Abune gorgorios school nursery_ukg
3.67K subscribers
186 photos
29 videos
126 files
12 links
Download Telegram
ጤና ይስጥልን ውድ ወላጆች ነገ ሰኞ እና ማክሰኞ ተማሪዎች በፈረቃቸው ትምህርት ሙሉ ቀን የሚኖራቸው ይሆናል። የአዲስ ጀማሪ ተማሪዎች ቅድመ ምዝገባ ነገ እንደሚጠናቀቅ ለመጨረሻ ጊዜ ለማሳስብ እንወዳለን!
ጤና ይስጥልን ውድ ወላጆች እንዴት አላችሁ ነገ ጠዋት 4:00 ተማሪዎቻችን በማሕበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የሚያቀርቡት ዝግጅት ስላለ እንድትከታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን።
ጤና ይስጥልን ውድ ወላጆች ከፈተና መርሀ ግብሩ ጋር ባሳወቅወቅነው መሰረት የሰኞ፣ረቡዕ እና ዓርብ ፈረቃ ተማሪዎች ፈተና ወረቀት ለመውስድ ት/ቤት የሚመጡት ረቡዕ በ14/11/2013 ዓ.ም ሲሆን የማክሰኞ፣የሐሙስ እና የቅዳሜ ፈረቃ ተማሪዎች ደግሞ ፈተና ወረቀት ለመውስድ ት/ቤት የሚመጡት ሐሙስ በ15/11/2013 ዓ.ም ይሆናል ።
ጤና ይስጥልኝ ውድ ወላጆች መደበኛው ምዝገባ የተራዘመው ከነርሰሪ ጀምሮ ላሉት ሁሉም ክፍሎች ሲሆን ኤልኬጂ እና ዩኬጂ ላይ አዲስ ለ22 ቱ አዲስ ቅርንጫፍ ማስመዝገብ ለምትፈልጉ ነባር ወላጆች፣ የድርጅቱ ሰራተኞች፣ ባለአክሲዮኖች እና አዲስ ወላጆች ከ28/11/2014 እስከ 01/12/2013 ዓ.ም ቅድመ ምዝገባ ስለሚካሄድ የተማሪውን ውጤት መግልጫ ካርድ ት/ቤት ይዛችሁ በመምጣት ጠዋት ከ3:00 እስከ 6፡30 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 9፡00 ማስመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን
ውድ ወላጆች ለ22 ቱ አዲስ ቅርንጫፍ ት/ቤት ምዝገባ የሚካሄደው አዋሬ አጸደ ሕፃናት መሆኑን እንገልፃለን።
ለኤልኬጂ/ኬጂ-2/ እና ለዩኬጂ /ኬጂ-3/ ነባር ተማሪዎች
የምዝገባ መርሐ ግብር
ለጀማሪ /Nursery/ ክፍል ተማሪዎች የምዝገባ መርሐ ግብር
ጤና ይስጥልን ለጀማሪ ተማሪዎች የመደበኛ ምዝገባ ፎርም የሞላችሁ ሰኞ ከ3፡00 እስከ 9፡00 ከቅ/ገብርኤል ሆስፒታል ገባ ብሎ ከአዲሱ የቅድስት አርሴማ እና የቅ/ገብርኤል ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው አዲሱ ቅርንጫፍ ት/ቤታችን በመገኘት የመክፈያ ወረቀት ወስዳችሁ ክፍያውን እንድትፈጽሙ በአክብሮት እንገልጻለን።
ዕጣ የምትጠባበቁ ወላጆች ማክሰኞ በ11/12/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ዕጣ ስለምና ወጣ አዋሬ አጸደ ሕፃናት ት/ቤት ተገኝታችሁ ዕጣ እንድታወጡ እናሳስባለን።