlsx
12.7 KB
Share '4_5825843126631139786.xlsx'
ጤና ይስጥልኝ ይህ ለ22 ቅርንጫፍ ት-ቤት ዕጣ የወጣላቸው ተማሪዎች ዝርዝር ነው እስከ ነገ 12/12/2013 ዓ.ም 6፡00 ድረስ ብቻ አዋሬ አጸደ ሕፃናት ት/ቤት ተገኝታችሁ የምዝገባ ፎርም ሞልታችሁ ክፍያ እንድትፈጽሙ እያሳሰብን በተገለጸው ሰዓት ካላስመዘገባችሁ በቦታው ተጠባባቂ ተማሪዎችን የምንጠራ ይሆናል።
እጣ የወጣው ለጀማሪ ተማሪዋች ሲሆን ለኬጂ 2 እና ለኬጂ 3 ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ቀን ሰሞኑን እናሳውቃለን።